caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Maaida፣ አንቀጽ 32

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 112 · 5:32

مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ أَنَّهُۥ مَن قَتَلَ نَفْسًۢا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِى ٱلْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ ٱلنَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَآ أَحْيَا ٱلنَّاسَ جَمِيعًا وَلَقَدْ جَآءَتْهُمْ رُسُلُنَا بِٱلْبَيِّنَٰتِ ثُمَّ إِنَّ كَثِيرًا مِّنْهُم بَعْدَ ذَٰلِكَ فِى ٱلْأَرْضِ لَمُسْرِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy32. በዚህ ምክንያት በኢስራኢል ልጆች ላይ «አንዲትን ንጹህ ነፍስን (ያልገደለችን) ወይም በምድር ላይ ምንንም ያላጠፋችን ነፍስ የገደለ ሁሉ ሰዎችን ሁሉ እንደገደለ ነው:: አንዲትን ነፍስ ህያው ያደረጋትም ሰዎችን ሁሉ ህያው እንዳደረገ ነው።» ማለትን ደነገግን። መልዕክተኞቻችንም ግልጽን ተዐምራት አምጥተውላቸዋል። ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ብዙዎቹ በምድር ላይ ወሰንን አላፊዎች ናቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ (መግደል) ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት (ካልሆነ በስተቀር) ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ማለትን ጻፍን፡፡ መልክተኞቻችንም በግልጽ ተዓምራት በእርግጥ መጡዋቸው፡፡ ከዚያም ከዚህ በኋላ ከእነሱ ብዙዎቹ በምድር ላይ ወሰንን አላፊዎች ናቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70