وَكَتَبْنَا عَلَيْهِمْ فِيهَآ أَنَّ ٱلنَّفْسَ بِٱلنَّفْسِ وَٱلْعَيْنَ بِٱلْعَيْنِ وَٱلْأَنفَ بِٱلْأَنفِ وَٱلْأُذُنَ بِٱلْأُذُنِ وَٱلسِّنَّ بِٱلسِّنِّ وَٱلْجُرُوحَ قِصَاصٌ فَمَن تَصَدَّقَ بِهِۦ فَهُوَ كَفَّارَةٌ لَّهُۥ وَمَن لَّمْ يَحْكُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy45. በእነርሱም ላይ በውስጡ ነፍስን በነፍስ፤ አይንን በአይን፤ አፍንጫን በአፍንጫ፤ ጆሮን በጆሮ፤ ጥርስን በጥርስ፤ ይያዛል:: ቁስሎችንም ማመሳሰል አለባቸው ብለን ደነገግን:: ይህንን መብቱን ይቅር ያለ ሁሉ እርሱ ለኃጢአቱ ማሰረዣው ነው:: አላህ ባወረደው መመሪያ የማይፈርዱ ሁሉ እነዚያ በደለኞቹ ማለት እነርሱ ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበእነርሱም ላይ በውስጧ «ነፍስ በነፍስ ዓይንም በዓይን አፍንጫም በአፍንጫ ጆሮም በጆሮ ጥርስም በጥርስ (ይያዛል)፡፡» ቁስሎችንም ማመሳሰል አለባቸው ማለትን ጻፍን፡፡ በእርሱም የመጸወተ (የማረ) ሰው እርሱ ለርሱ (ለሠራው ኃጢአት) ማስተሰሪያ ነው፡፡ አላህም ባወረደው ነገር የማይፈርድ ሰው፤ እነዚያ በደለኞቹ እነርሱ ናቸው፡፡