فَإِنْ عُثِرَ عَلَىٰٓ أَنَّهُمَا ٱسْتَحَقَّآ إِثْمًا فَـَٔاخَرَانِ يَقُومَانِ مَقَامَهُمَا مِنَ ٱلَّذِينَ ٱسْتَحَقَّ عَلَيْهِمُ ٱلْأَوْلَيَٰنِ فَيُقْسِمَانِ بِٱللَّهِ لَشَهَٰدَتُنَآ أَحَقُّ مِن شَهَٰدَتِهِمَا وَمَا ٱعْتَدَيْنَآ إِنَّآ إِذًا لَّمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy107. ሆኖም እነርሱ ኃጢአት (በውሸት ምስክርነት) የተገቡ መሆናቸው ቢታወቅ ከእነዚያ ከሟቹ ቅርብ ዘመዶች ውርስ ከተገባቸው ሁለት ሌሎች ሰዎች በስፍራቸው በምስክሮች ስፍራ ይቆሙና «ምስክርነታችን ከእነርሱ ምስክርነት ይልቅ እውነት ነው ወሰንም አላለፍንም። ያን ጊዜ እኛ ከበዳዩቹ ነን።» ሲሉ በአላህ ይምላሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነርሱም ኃጢአትን (በውሸት መስክረው) የተገቡ መኾናቸው ቢታወቅ ከእነዚያ (ለሟቹ) ቅርቦች በመኾን (ውርስ) ከተገባቸው የኾኑ ሁለት ሌሎች ሰዎች በስፍራቸው (በምስክሮች ስፍራ) ይቆሙና «ምስክርነታችን ከእነሱ ምስክርነት ይልቅ እውነት ነው ወሰንም አላለፍንም ያን ጊዜ እኛ ከበዳዮች ነን» ሲሉ በአላህ ይምላሉ፡፡