caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Maaida፣ አንቀጽ 48

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 112 · 5:48

وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ لِكُلٍّ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةً وَمِنْهَاجًا وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ لَجَعَلَكُمْ أُمَّةً وَٰحِدَةً وَلَٰكِن لِّيَبْلُوَكُمْ فِى مَآ ءَاتَىٰكُمْ فَٱسْتَبِقُوا۟ ٱلْخَيْرَٰتِ إِلَى ٱللَّهِ مَرْجِعُكُمْ جَمِيعًا فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! )ከበፊቱ የነበረውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ አድርገን ባንተ ላይ ቁርኣንን አወረድን:: እናም በመካከላቸው አላህ ባወረደው ህግ ፍረድ:: እውነቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል:: ለሁላችሁም ህግንና መንገድን አደረግን:: አላህ በፈለገ ኖሮ አንድ ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር:: ግን በሰጣችሁ ሕግጋት ሊሞክራችሁ ነው ለእያንዳንዳችሁ መንገዶችን ያደረገው:: እናም በጎ ስራዎችን ለመስራት ተሽቀዳደሙ:: የሁላችሁም መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው:: ከዚያ በእርሱ ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር እውነታ ይነግራችኋል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ፡፡ እውነቱም ከመጣልህ (በኋላ) ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ ከእናንተ ለሁሉም ሕግንና መንገድን አደረግን፡፡ አላህም በሻ ኖሮ አንድ ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር፡፡ ግን በሰጣችሁ ሕግጋት ሊሞክራችሁ (ለያያችሁ)፡፡ በጎ ሥራዎችንም (ለመሥራት) ተሽቀዳደሙ፤ መመለሻችሁ በጠቅላላ ወደ አላህ ነው፡፡ በእርሱም ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር ይነግራችኋል፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70