لَيْسَ عَلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ جُنَاحٌ فِيمَا طَعِمُوٓا۟ إِذَا مَا ٱتَّقَوا۟ وَّءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ ثُمَّ ٱتَّقَوا۟ وَّءَامَنُوا۟ ثُمَّ ٱتَّقَوا۟ وَّأَحْسَنُوا۟ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy93. በእነዚያ በአላህ ባመኑትና በጎ ስራዎችን በሰሩት ላይ ከተጠነቀቁና ካመኑ መልካምን ከሰሩ፤ ከዚያም ከተጠነቀቁና ካመኑ፤ ከዚያም ከተጠነቀቁና ስራንም ካሳመሩ ከመከልከሉ በፊት በተመገቡት ነገር ኃጢአት የለባቸዉም። አላህ ስራቸውን አሳማሪዎቹን ሁሉ ይወዳልና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበእነዚያ ባመኑትና በጎ ሥራዎችን በሠሩት ላይ (ክህደትን) በተጠነቀቁና ባመኑ መልካም ሥራዎችንም በሠሩ ከዚያም (የሚያሰክርንና ቁማርን) በተጠነቀቁና ባመኑ ከዚያም (ከተከለከለው ሁሉ) በተጠነቀቁና (ሥራን) ባሳመሩ ጊዜ (ከመከልከሉ በፊት) በተመገቡት ነገር ኃጢአት የለባቸውም፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡