وَٱتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ ٱبْنَىْ ءَادَمَ بِٱلْحَقِّ إِذْ قَرَّبَا قُرْبَانًا فَتُقُبِّلَ مِنْ أَحَدِهِمَا وَلَمْ يُتَقَبَّلْ مِنَ ٱلْـَٔاخَرِ قَالَ لَأَقْتُلَنَّكَ قَالَ إِنَّمَا يَتَقَبَّلُ ٱللَّهُ مِنَ ٱلْمُتَّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱ ላይ የአደምን ሁለት ልጆች ወሬ (ማለትም) ሁለቱም ቁርባን ባቀረቡና አላህ ከአንደኛቸው ቁርባኑን ተቀብሎ ከሌላው ባልተቀበለበት ጊዜ የሆነውን ታሪክ አንብብላቸው:: ተቀባይነት ያጣው ወንድሙን «እገድልሃለሁ።» አለው። (የተዛተበትም) አለ: «አላህ የሚቀበለው እኮ ከጥንቁቆቹ ብቻ ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበነርሱም ላይ የአደምን ሁለት ልጆች ወሬ ቁርባንን ባቀረቡና (አላህ) ከአንደኛቸው ተቀብሎ ከሌላው ባልተቀበለ ጊዜ (የኾነውን) በእውነት አንብብላቸው፡፡ «በእርግጥ እገድልሃለሁ» አለው፡፡ (ተገዳዩ) «አላህ የሚቀበለው እኮ ከጥንቁቆቹ ብቻ ነው» አለ፡፡