وَإِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ ءَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ ٱتَّخِذُونِى وَأُمِّىَ إِلَٰهَيْنِ مِن دُونِ ٱللَّهِ قَالَ سُبْحَٰنَكَ مَا يَكُونُ لِىٓ أَنْ أَقُولَ مَا لَيْسَ لِى بِحَقٍّ إِن كُنتُ قُلْتُهُۥ فَقَدْ عَلِمْتَهُۥ تَعْلَمُ مَا فِى نَفْسِى وَلَآ أَعْلَمُ مَا فِى نَفْسِكَ إِنَّكَ أَنتَ عَلَّٰمُ ٱلْغُيُوبِ
Amharic Translation - Africa Academy116. (መልዕክተኛች ሙሐመድ ሆይ!) አላህ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ሰዎችን ‹እኔንና እናቴን ከአላህ ውጭ ሁለት አማልዕክት አድርጋችሁ ያዙን።› ብለሃልን?» በሚለው ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ:: ዒሳም አለ፡- «ክብርና ልዕልና ላንተ ብቻ ይሁን! ለእኔ ልለው የማይገባኝን ነገር ማለቴ ፈጽሞ አግባብ አይደለም:: ይህን ተናግሬ ከሆነም ታውቀዋለህ:: አንተ በውስጤ ያለውን ሁሉ ጠንቅቀህ ታውቃለህ:: እኔ ግን ባንተ ውስጥ ያለውን አላውቅም:: አንተ ሩቅ ሚስጥራትን ሁሉ አዋቂ ነህና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- እኔንና እናቴን ከአላህ ሌላ ሁለት አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብላሃልን» በሚለው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ጥራት ይገባህ፤ ለእኔ ተገቢዬ ያልኾነን ነገር ማለት ለኔ አይገባኝም፡፡ ብዬው እንደ ኾነም በእርግጥ ዐውቀኸዋል፡፡ በነፍሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ታውቃለህ፡፡ ግን አንተ ዘንድ ያለውን አላውቅም፡፡ አንተ ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ አንተ ብቻ ነህና» ይላል፡፡