caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Maaida፣ አንቀጽ 41

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 112 · 5:41

يَٰٓأَيُّهَا ٱلرَّسُولُ لَا يَحْزُنكَ ٱلَّذِينَ يُسَٰرِعُونَ فِى ٱلْكُفْرِ مِنَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا بِأَفْوَٰهِهِمْ وَلَمْ تُؤْمِن قُلُوبُهُمْ وَمِنَ ٱلَّذِينَ هَادُوا۟ سَمَّٰعُونَ لِلْكَذِبِ سَمَّٰعُونَ لِقَوْمٍ ءَاخَرِينَ لَمْ يَأْتُوكَ يُحَرِّفُونَ ٱلْكَلِمَ مِنۢ بَعْدِ مَوَاضِعِهِۦ يَقُولُونَ إِنْ أُوتِيتُمْ هَٰذَا فَخُذُوهُ وَإِن لَّمْ تُؤْتَوْهُ فَٱحْذَرُوا۟ وَمَن يُرِدِ ٱللَّهُ فِتْنَتَهُۥ فَلَن تَمْلِكَ لَهُۥ مِنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَمْ يُرِدِ ٱللَّهُ أَن يُطَهِّرَ قُلُوبَهُمْ لَهُمْ فِى ٱلدُّنْيَا خِزْىٌ وَلَهُمْ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy41. መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እነዚያ ወደ ክህደት የሚቻኮሉ ሆነው ልቦቻቸው ሳያምኑ በአፎቻቸው ብቻ «አመንን» ካሉት አስመሳዮችና ከእነዚያም አይሁዶቹ አያሳዝኑህ:: እነርሱ ውሸትን ብቻ አድማጮች ናቸውና:: ገና ወደ አንተ ላልመጡ ለሌሎች ሕዝቦች አድማጮች ናቸው:: ንግግሮችንም ከስፍሮቻቸው ወደ ሌላ በመቀየር መልዕክት ያጣምማሉ። «ይህንን የተጣመመውን ከተሰጣችሁ ያዙት:: ካልተሰጣችሁም ተጠንቀቁ።» ይላሉ:: አላህ መፈተንን የሚሻበትን ሰው ሁሉ ለእርሱ ከአላህ ለመከላከል ፍጹም አትችልም:: እነዚያ ማለት አላህ ልቦቻቸውን ማጥራትን ያልሻላቸው ሰዎች ናቸው:: ለእነርሱም በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አለባቸው:: ለእነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለምም ሌላ ከባድ ቅጣት አለባቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአንተ መልክተኛ ሆይ! እነዚያ በክሕደት የሚቻኮሉት ከእነዚያ ልቦቻቸው ያላመኑ ሲኾኑ በአፎቻቸው «አመንን» ካሉትና ከእነዚያም አይሁድ ከኾኑት ሲኾኑ አያሳዝኑህ፡፡ (እነርሱ) ውሸትን አዳማጮች ናቸው፡፡ ለሌሎች ወዳንተ ላልመጡ ሕዝቦች አዳማጮች ናቸው፡፡ ንግግሮችን ከቦታቸው ሌላ ያጣምማሉ፡፡ «ይህንን (የተጣመመውን) ብትስሰጡ ያዙት፡፡ ባትስሰጡትም ተጠንቀቁ» ይላሉ፡፡ አላህም መፈተኑን የሚሻበትን ሰው ለእርሱ ከአላህ (ለመከላከል) ምንንም አትችልም፡፡ እነዚህ እነዚያ አላህ ልቦቻቸውን ማጥራትን ያልሻላቸው ናቸው፡፡ ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው፡፡ ለእነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከባድ ቅጣት አላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70