جَعَلَ ٱللَّهُ ٱلْكَعْبَةَ ٱلْبَيْتَ ٱلْحَرَامَ قِيَٰمًا لِّلنَّاسِ وَٱلشَّهْرَ ٱلْحَرَامَ وَٱلْهَدْىَ وَٱلْقَلَٰٓئِدَ ذَٰلِكَ لِتَعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَأَنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy97. አላህ ያ የተከበረውን ቤት ካዕባን፤ ክልክል የሆነውን ወር፤ ወደ መካ የሚወስደውን መስዋዕቱንና ባለ ምልክቶቹን መንጋዎች ለሰዎች እምነት (ዋልታ) መቋቋሚያ አደረገ:: ይህ የሆነው አላህ በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑንና ሁሉን ነገር አዋቂ መሆኑን እንድታውቁ ዘንድ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከዕባን፣ የተከበረውን ቤት፣ ክልክል የኾነውንም ወር፣ መስዋዕቱንና ባለ ምልክቶቹንም መንጋዎች አላህ ለሰዎች መቋቋሚያ አደረገ፡፡ ይህ አላህ በሰማያት ያለውን ሁሉ በምድርም ያለውን ሁሉ የሚያውቅ መኾኑን አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ መኾኑን እንድታውቁ ነው፡፡