caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Maaida፣ አንቀጽ 4

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 112 · 5:4

يَسْـَٔلُونَكَ مَاذَآ أُحِلَّ لَهُمْ قُلْ أُحِلَّ لَكُمُ ٱلطَّيِّبَٰتُ وَمَا عَلَّمْتُم مِّنَ ٱلْجَوَارِحِ مُكَلِّبِينَ تُعَلِّمُونَهُنَّ مِمَّا عَلَّمَكُمُ ٱللَّهُ فَكُلُوا۟ مِمَّآ أَمْسَكْنَ عَلَيْكُمْ وَٱذْكُرُوا۟ ٱسْمَ ٱللَّهِ عَلَيْهِ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلْحِسَابِ

Amharic Translation - Africa Academy4.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ሙስሊሞች ) ምን ምን እንደተፈቀደላቸው ይጠይቁሃል:: «ለእናንተ መልካሞች ሁሉ እና እነዚያም አላህ ካሳወቃችሁ አሰልጣኞች ሆናችሁ ያስተማራችኋቸው አዳኞች ውሾች ያደኑት ሁሉ ተፈቀደላችሁ።» በላቸው:: አላህ ካስተማራችሁ እውቀት ታስተምሯቸዋላችሁ:: ከያዙላችሁ ነገር ብሉ:: የአላህንም ስምም አውሱበት:: አላህን ፍሩ:: አላህ ምርመራው ፈጣን ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለእነርሱ ምን እንደተፈቀደላቸው ይጠይቁሃል፡፡ በላቸው፡- «ለእናንተ መልካሞች ሁሉና እነዚያም ከአዳኞች አሰልጣኞች ኾናችሁ ያስተማራችኋቸው (ያደኑት) ተፈቀደላችሁ፡፡ አላህ ከአስተማራችሁ ዕውቀት ታስተምሯቸዋላችሁ፡፡ ለእናንተም ከያዙላችሁ ነገር ብሉ፡፡ በርሱም ላይ የአላህን ስም አውሱ፡፡ አላህንም ፍሩ አላህ ምርመራው ፈጣን ነውና፡፡»
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70