caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Maaida፣ አንቀጽ 5

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 112 · 5:5

ٱلْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ ٱلطَّيِّبَٰتُ وَطَعَامُ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ حِلٌّ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّ لَّهُمْ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَٰفِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِىٓ أَخْدَانٍ وَمَن يَكْفُرْ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy5. (አማኞች ሆይ!) ዛሬ መልካም ነገሮች ለእናንተ ተፈቀዱ:: የእነዚያ መጽሐፍን የተሰጡ ሰዎች ምግብም (እርድ) ለእናንተ የተፈቀደ ነው:: ምግባችሁም ለእነርሱ የተፈቀደ ነው:: ከምዕመናት ሴቶችም ጥብቆቹ፤ ከእነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡ ህዝቦች ሴቶችም መካከል ጥብቆቹ፤ ዝሙተኞችና የሚስጥር ወዳጅ ያዢዎች ሳትሆኑ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቧቸው የተፈቀዱ ናቸው:: በአላህ ካመነ በኋላ ከእምነቱ ወደ ክህደት የሚመለስ ሁሉ በእርግጥ ስራው ተበላሸ:: በመጨረሻም ቀን ከከሳሪዎች ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqዛሬ መልካሞች ሁሉ ለናንተ ተፈቀዱ፡፡ የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ (ያረዱት) ለእናንተ የተፈቀደ ነው፡፡ ምግባችሁም ለነሱ የተፈቀደ ነው፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ (ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው)፡፡ ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70