caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Maaida፣ አንቀጽ 82

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 112 · 5:82

لَتَجِدَنَّ أَشَدَّ ٱلنَّاسِ عَدَٰوَةً لِّلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱلْيَهُودَ وَٱلَّذِينَ أَشْرَكُوا۟ وَلَتَجِدَنَّ أَقْرَبَهُم مَّوَدَّةً لِّلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّا نَصَٰرَىٰ ذَٰلِكَ بِأَنَّ مِنْهُمْ قِسِّيسِينَ وَرُهْبَانًا وَأَنَّهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy82. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድና እነዚያ በአላህ ያጋሩት ለእነዚያ ላመኑት በጠላትነት ከሌሎች ሁሉ የበረቱ ሆነው ታገኛቸዋለህ:: ከእነርሱ መካከል እነዚያ «እኛ ክርስቲያኖች ነን።» ያሉትን ደግሞ ለእነዚያ ላመኑት በወዳጅነት ይበልጥ የቀረቧቸው ሆነው ታገኛቸዋለህ:: ይህም ከእነርሱ መካከል ቀሳውስትና መነኮሳት በመኖራቸውና እነርሱም የማይኮሩ በመሆናቸው ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአይሁዶችንና እነዚያን ያጋሩትን ለእነዚያ ለአመኑት በጠላትነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የበረቱ ኾነው በእርግጥ ታገኛለህ፡፡ እነዚያንም «እኛ ክርስቲያኖች ነን» ያሉትን ለእነዚያ ለአመኑት በወዳጅነት በእርግጥ ይበልጥ የቀረቧቸው ኾነው ታገኛለህ፡፡ ይህ ከእነሱ ውስጥ ቀሳውስትና መነኮሳት በመኖራቸውና እነሱም የማይኮሩ በመኾናቸው ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70