قَالَ رَجُلَانِ مِنَ ٱلَّذِينَ يَخَافُونَ أَنْعَمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِمَا ٱدْخُلُوا۟ عَلَيْهِمُ ٱلْبَابَ فَإِذَا دَخَلْتُمُوهُ فَإِنَّكُمْ غَٰلِبُونَ وَعَلَى ٱللَّهِ فَتَوَكَّلُوٓا۟ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy23. ከእነዚያ አላህን ከሚፈሩትና አላህ ጸጋውን ከለገሰላቸው ሰዎች መካከል ሁለት ሰዎች «በእነርሱ በሀያሎቹ ላይ በሩን ግቡ:: በገባችሁ ጊዜ እናንተ አሸናፊዎች ናችሁ:: ትክክለኛ አማኞችም እንደሆናችሁ በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ።» አሏቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከእነዚያ (አላህን) ከሚፈሩትና አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሰላቸው የኾኑ ሁለት ሰዎች «በእነርሱ (በኀያሎቹ) ላይ በሩን ግቡ፡፡ በገባችሁትም ጊዜ እናንተ አሸናፊዎች ናችሁ፡፡ ምእመናንም እንደኾናችሁ በአላህ ላይ ተመኩ» አሉ፡፡