caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Maaida፣ አንቀጽ 110

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 112 · 5:110

إِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ ٱذْكُرْ نِعْمَتِى عَلَيْكَ وَعَلَىٰ وَٰلِدَتِكَ إِذْ أَيَّدتُّكَ بِرُوحِ ٱلْقُدُسِ تُكَلِّمُ ٱلنَّاسَ فِى ٱلْمَهْدِ وَكَهْلًا وَإِذْ عَلَّمْتُكَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ وَإِذْ تَخْلُقُ مِنَ ٱلطِّينِ كَهَيْـَٔةِ ٱلطَّيْرِ بِإِذْنِى فَتَنفُخُ فِيهَا فَتَكُونُ طَيْرًۢا بِإِذْنِى وَتُبْرِئُ ٱلْأَكْمَهَ وَٱلْأَبْرَصَ بِإِذْنِى وَإِذْ تُخْرِجُ ٱلْمَوْتَىٰ بِإِذْنِى وَإِذْ كَفَفْتُ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ عَنكَ إِذْ جِئْتَهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْهُمْ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy110. አላህ እንዲህ በሚልበት ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ላንተና ለእናትህ የዋልኩላችሁን ውለታ አስታውስ:: በሩሀል ቁዱስ (በጅብሪል) አጠነከርኩህ:: በሕጻንነትህም አድገህም ሰዎችን ማናገር ቻልክ። መጽሐፉንና ጥበብን ተውራትንና ኢንጂልንም አስተማርኩህ:: ከጭቃም የወፍ ቅርጽ ዓይነት በፈቃዴ መሥራት ቻልክ:: በሷ ውስጥ ነፈህ:: በፈቃዴም እውነተኛ በራሪ ሆነች:: እውር ሆኖ የተወለደንና ለምጻምን በፈቃዴ መፈወስ ቻልክ:: ሟችንም በፈቃዴ አስነሳህ:: የኢስራኢልንም ልጆች ግልጽ መረጃ ባመጣህላቸው ጊዜ ሊያጠቁህ ሲያስቡ አቀብኩልህ:: ከመካከላቸዉም እነዚያ በአላህ የካዱት ‹ይህ ግልጽ ድግምት ነው› አሉ:: ይህን ሁሉ ውለታዬን አስታውስ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ በሚል ጊዜ (አስታውስ)፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! በአንተና በእናትህ ላይ (የዋልኩላችሁን) ጸጋዬን አስታውስ፡፡ በሕፃንነትና በከፈኒሳነት (የበሰለ ሰው ኾነህ) ሰዎችን የምትናገር ስትኾን በቅዱስ መንፈስ (በጂብሪል) ባበረታሁህ ጊዜ፤ ጽሕፈትንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ባስተማርኩህ ጊዜ፣ ከጭቃም የወፍ ቅርጽ ብጤ በፈቃዴ በምትሠራና በውስጧ በምትነፋ በፈቃዴም ወፍ በምትኾን ጊዜ፣ ዕውርም ኾኖ የተወለደንና ለምጻምንም በፈቃዴ በምታሽር ጊዜ፣ ሙታንንም በፈቃዴ (ከመቃብራቸው) በምታወጣ ጊዜ፣ የእስራኤልንም ልጆች በተአምራት በመጣህባቸውና ከእነሱ እነዚያ የካዱት ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም ባሉ ጊዜ፣ (ሊገድሉህ ሲያስቡህ) ከአንተ ላይ በከለከልኩልህም ጊዜ (ያደረግሁልህን ውለታ አስታውስ)፡፡»
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70