إِنَّآ أَنزَلْنَا ٱلتَّوْرَىٰةَ فِيهَا هُدًى وَنُورٌ يَحْكُمُ بِهَا ٱلنَّبِيُّونَ ٱلَّذِينَ أَسْلَمُوا۟ لِلَّذِينَ هَادُوا۟ وَٱلرَّبَّٰنِيُّونَ وَٱلْأَحْبَارُ بِمَا ٱسْتُحْفِظُوا۟ مِن كِتَٰبِ ٱللَّهِ وَكَانُوا۟ عَلَيْهِ شُهَدَآءَ فَلَا تَخْشَوُا۟ ٱلنَّاسَ وَٱخْشَوْنِ وَلَا تَشْتَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِى ثَمَنًا قَلِيلًا وَمَن لَّمْ يَحْكُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْكَٰفِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy44. ተውራትን በውስጡ ለሰዎች መመሪያና ብርሃን ያለባት ሲሆን አወረድነው:: እነዚያ ትዕዛዙን የተቀበሉት ነብያት በአይሁዳውያን ላይ በእርሱ ይፈርዳሉ:: ሊቃውንቱና አዋቂዎቹም ከአላህ መጽሐፍን እንዲጠብቁ በተደረጉትና በእርሱ ላይ መስካሪዎቹ በመሆናቸው እንዲሁ በሱ ይፈርዳሉ:: እናም ሰዎችን አትፍሩ:: እኔን ብቻ ፍሩኝ:: በአንቀፆቼም አነስተኛን ዋጋ አትለውጡ አትግዙ:: እነዚያ አላህ ባወረደው መመሪያ ያልፈረዱ ሁሉ ከሓዲያን ማለት እነርሱው ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትኾን አወረድን፡፡ እነዚያ ትዕዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ፡፡ ሊቃውንቱና ዐዋቂዎቹም ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ በተደረጉትና በርሱም ላይ መስካሪዎች በኾኑት (ይፈርዳሉ)፡፡ ሰዎችንም አትፍሩ፡፡ ፍሩኝም፡፡ በአንቀጾቼም አነስተኛን ዋጋ አትለውጡ፡፡ አላህ ባወረደው ነገር ያልፈረደ ሰው እነዚያ ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡