يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ قَدْ جَآءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَيَعْفُوا۟ عَن كَثِيرٍ قَدْ جَآءَكُم مِّنَ ٱللَّهِ نُورٌ وَكِتَٰبٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy15. እናንተ የመጽሐፍ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ መካከል ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ብዙውንም የሚተው ሲሆን መልዕክተኛችን ሙሐመድ መጣላችሁ:: ከአላህ ዘንድም ብርሃንና ገላጭ የሆነ መጽሐፍ መጣላችሁ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን (ሙሐመድ) በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡