مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ وَكُنتُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًا مَّا دُمْتُ فِيهِمْ فَلَمَّا تَوَفَّيْتَنِى كُنتَ أَنتَ ٱلرَّقِيبَ عَلَيْهِمْ وَأَنتَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ شَهِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy117. «የነገርኳቸው ያን ያዘዝከኝን ብቻ ነው:: ‹የእኔም የእናንተም ጌታ የሆነውን አላህን ብቻ አምልኩ ነው› ያልኳቸው:: በመካከላቸው በነበርኩበት ወቅት ስለ እነርሱ መስካሪ ነበርኩ:: እንዳርግ ካደረግከኝ በኋላ ግን የእነርሱ ጠባቂና ተቆጣጣሪ አንተው ብቻ ነበርክ:: አንተ በሁሉም ነገር ላይ መስካሪ ነህና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ ማለትን እንጂ ለነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ በውስጣቸውም እስካለሁ ድረስ በነርሱ ላይ ተጣባበቂ ነበርኩ፡፡ በተሞላኸኝም ጊዜ (ባነሳኸኝ ጊዜ) አንተ በነሱ ላይ ተጠባባቂ ነበርክ፡፡ አንተም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነህ፡፡»