لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ قُلْ فَمَن يَمْلِكُ مِنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا إِنْ أَرَادَ أَن يُهْلِكَ ٱلْمَسِيحَ ٱبْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُۥ وَمَن فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًا وَلِلَّهِ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا يَخْلُقُ مَا يَشَآءُ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ «አላህ ማለት የመርየም ልጅ አልመሲህ ነው።» ያሉ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ በአላህ ካዱ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የመርየምን ልጅ አልመሲህንና እናቱን እንደዚሁም በምድር ያለን ፍጡር ሁሉ ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳን የሚችል ማን ነው? የሰማያትና የምድር የመካከላቸዉም ንግስና የአላህ ብቻ ነው:: የሚፈልገውን ይፈጥራል:: አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ የመርየምን ልጅ አልመሲሕን እናቱንም በምድር ያለንም ሁሉ ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳንን የሚችል ማነው በላቸው፡፡ የሰማያትና የምድር የመካከላቸውም ንግሥና የአላህ ብቻ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡