caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Maaida፣ አንቀጽ 12

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 112 · 5:12

وَلَقَدْ أَخَذَ ٱللَّهُ مِيثَٰقَ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ وَبَعَثْنَا مِنْهُمُ ٱثْنَىْ عَشَرَ نَقِيبًا وَقَالَ ٱللَّهُ إِنِّى مَعَكُمْ لَئِنْ أَقَمْتُمُ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَيْتُمُ ٱلزَّكَوٰةَ وَءَامَنتُم بِرُسُلِى وَعَزَّرْتُمُوهُمْ وَأَقْرَضْتُمُ ٱللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا لَّأُكَفِّرَنَّ عَنكُمْ سَيِّـَٔاتِكُمْ وَلَأُدْخِلَنَّكُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ فَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ مِنكُمْ فَقَدْ ضَلَّ سَوَآءَ ٱلسَّبِيلِ

Amharic Translation - Africa Academy12. አላህ የኢስራኢል ልጆችን የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዘባቸው:: ከእነርሱም መካከል አስራ ሁለት አለቆችን አስነሳን:: አላህም አላቸው፡- «ከእናንተ ጋር ነኝ። ሶላትን ደንቡን ጠብቃችሁ ብትሰግዱ፤ ግዴታ ምጽዋትንም በትክክል ብትሰጡ፤ በመልዕክተኞቼም በሙሉ ብታምኑና በሚያደርጉት ትግል ብትረዷቸው፤ ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩ ኃጢአቶቻችሁንም አብስላችኋለሁ:: ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም በእርግጥ አስገባችኋለሁ:: ከዚህ በኋላ ከናንተ መካከል በአላህ የካደ ግን ከቀጥተኛው መንገድ ተሳሳተ::»
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህም የእስራኤልን ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዘባቸው፡፡ ከነርሱም ዐስራ ሁለትን አለቆች አስነሳን፡፡ አላህም አላቸው፤ «እኔ ከናንተ ጋር ነኝ፤ ሶላትን ብታስተካክሉ ግዴታ ምጽዋትንም ብትሰጡ በመልክተኞቼም ብታምኑ ብትረዱዋቸውም ለአላህም መልካም ብድርን ብታበድሩ ኀጢአቶቻችሁን ከናንተ በእርግጥ አብሳለሁ፡፡ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችም በእርግጥ አገባችኋለሁ፡፡ ከዚህም በኋላ ከእናንተ የካደ ሰው ቀጥተኛውን መንገድ በእርግጥ ተሳሳተ፡፡»
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70