فَبِمَا نَقْضِهِم مِّيثَٰقَهُمْ لَعَنَّٰهُمْ وَجَعَلْنَا قُلُوبَهُمْ قَٰسِيَةً يُحَرِّفُونَ ٱلْكَلِمَ عَن مَّوَاضِعِهِۦ وَنَسُوا۟ حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا۟ بِهِۦ وَلَا تَزَالُ تَطَّلِعُ عَلَىٰ خَآئِنَةٍ مِّنْهُمْ إِلَّا قَلِيلًا مِّنْهُمْ فَٱعْفُ عَنْهُمْ وَٱصْفَحْ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy13. ቃል ኪዳናቸውን በማፍረሳቸው ረገምናቸው:: ልቦቻቸውንም ደረቆች አደረግን:: ቃላትን ከቦታዎቻቸው ይለውጣሉ:: ከታዘዙትም ነገር ከፊሉን ተው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ጥቂቶቹ ሲቀሩ ክዳትን ከማየት አትወገድም:: ለእነርሱ ይቅርታ አድርግ:: እለፋቸዉም:: አላህ መልካም ሰሪዎችን ሁሉ ይወዳልና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqቃል ኪዳናቸውንም በማፍረሳቸው ረገምናቸው፡፡ ልቦቻቸውንም ደረቆች አደረግን፡፡ ቃላትን ከቦታዎቻቸው ይለውጣሉ፡፡ በርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተው፡፡ ከእነሱም ጥቂቶች ሲቀሩ ከነርሱ የኾነን ክዳት የምታውቅባቸው ከመኾን አትወገድም፡፡ ከእነርሱም ይቅርታ አድርግ እለፋቸውም፡፡ አላህ መልካም ሠሪዎችን ይወዳልና፡፡