يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَتَّخِذُوا۟ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ دِينَكُمْ هُزُوًا وَلَعِبًا مِّنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ وَٱلْكُفَّارَ أَوْلِيَآءَ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy57. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከበፊታችሁ መጽሐፉን ከተሰጡትና ከእነዚያ ሃይማኖታችሁን መሳለቂያና መጫዎቻ ካደረጉት ከሓዲያን መካከል ወዳጆች አታድርጉ:: ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ አላህን ብቻ ፍሩ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከበፊታችሁ መጽሐፍን ከተሰጡት እነዚያን ሃይማኖታችሁን ማላገጫና መጫወቻ አድርገው የያዙትን ከሓዲዎችንም ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ምእምናንም እንደኾናችሁ አላህን ፍሩ፡፡