إِذْ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ يَٰعِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ هَلْ يَسْتَطِيعُ رَبُّكَ أَن يُنَزِّلَ عَلَيْنَا مَآئِدَةً مِّنَ ٱلسَّمَآءِ قَالَ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy112. «ሃዋሪያቶቹም፡- ‹የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ጌታህ ከሰማይ ማዕድ ሊያወርድልን ይቻላልን?› ባሉ ጊዜ የሆነውን አስታውስ። ዒሳም፡-‹ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ አላህን ብቻ ፍሩ።› አለ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሐዋርያት፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ጌታህ በእኛ ላይ ከሰማይ ማእድን ሊያወርድልን ይችላልን» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ምእመናን እንደ ኾናችሁ አላህን ፍሩ» አላቸው፡፡