بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَوْفُوا۟ بِٱلْعُقُودِ أُحِلَّتْ لَكُم بَهِيمَةُ ٱلْأَنْعَٰمِ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ غَيْرَ مُحِلِّى ٱلصَّيْدِ وَأَنتُمْ حُرُمٌ إِنَّ ٱللَّهَ يَحْكُمُ مَا يُرِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy1. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ቃልኪዳኖቻችሁን ሙሉ:: በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር የግመል፤ የከብት፤ የበግና የፍየል እንስሳት ተፈቅዶላችኋል:: በሐጅ ስራ ላይ ሆናችሁ አውሬ ማደንን እንደ ተፈቀደ ሳትቆጥሩ የሚበሉት የዱር እንስሳትም ተፈቅደውላችኋል:: አላህ የሚፈልገውን ሁሉ ነገር ይፈርዳልና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! በቃል ኪዳኖች ሙሉ፡፡ በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር፡፡ የግመል፣ የከብት፣ የበግና የፍየል እንስሳዎች ለእናንተ ተፈቀዱ፤ እናንተ በሐጅ ሥራ ላይ ኾናችሁ ማደንን የተፈቀደ ሳታደረጉ ፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈርዳል፡፡