يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَن يَرْتَدَّ مِنكُمْ عَن دِينِهِۦ فَسَوْفَ يَأْتِى ٱللَّهُ بِقَوْمٍ يُحِبُّهُمْ وَيُحِبُّونَهُۥٓ أَذِلَّةٍ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ أَعِزَّةٍ عَلَى ٱلْكَٰفِرِينَ يُجَٰهِدُونَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَا يَخَافُونَ لَوْمَةَ لَآئِمٍ ذَٰلِكَ فَضْلُ ٱللَّهِ يُؤْتِيهِ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy54. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ውስጥ ከሃይማኖቱ ወደ ክህደት የሚመለስ ሁሉ አላህ በእርሱ ስፍራ የሚወዳቸውና የሚወዱትን በምዕምናን ላይ ትሁቶች፤ በከሓዲያን ላይ ሀያላን፤ የሆኑትንና በአላህ መንገድ የሚታገሉን የወቃሽንም ወቀሳ የማይፈሩ ህዝቦችን ያመጣል:: ይህ የአላህ ችሮታ ነው:: ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል:: አላህ ችሮታው ሰፊ ሁሉንም አዋቂ ነውና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ውስጥ ከሃይማኖቱ የሚመለስ ሰው አላህ (በእነርሱ ስፍራ) የሚወዳቸውንና የሚወዱትን፣ በምእመናን ላይ ትሑቶች፣ በከሓዲዎች ላይ ኀያላን የኾኑን በአላህ መንገድ የሚታገሉን የወቃሽን ወቀሳ የማይፈሩን ሕዝቦች በእርግጥ ያመጣል፡፡ ይኸ የአላህ ችሮታ ነው፤ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፤ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡