caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Maaida፣ አንቀጽ 46

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 112 · 5:46

وَقَفَّيْنَا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم بِعِيسَى ٱبْنِ مَرْيَمَ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ وَءَاتَيْنَٰهُ ٱلْإِنجِيلَ فِيهِ هُدًى وَنُورٌ وَمُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ وَهُدًى وَمَوْعِظَةً لِّلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy46. በነብያቶች ፈለግ ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን በስተፊቱ ያለውን ተውራትን አረጋጋጭ ሲሆን አስከተልን:: ኢንጅልም በውስጡ ቀጥተኛ መመሪያና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለውን ተውራትን የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆቹም መሪና ገሳጭ ሲሆን ሰጠነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበፈለጎቻቸውም (በነቢያቶቹ ፈለግ) ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን አስከተልን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲኾን፡፡ ኢንጂልንም ሰጠነው በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሳጭ ሲኾን፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70