caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ At-Tawba التوبة

129 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 113

بَرَآءَةٌ مِّنَ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦٓ إِلَى ٱلَّذِينَ عَٰهَدتُّم مِّنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

Amharic Translation - Africa Academy1.(ሙስሊሞች ሆይ! ይህ) ከአላህና ከመልዕክተኛው ወደ እነዚያ ቃል ኪዳን ወደ ተጋባችኋቸው አጋሪዎች የሚደርስ የውል መሻሪያ መልዕክት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَسِيحُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ أَرْبَعَةَ أَشْهُرٍ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّكُمْ غَيْرُ مُعْجِزِى ٱللَّهِ وَأَنَّ ٱللَّهَ مُخْزِى ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy2. (ከሓዲያን ሆይ!) በምድር ላይ አራት ወሮችን ጸጥተኛ ስትሆኑ ተንቀሳቀሱ:: እናንተ ከአላህ ቅጣት የማታመልጡ መሆናችሁንና አላህ ከሓዲያንን አዋራጅ መሆኑንም እወቁ፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَذَٰنٌ مِّنَ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦٓ إِلَى ٱلنَّاسِ يَوْمَ ٱلْحَجِّ ٱلْأَكْبَرِ أَنَّ ٱللَّهَ بَرِىٓءٌ مِّنَ ٱلْمُشْرِكِينَ وَرَسُولُهُۥ فَإِن تُبْتُمْ فَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ وَإِن تَوَلَّيْتُمْ فَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّكُمْ غَيْرُ مُعْجِزِى ٱللَّهِ وَبَشِّرِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِعَذَابٍ أَلِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy3. (ይህ) ከአላህና ከመልዕክተኛው በታላቁ ሐጅ ቀን የወጣ አላህ እና መልዕክተኛው ከአጋሪዎቹ ንጹህ መሆናቸውን የሚገልፅ አዋጅ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከክህደት ብትጸጸቱ እርሱ ለእናንተ በላጭ ነው:: ከእምነት ብትሸሹ ግን እናንተ አላህን የማታቅቱት መሆናችሁን እወቁ በማለት ወደ ሰዎች የሚደርስ ማስታወቂያ ነው:: እነዚያን በአላህ የካዱትን ሰዎች በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا ٱلَّذِينَ عَٰهَدتُّم مِّنَ ٱلْمُشْرِكِينَ ثُمَّ لَمْ يَنقُصُوكُمْ شَيْـًٔا وَلَمْ يُظَٰهِرُوا۟ عَلَيْكُمْ أَحَدًا فَأَتِمُّوٓا۟ إِلَيْهِمْ عَهْدَهُمْ إِلَىٰ مُدَّتِهِمْ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy4. እነዚያ ከአጋሪዎቹ መካከል እነዚያ ቃል ኪዳን የተጋባችሁላቸውና ከዚያ ምንም ያላጎደሉባችሁ፤ በእናንተ ላይ ለማጥቃት አንድንም ያልተባበሩባችሁ ቃል ኪዳናቸውን እስከ ጊዜያቸው መጨረሻ ድረስ ሙሉላቸው:: አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِذَا ٱنسَلَخَ ٱلْأَشْهُرُ ٱلْحُرُمُ فَٱقْتُلُوا۟ ٱلْمُشْرِكِينَ حَيْثُ وَجَدتُّمُوهُمْ وَخُذُوهُمْ وَٱحْصُرُوهُمْ وَٱقْعُدُوا۟ لَهُمْ كُلَّ مَرْصَدٍ فَإِن تَابُوا۟ وَأَقَامُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَوُا۟ ٱلزَّكَوٰةَ فَخَلُّوا۟ سَبِيلَهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy5. የተከበሩት ወሮች ባለቁ ጊዜ አጋሪዎቹን ባገኛችሁባቸው ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው:: ያዟቸዉም:: ክበቧቸዉም:: እነርሱንም ለመጠባበቅ ስትሉ በየኬላው ላይ ተቀመጡ:: ሆኖም ቢጸጸቱ፤ ሶላትን በደንቡ ቢሰግዱና ግዴታ የሆነባቸውን የዘካ ምጽዋትን በትክክል ከሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ ٱلْمُشْرِكِينَ ٱسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَٰمَ ٱللَّهِ ثُمَّ أَبْلِغْهُ مَأْمَنَهُۥ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአጋሪዎች መካከል አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅህ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው:: ከዚያ ወደ ሰላም ማግኛው ስፍራ አድርሰው:: ይህም የሆነው እነርሱ የማያውቁ ህዝቦች በመሆናቸው ነው ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَيْفَ يَكُونُ لِلْمُشْرِكِينَ عَهْدٌ عِندَ ٱللَّهِ وَعِندَ رَسُولِهِۦٓ إِلَّا ٱلَّذِينَ عَٰهَدتُّمْ عِندَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ فَمَا ٱسْتَقَٰمُوا۟ لَكُمْ فَٱسْتَقِيمُوا۟ لَهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy7. ለአጋሪዎች ከአላህና ከመልዕክተኛው ዘንድ የሰላም ቃል ኪዳን እንዴት ይኖራቸዋል? እነዚያ በተከበረው መስጊድ ዘንድ ቃል ኪዳን የገባችሁላቸው ሰዎች ብቻ ሲቀሩ:: እነዚያማ በቃል ኪዳናቸው ለእናንተ ቀጥ እስካሉላችሁ ድረስ ለእርሱም በቃላችሁ ቀጥ በሉላቸው:: አላህ ጥንቁቆችን ሁሉ ይወዳልና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَيْفَ وَإِن يَظْهَرُوا۟ عَلَيْكُمْ لَا يَرْقُبُوا۟ فِيكُمْ إِلًّا وَلَا ذِمَّةً يُرْضُونَكُم بِأَفْوَٰهِهِمْ وَتَأْبَىٰ قُلُوبُهُمْ وَأَكْثَرُهُمْ فَٰسِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy8. በእናንተ ላይ ቢያይሉ ዝምድናንና ቃልኪዳንን የማይጠብቁ ሰዎች ሲሆኑ እንዴት ከአላህና ከመልዕክተኛው ዘንድ ቃልኪዳን ይኖራቸዋል? በአፎቻቸው ይሸነግሏችኋል:: ልቦቻቸው ግን እምቢ ይላሉ:: አብዛኞቻቸዉም አመጸኞች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱشْتَرَوْا۟ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا فَصَدُّوا۟ عَن سَبِيلِهِۦٓ إِنَّهُمْ سَآءَ مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy9. በአላህ አናቅጽ ጥቂትን ዋጋ ገዙ:: እናም ከመንገዱም ሰዎችን አገዱ:: እነርሱ ይሰሩት የነበሩት ሥራም እጅግ በጣም ከፋ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يَرْقُبُونَ فِى مُؤْمِنٍ إِلًّا وَلَا ذِمَّةً وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُعْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy10. በትክክለኛ አማኞች ላይ ዝምድናንም ሆነ ቃል ኪዳንን አይጠብቁም:: ወሰን አላፊዎች ማለት እነርሱው ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِن تَابُوا۟ وَأَقَامُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَوُا۟ ٱلزَّكَوٰةَ فَإِخْوَٰنُكُمْ فِى ٱلدِّينِ وَنُفَصِّلُ ٱلْـَٔايَٰتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy11. (ሙስሊሞች ሆይ!) ቢጸጸቱ፤ ሶላትንም ደንቡን አሟልተው ቢሰገዱና ግድ የሆነባቸውንም ዘካን በትክክል ቢሰጡ የእምነት ወንድሞቻችሁ ናቸው:: ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን እናብራራለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن نَّكَثُوٓا۟ أَيْمَٰنَهُم مِّنۢ بَعْدِ عَهْدِهِمْ وَطَعَنُوا۟ فِى دِينِكُمْ فَقَٰتِلُوٓا۟ أَئِمَّةَ ٱلْكُفْرِ إِنَّهُمْ لَآ أَيْمَٰنَ لَهُمْ لَعَلَّهُمْ يَنتَهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy12. ከቃልኪዳናቸው በኋላ መሀላዎቻቸውን ካፈረሱና ሃይማኖታችሁን ካንቋሸሹ የክህደት መሪዎች ከክህደት ተግባራቸው ይከለከሉ ዘንድ ተዋጓቸው:: እነርሱ ምንም ቃልኪዳን የላቸዉምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَا تُقَٰتِلُونَ قَوْمًا نَّكَثُوٓا۟ أَيْمَٰنَهُمْ وَهَمُّوا۟ بِإِخْرَاجِ ٱلرَّسُولِ وَهُم بَدَءُوكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍ أَتَخْشَوْنَهُمْ فَٱللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخْشَوْهُ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy13. እነዚያ መሀላዎቻቸውን ያፈረሱትን፤ መልዕክተኛውንም ከሀገር ለማውጣት ያሰቡትን ህዝቦች እነርሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ጦርነት የጀመሯችሁን ህዝቦች ሲሆኑ ለምን አትወጓቸዉም? ትፈሯቸዋላችሁን? ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ አላህን ይበልጥ ልትፈሩት የተገባው ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَٰتِلُوهُمْ يُعَذِّبْهُمُ ٱللَّهُ بِأَيْدِيكُمْ وَيُخْزِهِمْ وَيَنصُرْكُمْ عَلَيْهِمْ وَيَشْفِ صُدُورَ قَوْمٍ مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy14. (ሙስሊሞች ሆይ!) ተጋደሏቸው:: አላህ በእጆቻችሁ ያሰቃያቸዋል:: ያዋርዳቸዋልም:: በእነርሱም ላይ ይረዳችኋል:: የአማኝ ህዝቦችን ልቦችንም ያሽራል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيُذْهِبْ غَيْظَ قُلُوبِهِمْ وَيَتُوبُ ٱللَّهُ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy15. የልቦቻቸውንም ቁጭት ያስወግዳል:: አላህ ከሚፈልገው ሰው ላይ ጸጸትን ይቀበላል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ حَسِبْتُمْ أَن تُتْرَكُوا۟ وَلَمَّا يَعْلَمِ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ جَٰهَدُوا۟ مِنكُمْ وَلَمْ يَتَّخِذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَا رَسُولِهِۦ وَلَا ٱلْمُؤْمِنِينَ وَلِيجَةً وَٱللَّهُ خَبِيرٌۢ بِمَا تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy16. አላህ ከመካከላችሁ በትክክል ለአላህ መስዋዕት የሚከፍሉትንና (የታገሉትንና) ከአላህ፣ ከመልዕክተኛውና ከትክክለኛ አማኞች በስተቀር አማካሪ ያልያዙትን ክፍሎች ለይቶ ሳያውቅ (ሳይገልጽ) የምትተዉ መሰላችሁን? አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ዉስጠ አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا كَانَ لِلْمُشْرِكِينَ أَن يَعْمُرُوا۟ مَسَٰجِدَ ٱللَّهِ شَٰهِدِينَ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِم بِٱلْكُفْرِ أُو۟لَٰٓئِكَ حَبِطَتْ أَعْمَٰلُهُمْ وَفِى ٱلنَّارِ هُمْ خَٰلِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy17. አጋሪዎች በራሳቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ ሲሆኑ የአላህን መስጊዶች ሊንከባከቡ አይገባቸዉም:: እነዚያ ሥራዎቻቸው የተበላሹና በአኼራም በእሳት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا يَعْمُرُ مَسَٰجِدَ ٱللَّهِ مَنْ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَأَقَامَ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَى ٱلزَّكَوٰةَ وَلَمْ يَخْشَ إِلَّا ٱللَّهَ فَعَسَىٰٓ أُو۟لَٰٓئِكَ أَن يَكُونُوا۟ مِنَ ٱلْمُهْتَدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy18. የአላህን መስጊዶች የሚንከባከቡ ሰዎች በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመኑ፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው የሚሰግዱ፤ ግዴታ ምጽዋትን በትክክል የሚሰጡ፤ ከአላህ ሌላ ምንንም ያልፈሩ ሰዎች ብቻ ናቸው:: እንዲህ ያሉት ሰዎች ቀናዉን መስመር ከያዙት መሆናቸው ይከጀላልና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَجَعَلْتُمْ سِقَايَةَ ٱلْحَآجِّ وَعِمَارَةَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ كَمَنْ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَجَٰهَدَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ لَا يَسْتَوُۥنَ عِندَ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy19. ሰዎችን ማጠጣትንና የተከበረውን መስጊድ መንከባከብን፤ በአላህና በመጨረሻው ቀን እንዳመነና በአላህ መንገድም እንደታገለ ሰው እምነትና ትግል አደረጋችሁትን? በአላህ ዘንድ ፈጽሞ ሁለቱ ተግባሮች አይስተካከሉም:: አላህ በዳይ ህዝቦችን ሁሉ ወደ ቀጥተኛው መንገድ አይመራምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَهَاجَرُوا۟ وَجَٰهَدُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ أَعْظَمُ دَرَجَةً عِندَ ٱللَّهِ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْفَآئِزُونَ

Amharic Translation - Africa Academy20. እነዚያ በአላህ ያመኑት ከየአገሮቻቸዉም የተሰደዱት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸዉም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት አላህ ዘንድ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው:: ፍላጎታቸውን ያገኙ ማለትም እነርሱው ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُبَشِّرُهُمْ رَبُّهُم بِرَحْمَةٍ مِّنْهُ وَرِضْوَٰنٍ وَجَنَّٰتٍ لَّهُمْ فِيهَا نَعِيمٌ مُّقِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy21. ጌታቸው ከእርሱ በሆነው እዝነትና ውዴታ፤ በውስጧ የማያቋርጥ መጠቀሚያ ባለባት ገነትም ያበስራቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا إِنَّ ٱللَّهَ عِندَهُۥٓ أَجْرٌ عَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy22. በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያበስራቸዋል:: አላህ እርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አለና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَتَّخِذُوٓا۟ ءَابَآءَكُمْ وَإِخْوَٰنَكُمْ أَوْلِيَآءَ إِنِ ٱسْتَحَبُّوا۟ ٱلْكُفْرَ عَلَى ٱلْإِيمَٰنِ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy23. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አባቶቻችሁንና ወንድሞቻችሁን ክህደትን ከእምነት አብልጠው ከወደዱ ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዟቸው:: ከናንተ መካከል እነርሱን ወዳጅ የሚያደርጓቸው ሁሉ በዳዮች ማለት እነርሱው ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ إِن كَانَ ءَابَآؤُكُمْ وَأَبْنَآؤُكُمْ وَإِخْوَٰنُكُمْ وَأَزْوَٰجُكُمْ وَعَشِيرَتُكُمْ وَأَمْوَٰلٌ ٱقْتَرَفْتُمُوهَا وَتِجَٰرَةٌ تَخْشَوْنَ كَسَادَهَا وَمَسَٰكِنُ تَرْضَوْنَهَآ أَحَبَّ إِلَيْكُم مِّنَ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَجِهَادٍ فِى سَبِيلِهِۦ فَتَرَبَّصُوا۟ حَتَّىٰ يَأْتِىَ ٱللَّهُ بِأَمْرِهِۦ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْفَٰسِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አባቶቻችሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁ፤ ወንድሞቻችሁ፤ ሚስቶቻችሁ ዘመዶቻችሁ፤ የሰበሰባችኋቸው ሀብቶች፤ መክሰሯን የምትፈሯት ንግድና የምትወዷቸው መኖሪያዎች በእናንተ ዘንድ ከአላህ፤ ከመልዕክተኛውና በእርሱ መንገድ ከመታገል ይበልጥ የተወደዱ ከሆኑ አላህ ጉዳዩን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ በላቸው:: አላህ አመጸኞች ህዝቦችን ሁሉ አይመራም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَقَدْ نَصَرَكُمُ ٱللَّهُ فِى مَوَاطِنَ كَثِيرَةٍ وَيَوْمَ حُنَيْنٍ إِذْ أَعْجَبَتْكُمْ كَثْرَتُكُمْ فَلَمْ تُغْنِ عَنكُمْ شَيْـًٔا وَضَاقَتْ عَلَيْكُمُ ٱلْأَرْضُ بِمَا رَحُبَتْ ثُمَّ وَلَّيْتُم مُّدْبِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy25. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ በብዙ የጦር ሜዳዎች ላይ እገዛውን ለግሶላችኋል:: የሁነይንም ቀን ብዛታችሁ ባስደነቀቻችሁና ለእናንተም ብዛት ምንም ባልጠቀመቻችሁ ጊዜ ምድርም ከስፋቷ ጋር በጠበበቻችሁና ከዚያ ተሸናፊዎች ሆናችሁም በዞራችሁ ጊዜ ረዳችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ أَنزَلَ ٱللَّهُ سَكِينَتَهُۥ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ وَعَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ وَأَنزَلَ جُنُودًا لَّمْ تَرَوْهَا وَعَذَّبَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَذَٰلِكَ جَزَآءُ ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy26. ከዚያም አላህ እርጋታውን በመልዕክተኛውና በምዕመናኖች ላይ አወረደ:: ያላያችኋቸውንም ሰራዊት አወረደ:: እነዚያን የካዱትንም ሰዎች በመግደልና በመማረክ አሰቃየ:: ይህም የከሓዲያን ፍዳ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ يَتُوبُ ٱللَّهُ مِنۢ بَعْدِ ذَٰلِكَ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy27. ከዚያም ከዚህ በኋላ አላህ ከሚፈልገው ሰው ላይ ጸጸትን ይቀበላል:: አላህ እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّمَا ٱلْمُشْرِكُونَ نَجَسٌ فَلَا يَقْرَبُوا۟ ٱلْمَسْجِدَ ٱلْحَرَامَ بَعْدَ عَامِهِمْ هَٰذَا وَإِنْ خِفْتُمْ عَيْلَةً فَسَوْفَ يُغْنِيكُمُ ٱللَّهُ مِن فَضْلِهِۦٓ إِن شَآءَ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy28. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው:: እናም ከዚህ ዓመታቸው በኋላ ወደ ተከበረው መስጊድ እንዳይቀርቡ። ድህነትንም ብትፈሩ አላህ ቢፈልግ ከችሮታው በእርግጥ ያከብራችኋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَٰتِلُوا۟ ٱلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَلَا بِٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَلَا يُحَرِّمُونَ مَا حَرَّمَ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَلَا يَدِينُونَ دِينَ ٱلْحَقِّ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ حَتَّىٰ يُعْطُوا۟ ٱلْجِزْيَةَ عَن يَدٍ وَهُمْ صَٰغِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy29. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከእነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡ ሰዎች መካከል እነዚያን በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑትን ክፍሎች አላህና መልዕክተኛው እርም ያደረጉትንም እርም የማያደርጉትን፤ እውነተኛውንም ሃይማኖት የማይቀበሉትን የተዋረዱ ሆነው ግብርን በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጓቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَتِ ٱلْيَهُودُ عُزَيْرٌ ٱبْنُ ٱللَّهِ وَقَالَتِ ٱلنَّصَٰرَى ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ ٱللَّهِ ذَٰلِكَ قَوْلُهُم بِأَفْوَٰهِهِمْ يُضَٰهِـُٔونَ قَوْلَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِن قَبْلُ قَٰتَلَهُمُ ٱللَّهُ أَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy30. አይሁድ «ኡዘይር የአላህ ልጅ ነው።» አሉ:: ክርስቲያኖችም «አል-መሲህ የአላህ ልጅ ነው።» አሉ:: ይህ በአፎቻቸው የሚናገሩት ጸያፍ ቃላቸው ነው:: የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የካዱትን (ሰዎች) ቃል ያመሳስላሉ:: አላህ ያጥፋቸው:: ከእውነት እንዴት ያፈነግጣሉ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱتَّخَذُوٓا۟ أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَٰنَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ ٱللَّهِ وَٱلْمَسِيحَ ٱبْنَ مَرْيَمَ وَمَآ أُمِرُوٓا۟ إِلَّا لِيَعْبُدُوٓا۟ إِلَٰهًا وَٰحِدًا لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ سُبْحَٰنَهُۥ عَمَّا يُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy31. አይሁድና ክርስቲያኖች ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንዱን አምላክ አላህን ብቻ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲሆኑ ሊቃውንቶቻቸውን፤ መነኮሳቶቻቸውንና የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ:: ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላክ የለም:: አላህ ግን ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُرِيدُونَ أَن يُطْفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفْوَٰهِهِمْ وَيَأْبَى ٱللَّهُ إِلَّآ أَن يُتِمَّ نُورَهُۥ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْكَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy32. ከሓዲያን የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ:: እርሱ (አላህ) ከሓዲያን ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጂ ሌላን አይሻም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلْهُدَىٰ وَدِينِ ٱلْحَقِّ لِيُظْهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْمُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy33. አላህ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ መልዕክተኛው ሙሓመድን በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ አድርጎ የላከው ብቸኛ አምላክ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ كَثِيرًا مِّنَ ٱلْأَحْبَارِ وَٱلرُّهْبَانِ لَيَأْكُلُونَ أَمْوَٰلَ ٱلنَّاسِ بِٱلْبَٰطِلِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ يَكْنِزُونَ ٱلذَّهَبَ وَٱلْفِضَّةَ وَلَا يُنفِقُونَهَا فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ فَبَشِّرْهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy34. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሊቃውንትና ከመነኮሳት ብዙዎቹ የሰዎችን ገንዘቦች በውሸትም ይበላሉ:: ከአላህም መንገድም ሰዎችን ያግዳሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም ወርቅንና ብርን የሚያደልቡትን በአላህም መንገድ ላይ የማያወጧቸውን ሰዎች በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ يُحْمَىٰ عَلَيْهَا فِى نَارِ جَهَنَّمَ فَتُكْوَىٰ بِهَا جِبَاهُهُمْ وَجُنُوبُهُمْ وَظُهُورُهُمْ هَٰذَا مَا كَنَزْتُمْ لِأَنفُسِكُمْ فَذُوقُوا۟ مَا كُنتُمْ تَكْنِزُونَ

Amharic Translation - Africa Academy35. (በብሩና በወርቁ) ላይ በገሀነም እሳት ውስጥ በሚግሉበትና ግንባሮቻቸውም፣ ጎኖቻቸውም፣ ጀርቦቻቸውም በእርሱ በሚተኮሱበት ቀን አሳማሚ በሆነ ቅጣት አብስራቸው:: «ይህ ለነፍሶቻችሁ ያደለባችሁት ነው:: ታደልቡት የነበራችሁትንም ቅመሱ።» ይባላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ عِدَّةَ ٱلشُّهُورِ عِندَ ٱللَّهِ ٱثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِى كِتَٰبِ ٱللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ مِنْهَآ أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلْقَيِّمُ فَلَا تَظْلِمُوا۟ فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ وَقَٰتِلُوا۟ ٱلْمُشْرِكِينَ كَآفَّةً كَمَا يُقَٰتِلُونَكُمْ كَآفَّةً وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy36. የወራት ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አስራ ሁለት ወር ብቻ ነው:: ከእነርሱም መካከል አራቱ የተከበሩ ወሮች ናቸው:: ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው:: በእነርሱ ውስጥም (ክብሮቻቸውን በመጣስ) ነፍሶቻችሁን አትበድሉ:: አጋሪዎችንም በአንድ ላይ ሆነው እንደሚጋደሏችሁ በአንድ ላይ ሆናችሁ ተጋደሏቸው:: አላህ በእርዳታው እርሱኑ ከሚፈሩት ጋር መሆኑን እወቁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا ٱلنَّسِىٓءُ زِيَادَةٌ فِى ٱلْكُفْرِ يُضَلُّ بِهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ يُحِلُّونَهُۥ عَامًا وَيُحَرِّمُونَهُۥ عَامًا لِّيُوَاطِـُٔوا۟ عِدَّةَ مَا حَرَّمَ ٱللَّهُ فَيُحِلُّوا۟ مَا حَرَّمَ ٱللَّهُ زُيِّنَ لَهُمْ سُوٓءُ أَعْمَٰلِهِمْ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy37. የአንዱን ወር ክብር ወደ ሌላው ማዘግየት በክህደት ላይ ክህደትን መጨመር ነው:: በዚህ ተግባር ላይ እነዚያ በአላህ የካዱት (ሰዎች) ይሳሳቱበታል:: በአንደኛው ዓመት የተፈቀደ ያደርጉታል:: በሌላው ዓመት ደግሞ ያወግዙታል:: ይህም አላህ ያከበራቸውን ወሮች ቁጥር ሊሞሉበትና አላህ እርም ያደረገውን ደግሞ የተፈቀደ ሊያደርጉበት ነው:: መጥፎ ሥራዎቻቸው ለእነርሱ ተዋበላቸው:: አላህ ከሓዲያን ህዝቦችን ወደ ቀናው መንገድ አይመራም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَا لَكُمْ إِذَا قِيلَ لَكُمُ ٱنفِرُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ ٱثَّاقَلْتُمْ إِلَى ٱلْأَرْضِ أَرَضِيتُم بِٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا مِنَ ٱلْـَٔاخِرَةِ فَمَا مَتَٰعُ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ إِلَّا قَلِيلٌ

Amharic Translation - Africa Academy38. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! «በአላህ መንገድ ለመታገል ዝመቱ።» በተባላችሁ ጊዜ ወደ ምድር የምትወዘፉት ለምንድን ነው? የቅርቢቱን ህይወት ከመጨረሻይቱ ህይወት ይበልጥ ወደዳችሁን? የቅርቢቱ ህይወት ጥቅም ከመጨረሻይቱ ህይወት አንፃር ጥቂት እንጂ ምንም አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا تَنفِرُوا۟ يُعَذِّبْكُمْ عَذَابًا أَلِيمًا وَيَسْتَبْدِلْ قَوْمًا غَيْرَكُمْ وَلَا تَضُرُّوهُ شَيْـًٔا وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy39. ( አማኞች ሆይ!) ለዘመቻ ባትወጡ አላህ አሳማሚ ቅጣት ይቀጣችኋል:: ከናንተ ሌላ የሆኑን ህዝቦችም ይለውጣል:: አላህን በምንም አትጎዱትምም:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا تَنصُرُوهُ فَقَدْ نَصَرَهُ ٱللَّهُ إِذْ أَخْرَجَهُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ثَانِىَ ٱثْنَيْنِ إِذْ هُمَا فِى ٱلْغَارِ إِذْ يَقُولُ لِصَٰحِبِهِۦ لَا تَحْزَنْ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَنَا فَأَنزَلَ ٱللَّهُ سَكِينَتَهُۥ عَلَيْهِ وَأَيَّدَهُۥ بِجُنُودٍ لَّمْ تَرَوْهَا وَجَعَلَ كَلِمَةَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ٱلسُّفْلَىٰ وَكَلِمَةُ ٱللَّهِ هِىَ ٱلْعُلْيَا وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy40. (ሙስሊሞች ሆይ!) ነብዩ ሙሐመድን ባትረዱት እነዚያ በአላህ የካዱት ህዝቦች የሁለት ሰዎች ሁለተኛ ሆኖ ከመካ ባስወጡት ጊዜ አላህ ረድቶታል:: ሁለቱም በዋሻው ሳሉ ለጓደኛው «አትዘን አላህ ከእኛ ጋር ነውና» ባለ ጊዜ አላህ እርጋታውን በእርሱ ላይ አወረደ:: ባላያችኋቸዉም ሰራዊት አበረታው:: የእነዚያን በአላህ የካዱትን ሰዎች ቃል የበታች አደረገ:: የአላህ ቃል ግን የበላይ ነው:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱنفِرُوا۟ خِفَافًا وَثِقَالًا وَجَٰهِدُوا۟ بِأَمْوَٰلِكُمْ وَأَنفُسِكُمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy41.(አማኞች ሆይ!) ቀላሎችም ከባዶችም ኾናችሁ ዝመቱ:: በአላህ መንገድ በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ታገሉ :: ይህ ተግባር የምታውቁ ከሆናችሁ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَوْ كَانَ عَرَضًا قَرِيبًا وَسَفَرًا قَاصِدًا لَّٱتَّبَعُوكَ وَلَٰكِنۢ بَعُدَتْ عَلَيْهِمُ ٱلشُّقَّةُ وَسَيَحْلِفُونَ بِٱللَّهِ لَوِ ٱسْتَطَعْنَا لَخَرَجْنَا مَعَكُمْ يُهْلِكُونَ أَنفُسَهُمْ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ إِنَّهُمْ لَكَٰذِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጠራህባቸው ነገር ቅርብ ጥቅምና መካከለኛ ጉዞ በሆነ ኖሮ በተከተሉህ ነበር:: ግን በእነርሱ ላይ መንገዲቱ ራቀችባቸው:: «በቻልንም ኖሮ ከናንተ ጋር በወጣን ነበር» ሲሉ በአላህ ይምላሉ:: እራሳቸውን ለጥፋት (በውሸት) ይዳርጋሉ :: አላህ እነርሱ ውሸታሞች መሆናቸውን ያውቃል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَفَا ٱللَّهُ عَنكَ لِمَ أَذِنتَ لَهُمْ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَكَ ٱلَّذِينَ صَدَقُوا۟ وَتَعْلَمَ ٱلْكَٰذِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) አላህ ይቅር ብሎሀል:: እነዚያ እውነተኞቹ እስከሚገለጹልህና ውሸታሞቹን ለይተህ እስከምታውቅ ድረስ ለእነርሱ ከዘመቻ እንዲቀሩ ለምን ፈቀድክላቸው?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يَسْتَـْٔذِنُكَ ٱلَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ أَن يُجَٰهِدُوا۟ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ وَٱللَّهُ عَلِيمٌۢ بِٱلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው ከመታገላቸው ለመቅረት ፈቃድን አይጠይቁህም:: አላህም በትክክል የሚፈሩትን ሰዎች ሁሉ አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا يَسْتَـْٔذِنُكَ ٱلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَٱرْتَابَتْ قُلُوبُهُمْ فَهُمْ فِى رَيْبِهِمْ يَتَرَدَّدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ፈቃድ የሚጠይቁህ እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑት፤ ልቦቻቸው የተጠራጠሩት ሰዎች ብቻ ናቸው:: እነርሱም በጥርጣሬያቸው ውስጥ ይዋልላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ أَرَادُوا۟ ٱلْخُرُوجَ لَأَعَدُّوا۟ لَهُۥ عُدَّةً وَلَٰكِن كَرِهَ ٱللَّهُ ٱنۢبِعَاثَهُمْ فَثَبَّطَهُمْ وَقِيلَ ٱقْعُدُوا۟ مَعَ ٱلْقَٰعِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ዘመቻ መውጣት ባሰቡ ኖሮ ለእርሱ ዝግጅትን ባሰናዱ ነበር:: ግን አላህ ለመውጣት እንቅስቃሴያቸውን ጠላውና አሰነፋቸው:: «ከተቀማጮቹ ጋር ተቀመጡ።» ተባሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَوْ خَرَجُوا۟ فِيكُم مَّا زَادُوكُمْ إِلَّا خَبَالًا وَلَأَوْضَعُوا۟ خِلَٰلَكُمْ يَبْغُونَكُمُ ٱلْفِتْنَةَ وَفِيكُمْ سَمَّٰعُونَ لَهُمْ وَٱللَّهُ عَلِيمٌۢ بِٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy47. (አማኞች ሆይ!) ከናንተ ጋር በወጡ ኖሮ ጥፋትን እንጂ አይጨምሩላችሁም ነበር:: ሁከትንም የሚፈልጉላችሁ ሲሆኑ በመካከላችሁ ነገርን በማሳበቅ ይቻኮሉ ነበር:: በእናንተ ውስጥ ለእነርሱ አዳማጮች አሏቸው:: አላህም በዳዮችን አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَقَدِ ٱبْتَغَوُا۟ ٱلْفِتْنَةَ مِن قَبْلُ وَقَلَّبُوا۟ لَكَ ٱلْأُمُورَ حَتَّىٰ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَظَهَرَ أَمْرُ ٱللَّهِ وَهُمْ كَٰرِهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ ጠይዎች ሲኾኑ እውነቱ እስከመጣና የአላህም ትዕዛዝ እስከተገለጸ ድረስ ከዚህ በፊት ሁከትን በእርግጥ ፈለጉ፡፡ ነገሮችንም ሁሉ አገላበጡልህ፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْهُم مَّن يَقُولُ ٱئْذَن لِّى وَلَا تَفْتِنِّىٓ أَلَا فِى ٱلْفِتْنَةِ سَقَطُوا۟ وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمُحِيطَةٌۢ بِٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy49. ከእነርሱም ውስጥ «ፍቀድልኝ አትሞክረኝ» የሚል ሰው አለ። (ሙስሊሞች) አስተውሉ! እነኝህ ሰዎች በመከራ ውስጥ ወደቁ:: ገሀነም ከሓዲያንን ከባቢ ናት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن تُصِبْكَ حَسَنَةٌ تَسُؤْهُمْ وَإِن تُصِبْكَ مُصِيبَةٌ يَقُولُوا۟ قَدْ أَخَذْنَآ أَمْرَنَا مِن قَبْلُ وَيَتَوَلَّوا۟ وَّهُمْ فَرِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልካም ነገር ቢያገኝህ ያስከፋቸዋል:: መከራ ቢያገኝህ ግን «ፊቱንም ይህን ፈርተን የግል ጥንቃቄያችንን ይዘናል።» ይላሉ። ተደሳቾች ሆነዉም ይሸሻሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُل لَّن يُصِيبَنَآ إِلَّا مَا كَتَبَ ٱللَّهُ لَنَا هُوَ مَوْلَىٰنَا وَعَلَى ٱللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ ٱلْمُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ለእኛ የጻፈልን እንጂ ሌላ አይነካንም:: እርሱ ረዳታችን ነው:: ምዕምናን በአላህ ላይ ብቻ ይመኩ።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ هَلْ تَرَبَّصُونَ بِنَآ إِلَّآ إِحْدَى ٱلْحُسْنَيَيْنِ وَنَحْنُ نَتَرَبَّصُ بِكُمْ أَن يُصِيبَكُمُ ٱللَّهُ بِعَذَابٍ مِّنْ عِندِهِۦٓ أَوْ بِأَيْدِينَا فَتَرَبَّصُوٓا۟ إِنَّا مَعَكُم مُّتَرَبِّصُونَ

Amharic Translation - Africa Academy52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእኛ ላይ ከሁለቱ መልካሞች አንደኛዋን እንጂ ሌላን ትጠባበቃላችሁን? እኛም አላህ ከእርሱ በሆነው ቅጣት ወይም በእጆቻችን የሚያጠፋችሁ መሆኑን በእናንተ ላይ እንጠባበቃለን:: ተጠባበቁ:: እኛም ከናንተው ጋር ተጠባባቂዎች ነንና።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ أَنفِقُوا۟ طَوْعًا أَوْ كَرْهًا لَّن يُتَقَبَّلَ مِنكُمْ إِنَّكُمْ كُنتُمْ قَوْمًا فَٰسِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ወዳችሁም ሆነ ጠልታችሁ ለግሱ ከናንተ ተቀባይ የላችሁም:: እናንተ አመጸኞች ህዝቦች ናችሁና።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا مَنَعَهُمْ أَن تُقْبَلَ مِنْهُمْ نَفَقَٰتُهُمْ إِلَّآ أَنَّهُمْ كَفَرُوا۟ بِٱللَّهِ وَبِرَسُولِهِۦ وَلَا يَأْتُونَ ٱلصَّلَوٰةَ إِلَّا وَهُمْ كُسَالَىٰ وَلَا يُنفِقُونَ إِلَّا وَهُمْ كَٰرِهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy54. ልግስናዎቻቸውን ከእነርሱ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ያደረገው በአላህና በመልዕክተኛው የካዱ፤ ሶላትንም ስልቹዎች ሆነው እንጂ የማይሰግዱ፤ እነርሱም ጠይዎች ሆነው እንጂ የማይሰጡ ከመሆናቸው በስተቀር ሌላ ነገር አልከለከላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَا تُعْجِبْكَ أَمْوَٰلُهُمْ وَلَآ أَوْلَٰدُهُمْ إِنَّمَا يُرِيدُ ٱللَّهُ لِيُعَذِّبَهُم بِهَا فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَتَزْهَقَ أَنفُسُهُمْ وَهُمْ كَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው አይድነቁህ:: አላህ የሚሻው በቅርቢቱ ህይወት በእነርሱ (በገንዘቦቻቸውና በልጆቻቸው) ሊቀጣቸው ነፍሶቻቸዉም ከሓዲያን ሆነው ሊሞቱ ብቻ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَحْلِفُونَ بِٱللَّهِ إِنَّهُمْ لَمِنكُمْ وَمَا هُم مِّنكُمْ وَلَٰكِنَّهُمْ قَوْمٌ يَفْرَقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy56. እነርሱም ከናንተ ጋር ለመሆናቸው በአላህ ይምላሉ:: እነርሱ ግን ከናንተ ጋር አይደሉም:: ይልቁንም እነርሱ አጋሪዎችን ያገኘው ነገር እንዳያገኛቸው የሚፈሩ ህዝቦች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَوْ يَجِدُونَ مَلْجَـًٔا أَوْ مَغَٰرَٰتٍ أَوْ مُدَّخَلًا لَّوَلَّوْا۟ إِلَيْهِ وَهُمْ يَجْمَحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy57. (ሙስሊሞች ሆይ!) መጠጊያ ወይም መሸሸጊያ ዋሻዎችን ወይም መግቢያ ቀዳዳዎችን ባገኙ ኖሮ በፍጥነት ወደ እርሱ በሸሹ ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْهُم مَّن يَلْمِزُكَ فِى ٱلصَّدَقَٰتِ فَإِنْ أُعْطُوا۟ مِنْهَا رَضُوا۟ وَإِن لَّمْ يُعْطَوْا۟ مِنْهَآ إِذَا هُمْ يَسْخَطُونَ

Amharic Translation - Africa Academy58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል በምጽዋቶች ክፍፍል ዙሪያ የሚዘልፉህ ሰዎች አሉ:: ከእርሷም የሚሹትን ያህል ቢሰጡ ይደሰታሉ:: ከእርሷ ምንም ካልተሰጣቸው ግን ይጠላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ أَنَّهُمْ رَضُوا۟ مَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَقَالُوا۟ حَسْبُنَا ٱللَّهُ سَيُؤْتِينَا ٱللَّهُ مِن فَضْلِهِۦ وَرَسُولُهُۥٓ إِنَّآ إِلَى ٱللَّهِ رَٰغِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy59. እነርሱም አላህና መልእክተኛው የሰጣቸውን በወደዱ፤ «አላህ በቂያችን ነው አላህ ከችሮታው በእርግጥ ይሰጠናል፣ መልክተኛውም (ይሰጠናል) እኛ ወደ አላህ ከጃዮች ነን።» ባሉ ኖሮ ለነርሱ በተሸላቸው ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا ٱلصَّدَقَٰتُ لِلْفُقَرَآءِ وَٱلْمَسَٰكِينِ وَٱلْعَٰمِلِينَ عَلَيْهَا وَٱلْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِى ٱلرِّقَابِ وَٱلْغَٰرِمِينَ وَفِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱبْنِ ٱلسَّبِيلِ فَرِيضَةً مِّنَ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy60. ግዴታ ዘካን የሚከፈሉት ለድሆች፤ ለችግረኞች፤ በእርሷም ላይ ለሚሰሩ ሠራተኞች፤ ልቦቻቸው በኢስላም ለሚለማመዱት ወገኖች፤ ጫንቃዎችን (ባሪያዎች) ነጻ ለማውጣት፤ ባለ እዳ ለሆኑት፤ በአላህ መንገድም ለሚሰሩና (ስንቅ ላለቀበት) መንገደኛ ብቻ ነው:: ይህ ስርአት ከአላህ የተደነገገ ግዴታ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْهُمُ ٱلَّذِينَ يُؤْذُونَ ٱلنَّبِىَّ وَيَقُولُونَ هُوَ أُذُنٌ قُلْ أُذُنُ خَيْرٍ لَّكُمْ يُؤْمِنُ بِٱللَّهِ وَيُؤْمِنُ لِلْمُؤْمِنِينَ وَرَحْمَةٌ لِّلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنكُمْ وَٱلَّذِينَ يُؤْذُونَ رَسُولَ ٱللَّهِ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) ከአስመሳዮች መካከል ነብዩ ሙሐመድን የሚያስቸግሩና «እርሱ እኮ ወሬ ሰሚ ነው።» የሚሉ አሉ። «ለእናንተ የበጎ ወሬ ሰሚ ነው:: በአላህ ያምናል:: አማኞችንም ያምናቸዋል:: ከናንተ መካከል ለእነዚያ በአላህ ላመኑት ሰዎችም እዝነት ነው።» በላቸው:: እነዚያ የአላህን መልዕክተኛ የሚያስቸግሩ ሰዎች ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَحْلِفُونَ بِٱللَّهِ لَكُمْ لِيُرْضُوكُمْ وَٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥٓ أَحَقُّ أَن يُرْضُوهُ إِن كَانُوا۟ مُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy62. አላህንና መልዕክተኛውን ሊያስወድዱ ሲገባቸው እናንተን ሊያስወድዷችሁ ዘንድ በአላህ ይምሉላችኋል። ትክክለኛ አማኞች ከሆኑ (ግን አላህንና መልዕክተኛው ሊያስወድዱ ይገባቸዋል)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ يَعْلَمُوٓا۟ أَنَّهُۥ مَن يُحَادِدِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَأَنَّ لَهُۥ نَارَ جَهَنَّمَ خَٰلِدًا فِيهَا ذَٰلِكَ ٱلْخِزْىُ ٱلْعَظِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy63. አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከር ሰው ሁሉ በውስጡ ዘውታሪ ሲሆን የተዘጋጀችለት የገሀነም እሳት መሆኑን አያውቁምን? ይህ ደግሞ ታላቅ ውርደት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَحْذَرُ ٱلْمُنَٰفِقُونَ أَن تُنَزَّلَ عَلَيْهِمْ سُورَةٌ تُنَبِّئُهُم بِمَا فِى قُلُوبِهِمْ قُلِ ٱسْتَهْزِءُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ مُخْرِجٌ مَّا تَحْذَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስመሳዮች በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ የሚነግራቸው ምዕራፍ በእነርሱ ላይ መወረዱን ዘወትር ይፈራሉ:: «ተሳለቁ:: አላህ የምትፈሩትን ነገር ሁሉ ገላጭ ነው።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَئِن سَأَلْتَهُمْ لَيَقُولُنَّ إِنَّمَا كُنَّا نَخُوضُ وَنَلْعَبُ قُلْ أَبِٱللَّهِ وَءَايَٰتِهِۦ وَرَسُولِهِۦ كُنتُمْ تَسْتَهْزِءُونَ

Amharic Translation - Africa Academy65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብትጠይቃቸው «እኛ የምንዘባርቅና የምንጫወት ሰዎች ብቻ ነበርን።» ይላሉ:: «በአላህ፤ በአናቅጹና በመልዕክተኛው ላይ ትቀልዱ ነበራችሁን?» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا تَعْتَذِرُوا۟ قَدْ كَفَرْتُم بَعْدَ إِيمَٰنِكُمْ إِن نَّعْفُ عَن طَآئِفَةٍ مِّنكُمْ نُعَذِّبْ طَآئِفَةًۢ بِأَنَّهُمْ كَانُوا۟ مُجْرِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy66. (አስመሳዮች ሆይ!) አታመካኙ ከእምነታችሁ በኋላ በእርግጥ ክዳችኋልና:: ከናንተ አንዷን ቡድን ብንምር የሌላዋን ቡድን አባላት ግን ኃጢአተኞች በመሆናቸው እንቀጣለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلْمُنَٰفِقُونَ وَٱلْمُنَٰفِقَٰتُ بَعْضُهُم مِّنۢ بَعْضٍ يَأْمُرُونَ بِٱلْمُنكَرِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ ٱلْمَعْرُوفِ وَيَقْبِضُونَ أَيْدِيَهُمْ نَسُوا۟ ٱللَّهَ فَنَسِيَهُمْ إِنَّ ٱلْمُنَٰفِقِينَ هُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy67. የወንድ አስመሳዮችና የሴት አስመሳዮች ከፊሎቻቸው ከከፊሉ ናቸው:: በመጥፎ ነገር ያዛሉ:: ከደግ ነገርም ይከለክላሉ:: እጆቻቸውን ከልግስና ይሰበስባሉ:: ለአላህ መታዘዝን ረሱ (ተዉ):: ስለዚህ እርሱም ተዋቸው:: አስመሳዮቹ አመጸኞች ማለት እነርሱው ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلْمُنَٰفِقِينَ وَٱلْمُنَٰفِقَٰتِ وَٱلْكُفَّارَ نَارَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَا هِىَ حَسْبُهُمْ وَلَعَنَهُمُ ٱللَّهُ وَلَهُمْ عَذَابٌ مُّقِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy68. የወንድ አስመሳዮችንና የሴት አስመሳዮችን እንዲሁም ከሓዲያንን የገሀነምን እሳት በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ አላህ ቃል ገብቶላቸዋል:: እርሷ በቂያቸው ናት:: አላህ ረግሟቸዋል:: ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ كَانُوٓا۟ أَشَدَّ مِنكُمْ قُوَّةً وَأَكْثَرَ أَمْوَٰلًا وَأَوْلَٰدًا فَٱسْتَمْتَعُوا۟ بِخَلَٰقِهِمْ فَٱسْتَمْتَعْتُم بِخَلَٰقِكُمْ كَمَا ٱسْتَمْتَعَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُم بِخَلَٰقِهِمْ وَخُضْتُمْ كَٱلَّذِى خَاضُوٓا۟ أُو۟لَٰٓئِكَ حَبِطَتْ أَعْمَٰلُهُمْ فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْخَٰسِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy69. (አስመሳዮች ሆይ!) ተግባራችሁ ልክ እንደእነዚያ ከናንተ በፊት እንደነበሩት ህዝቦች ነው:: ከናንተ ይበልጥ በሃይል የበረቱ በገንዘብና በልጆችም ከናንተ ይበልጥ የበዙ ነበሩ:: በእድላቸው ተጠቀሙ:: እነዚያም ከእናንተ በፊት የነበሩት በዕድላቸው እንደተጠቀሙ በዕድላችሁ ተጠቀማችሁ፡፡ እንደዘባረቁትም ዘባረቃችሁ:: እነዚያ ስራዎቻቸው በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ተበላሸ:: ከሳሪዎቹም ማለት እነርሱው ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ يَأْتِهِمْ نَبَأُ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ قَوْمِ نُوحٍ وَعَادٍ وَثَمُودَ وَقَوْمِ إِبْرَٰهِيمَ وَأَصْحَٰبِ مَدْيَنَ وَٱلْمُؤْتَفِكَٰتِ أَتَتْهُمْ رُسُلُهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيَظْلِمَهُمْ وَلَٰكِن كَانُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy70. የእነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት የኑህ፤ የዓድ፤ የሰሙድ፤ የኢብራሂም ህዝቦች፤ የመድየን ባለቤቶችና የተገልባጮቹም ከተሞች ታሪክ አልመጣላቸዉምን? መልዕክተኞቻቸው ግልጽ ተዓምራትን አመጡላቸው:: አላህ የሚበድላቸው አልነበረም:: ግን በራሳቸው ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْمُؤْمِنُونَ وَٱلْمُؤْمِنَٰتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَآءُ بَعْضٍ يَأْمُرُونَ بِٱلْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ ٱلْمُنكَرِ وَيُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤْتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَيُطِيعُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓ أُو۟لَٰٓئِكَ سَيَرْحَمُهُمُ ٱللَّهُ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy71. ወንድ አማኞችና ሴት አማኞች ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው:: በደግ ነገር ያዝዛሉ:: ከክፉም ነገር ይከለክላሉ:: ሶላትን ይሰግዳሉ:: ዘካን ይሰጣሉ:: አላህንና መልዕክተኛውን ይታዘዛሉ:: እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمُؤْمِنَٰتِ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَمَسَٰكِنَ طَيِّبَةً فِى جَنَّٰتِ عَدْنٍ وَرِضْوَٰنٌ مِّنَ ٱللَّهِ أَكْبَرُ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy72. አላህ የወንድ ትክክለኛ አማኞችንና የሴት ትክክለኛ አማኞችን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በመኖሪያ ገነቶችም ውስጥ መልካም መኖሪያ ቤቶችን ቃል ገብቶላቸዋል:: ከአላህ የሆነው ውዴታ ደግሞ ከሁሉ የበለጠ ነው:: ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ جَٰهِدِ ٱلْكُفَّارَ وَٱلْمُنَٰفِقِينَ وَٱغْلُظْ عَلَيْهِمْ وَمَأْوَىٰهُمْ جَهَنَّمُ وَبِئْسَ ٱلْمَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy73. አንተ ነብዩ ሆይ! ከሓዲያንንና አስመሳዮችን ታገል:: በእነርሱ ላይም ጨክን:: መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት:: መመለሻይቱም በጣም ከፋች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَحْلِفُونَ بِٱللَّهِ مَا قَالُوا۟ وَلَقَدْ قَالُوا۟ كَلِمَةَ ٱلْكُفْرِ وَكَفَرُوا۟ بَعْدَ إِسْلَٰمِهِمْ وَهَمُّوا۟ بِمَا لَمْ يَنَالُوا۟ وَمَا نَقَمُوٓا۟ إِلَّآ أَنْ أَغْنَىٰهُمُ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ مِن فَضْلِهِۦ فَإِن يَتُوبُوا۟ يَكُ خَيْرًا لَّهُمْ وَإِن يَتَوَلَّوْا۟ يُعَذِّبْهُمُ ٱللَّهُ عَذَابًا أَلِيمًا فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَمَا لَهُمْ فِى ٱلْأَرْضِ مِن وَلِىٍّ وَلَا نَصِيرٍ

Amharic Translation - Africa Academy74. ምንም ያላሉ ለመሆናቸው በአላህ ይምላሉ:: ግን የክህደትን ቃል በእርግጥ አሉ:: ከእስልምናቸዉም በኋላ ካዱ:: ያላገኙትንም ነገር አሰቡ:: አላህና መልዕክተኛው ከችሮታው ያከበራቸው መሆኑን እንጂ ሌላን አልጠሉም:: ቢጸጸቱም ለእነርሱ የተሻለ ይሆናል:: ቢሸሹም አላህ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም አሳማሚን ቅጣት ይቀጣቸዋል:: ለእነርሱም በምድር ውስጥ ምንም ወዳጅና ረዳት የላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْهُم مَّنْ عَٰهَدَ ٱللَّهَ لَئِنْ ءَاتَىٰنَا مِن فَضْلِهِۦ لَنَصَّدَّقَنَّ وَلَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy75. ከእነርሱም መካከል አላህን «ከችሮታው ቢሰጠን በእርግጥ እንመጸውታለን::በእርግጥ ከመልካሞችም እንሆናለን።» ሲል ቃል የገባ አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّآ ءَاتَىٰهُم مِّن فَضْلِهِۦ بَخِلُوا۟ بِهِۦ وَتَوَلَّوا۟ وَّهُم مُّعْرِضُونَ

Amharic Translation - Africa Academy76. ከዚያም ከችሮታዉም በሰጣቸው ጊዜ ሰሰቱ:: እነርሱ ቃል ኪዳናቸውን የተው ሆነዉም ዞሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَعْقَبَهُمْ نِفَاقًا فِى قُلُوبِهِمْ إِلَىٰ يَوْمِ يَلْقَوْنَهُۥ بِمَآ أَخْلَفُوا۟ ٱللَّهَ مَا وَعَدُوهُ وَبِمَا كَانُوا۟ يَكْذِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy77. ለአላህ ቃል የገቡትን በማፍረሳቸውና ይዋሹትም በነበሩት ውሸት ምክንያት እስከሚገናኙት ቀን ድረስ ንፍቅናን በልቦቻቻው አስከተላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ يَعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَىٰهُمْ وَأَنَّ ٱللَّهَ عَلَّٰمُ ٱلْغُيُوبِ

Amharic Translation - Africa Academy78. (አስመሳዮችን) አላህ ምስጢራቸውንና ውይይታቸውን የሚያውቅ መሆኑንና አላህም ሩቅ ነገሮችን ሁሉ በጣም አዋቂ መሆኑን አያውቁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يَلْمِزُونَ ٱلْمُطَّوِّعِينَ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ فِى ٱلصَّدَقَٰتِ وَٱلَّذِينَ لَا يَجِدُونَ إِلَّا جُهْدَهُمْ فَيَسْخَرُونَ مِنْهُمْ سَخِرَ ٱللَّهُ مِنْهُمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy79. እነዚያ ከምዕምናን በምጽዋቶች ፈቃደኛ የሆኑትን የችሎታቸውን ያክል እንጂ የማያገኙትን ሰዎች የሚያነውሩና በእነርሱ የሚሳለቁ ሰዎች ሁሉ አላህ ከእነርሱ ይሳለቅባቸዋል:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱسْتَغْفِرْ لَهُمْ أَوْ لَا تَسْتَغْفِرْ لَهُمْ إِن تَسْتَغْفِرْ لَهُمْ سَبْعِينَ مَرَّةً فَلَن يَغْفِرَ ٱللَّهُ لَهُمْ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَفَرُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْفَٰسِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱ ምሕረትን ብትለምንላቸዉም ወይም ባትለምንላቸው ሁሉም እኩል ነው:: ለእነርሱ ሰባ ጊዜ ምህረትን ብትለምንላቸው እንኳን አላህ በፍጹም አይምራቸዉምና:: ምክንያቱም እነርሱ በአላህና በመልዕክተኛው ክደዋልና:: አላህ አመጸኞች ህዝቦችን አያቀናም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَرِحَ ٱلْمُخَلَّفُونَ بِمَقْعَدِهِمْ خِلَٰفَ رَسُولِ ٱللَّهِ وَكَرِهُوٓا۟ أَن يُجَٰهِدُوا۟ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَقَالُوا۟ لَا تَنفِرُوا۟ فِى ٱلْحَرِّ قُلْ نَارُ جَهَنَّمَ أَشَدُّ حَرًّا لَّوْ كَانُوا۟ يَفْقَهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy81. እነዚያ ከዘመቻ የቀሩት ሰዎች ከአላህ መልዕክተኛ በኋላ ተገንጥለው በመቀመጣቸው ተደሰቱ:: በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው መታገልን ጠሉ:: ለሌሎችም «በሐሩር አትሂዱ» አሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የገሀነም እሳት ትኩሳት በጣም ከዚህ የበረታ ነው።» በላቸው:: እናም የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ ከዘመቻው አይቀሩም ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلْيَضْحَكُوا۟ قَلِيلًا وَلْيَبْكُوا۟ كَثِيرًا جَزَآءًۢ بِمَا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy82. አስመሳዮች ጥቂት ጊዜን ብቻ ይሳቁ:: ይሠሩት በነበሩት እኩይ ተግባር ምክንያት ዋጋ ብዙ ጊዜ ያለቅሳሉና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِن رَّجَعَكَ ٱللَّهُ إِلَىٰ طَآئِفَةٍ مِّنْهُمْ فَٱسْتَـْٔذَنُوكَ لِلْخُرُوجِ فَقُل لَّن تَخْرُجُوا۟ مَعِىَ أَبَدًا وَلَن تُقَٰتِلُوا۟ مَعِىَ عَدُوًّا إِنَّكُمْ رَضِيتُم بِٱلْقُعُودِ أَوَّلَ مَرَّةٍ فَٱقْعُدُوا۟ مَعَ ٱلْخَٰلِفِينَ

Amharic Translation - Africa Academy83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል ወደ ሆነችው ቡድን አላህ በሰላም ቢመልስህና ካንተ ጋር ዘመቻ ለመውጣት ቢያስፈቅዱህ «ከእኔ ጋር በፍጹም አትወጡም:: ከእኔም ጋር ጠላትን አትዋጉም:: እናንተ በመጀመሪያ ጊዜ መቀመጥን ወዳችኋልና:: ይልቁንም ከተቀማጮች ጋር ተቀመጡ።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تُصَلِّ عَلَىٰٓ أَحَدٍ مِّنْهُم مَّاتَ أَبَدًا وَلَا تَقُمْ عَلَىٰ قَبْرِهِۦٓ إِنَّهُمْ كَفَرُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَمَاتُوا۟ وَهُمْ فَٰسِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል በሞተ በአንዱም ሰው ላይ ቢሆን ፈጽሞ አትስገድ:: በመቃብሩም ላይ አትቁም:: እነርሱ በአላህና በመልዕክተኛው ክደዋል:: እነርሱ አመጸኞችም ሆነው ሞተዋልና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تُعْجِبْكَ أَمْوَٰلُهُمْ وَأَوْلَٰدُهُمْ إِنَّمَا يُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُعَذِّبَهُم بِهَا فِى ٱلدُّنْيَا وَتَزْهَقَ أَنفُسُهُمْ وَهُمْ كَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው አይድነቁህ:: አላህ የሚፈልገው በቅርቢቱ ዓለም በገንዘቦቻቸውና በልጆቻቸው ሊቀጣቸውና ከሓዲያንም ሆነው ነፍሶቻቸው እንዲወጡ ሊያደርግ ብቻ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَآ أُنزِلَتْ سُورَةٌ أَنْ ءَامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَجَٰهِدُوا۟ مَعَ رَسُولِهِ ٱسْتَـْٔذَنَكَ أُو۟لُوا۟ ٱلطَّوْلِ مِنْهُمْ وَقَالُوا۟ ذَرْنَا نَكُن مَّعَ ٱلْقَٰعِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ እመኑ:: ከመልዕክተኛው ጋር ሆናችሁ ታገሉ በማለት የቁርኣን ምዕራፍ በተወረደ ጊዜ ከእነርሱ የሰፊ ሀብት ባለቤቶች የሆኑት ሰዎች ለመቅረት ፈቃድ ይጠይቁሃል:: «ከተቀማጮቹ ጋር እንሁን ተወን» ይሉሃል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَضُوا۟ بِأَن يَكُونُوا۟ مَعَ ٱلْخَوَالِفِ وَطُبِعَ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَفْقَهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy87. በቤት ከሚቀሩት ወገኖች ጋር መሆናቸውን ወደዱ:: በልቦቻቸዉም ላይ (ዝገት) ታተመባቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَٰكِنِ ٱلرَّسُولُ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ جَٰهَدُوا۟ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ وَأُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلْخَيْرَٰتُ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُفْلِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy88. ግን መልዕክተኛውና ከእርሱ ጋር ያመኑት ሰዎች በገንዘቦቻቸዉም በነፍሶቻቸዉም ታገሉ:: እነዚያም መልካሞች ሁሉ ለእነርሱ ብቻ የተዘጋጁ ናቸው:: እነዚያም እነርሱ ምኞታቸውን ያገኙ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَعَدَّ ٱللَّهُ لَهُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا ذَٰلِكَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy89. አላህ ለእነርሱ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችን በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ አዘጋጅቶላቸዋል:: ይህ ታላቅ ማግኜት (እድል) ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَآءَ ٱلْمُعَذِّرُونَ مِنَ ٱلْأَعْرَابِ لِيُؤْذَنَ لَهُمْ وَقَعَدَ ٱلَّذِينَ كَذَبُوا۟ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ سَيُصِيبُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy90. ከአረብ ዘላኖች መካከል ይቅርታ ፈላጊዎቹ እንዲፈቀድላቸው መጡ:: እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን ያስተባበሉት ግን ተቀመጡ:: እነዚያን በአላህ የካዱት ሰዎች አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል (ያገኛቸዋል)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّيْسَ عَلَى ٱلضُّعَفَآءِ وَلَا عَلَى ٱلْمَرْضَىٰ وَلَا عَلَى ٱلَّذِينَ لَا يَجِدُونَ مَا يُنفِقُونَ حَرَجٌ إِذَا نَصَحُوا۟ لِلَّهِ وَرَسُولِهِۦ مَا عَلَى ٱلْمُحْسِنِينَ مِن سَبِيلٍ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy91. በደካሞች ላይ፤ በበሽተኞች ላይ፤ በእነዚያም ለስንቅና ለትጥቅ የሚያወጡት ገንዘብ በማያገኙት ላይ ለአላህና ለመልዕክተኛው ፍጹም ታዛዦች ከሆኑ ወደ ዘመቻ ባይወጡም ኃጢአት የለባቸዉም:: በበጎ አድራጊዎች ላይ ምንም የመወቀሻ መንገድ የለባቸዉም:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا عَلَى ٱلَّذِينَ إِذَا مَآ أَتَوْكَ لِتَحْمِلَهُمْ قُلْتَ لَآ أَجِدُ مَآ أَحْمِلُكُمْ عَلَيْهِ تَوَلَّوا۟ وَّأَعْيُنُهُمْ تَفِيضُ مِنَ ٱلدَّمْعِ حَزَنًا أَلَّا يَجِدُوا۟ مَا يُنفِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy92. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በነዚያም መጓጓዣያ እንድትሰጣቸው ፈልገው ወደ አንተ በመጡ ጊዜ «እናንተን የምጭንበት (አጋሰስ) አላገኝም።» ያልካቸው ስትሆን የሚያወጡት ገንዘብ ባለማግኘታቸው ለማዘናቸው ዓይኖቻቸው እንባን እያፈሰሱ በዞሩት ላይ ምንም ወቀሳ የለባቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا ٱلسَّبِيلُ عَلَى ٱلَّذِينَ يَسْتَـْٔذِنُونَكَ وَهُمْ أَغْنِيَآءُ رَضُوا۟ بِأَن يَكُونُوا۟ مَعَ ٱلْخَوَالِفِ وَطَبَعَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሚወቀሱት እነዚያ ባለጸጋዎች ሆነው ሳሉ ለመቅረት ፈቃድ በሚጠይቁህ ሰዎች ላይ ብቻ ናቸው:: ከቀሪዎቹ ጋር መሆናቸውን ወደዱ:: አላህ በልቦቻቸው ላይ አተመባቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَعْتَذِرُونَ إِلَيْكُمْ إِذَا رَجَعْتُمْ إِلَيْهِمْ قُل لَّا تَعْتَذِرُوا۟ لَن نُّؤْمِنَ لَكُمْ قَدْ نَبَّأَنَا ٱللَّهُ مِنْ أَخْبَارِكُمْ وَسَيَرَى ٱللَّهُ عَمَلَكُمْ وَرَسُولُهُۥ ثُمَّ تُرَدُّونَ إِلَىٰ عَٰلِمِ ٱلْغَيْبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነርሱ በተመለሳችሁ ጊዜ ምክንያቶቻቸውን ያቀርቡላችኋል:: «አታመካኙ እናንተን ፈጽሞ አናምንም:: አላህ ከወሬዎቻችሁ አስቀድሞ ነግሮናልና:: አላህና መልዕክተኛው ሥራችሁን ያያሉ:: ከዚያ ሩቅንና ቅርብን ሁሉ አዋቂ ወደ ሆነው አላህ ትመለሳላችሁ:: ወዲያዉም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَيَحْلِفُونَ بِٱللَّهِ لَكُمْ إِذَا ٱنقَلَبْتُمْ إِلَيْهِمْ لِتُعْرِضُوا۟ عَنْهُمْ فَأَعْرِضُوا۟ عَنْهُمْ إِنَّهُمْ رِجْسٌ وَمَأْوَىٰهُمْ جَهَنَّمُ جَزَآءًۢ بِمَا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy95. (አማኞች ሆይ!) ከዘመቻ ወደ እነርሱ በተመለሳችሁ ጊዜ ጥፋታቸውን ይቅር እንድትሉሏቸው ለእናንተ በአላህ ይምላሉ:: እነርሱን ተዏቸው:: እነርሱ እርኩሶች ናቸውና:: ይሠሩትም በነበረው ኃጢአት መኖሪያቸው ገሀነም ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَحْلِفُونَ لَكُمْ لِتَرْضَوْا۟ عَنْهُمْ فَإِن تَرْضَوْا۟ عَنْهُمْ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يَرْضَىٰ عَنِ ٱلْقَوْمِ ٱلْفَٰسِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy96. እነርሱ ትወዱላቸው ዘንድ ለእናንተ ይምሉላችኋል:: እናንተ ብትወዱላቸውም አላህ ከአመጸኛ ህዝቦች አይወድም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلْأَعْرَابُ أَشَدُّ كُفْرًا وَنِفَاقًا وَأَجْدَرُ أَلَّا يَعْلَمُوا۟ حُدُودَ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy97. ዘላን አረቦች በክሕደትና በንፍቅና በጣም የበረቱ፤ አላህ በመልዕክተኛው ላይ ያወረደውን ህግጋት ባለማወቅም የተገቡ ናቸው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنَ ٱلْأَعْرَابِ مَن يَتَّخِذُ مَا يُنفِقُ مَغْرَمًا وَيَتَرَبَّصُ بِكُمُ ٱلدَّوَآئِرَ عَلَيْهِمْ دَآئِرَةُ ٱلسَّوْءِ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy98. ከዘለኖች መካከል በአላህ መንገድ የሚያወጣውን ገንዘብ እዳ አድርጎ የሚይዝና በእናንተ ላይ የጊዜን መገለባበጥ የሚጠባበቅ ሰው አለ:: በእነርሱ ላይ ጥፋቱ ይዙርባቸው:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنَ ٱلْأَعْرَابِ مَن يُؤْمِنُ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَيَتَّخِذُ مَا يُنفِقُ قُرُبَٰتٍ عِندَ ٱللَّهِ وَصَلَوَٰتِ ٱلرَّسُولِ أَلَآ إِنَّهَا قُرْبَةٌ لَّهُمْ سَيُدْخِلُهُمُ ٱللَّهُ فِى رَحْمَتِهِۦٓ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy99. ከአረብ ዘላኖች መካከል በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሚሰጣቸውንም ምጽዋቶች አላህ ዘንድ መቃረቢያዎችና ወደ መልዕክተኛው ጸሎቶች መዳረሻ አድርጎ የሚይዝ ክፍል አለ:: አስተዉሉ! እርሷ ለእነርሱ በእርግጥ አቃራቢ ናት:: አላህ በችሮታው ውስጥ በገነቱ በእርግጥ ያስገባቸዋል:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلسَّٰبِقُونَ ٱلْأَوَّلُونَ مِنَ ٱلْمُهَٰجِرِينَ وَٱلْأَنصَارِ وَٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُم بِإِحْسَٰنٍ رَّضِىَ ٱللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا۟ عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى تَحْتَهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا ذَٰلِكَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy100. ከስደተኞቹም ሆነ ከረዳቶቹ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎችና እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው ሰዎች አላህ የእነርሱን ተግባር ወዶላቸዋል:: እነርሱም ወደውለታል:: በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸዉም ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲሆኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል:: ይህ ታላቅ እድለኛነት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِمَّنْ حَوْلَكُم مِّنَ ٱلْأَعْرَابِ مُنَٰفِقُونَ وَمِنْ أَهْلِ ٱلْمَدِينَةِ مَرَدُوا۟ عَلَى ٱلنِّفَاقِ لَا تَعْلَمُهُمْ نَحْنُ نَعْلَمُهُمْ سَنُعَذِّبُهُم مَّرَّتَيْنِ ثُمَّ يُرَدُّونَ إِلَىٰ عَذَابٍ عَظِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy101. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዙሪያችሁም ካሉት የዐረብ ዘላኖች አስመሳዮች አሉ:: ከመዲና ሰዎችም በንፍቅና ላይ በማመጽ የዘወተሩ አሉ:: አታውቃቸዉም:: እኛ እናውቃቸዋለን:: ሁለት ጊዜ እንቀጣቸዋለን:: ከዚያ ወደ ታላቅ ቅጣት ይመለሳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَءَاخَرُونَ ٱعْتَرَفُوا۟ بِذُنُوبِهِمْ خَلَطُوا۟ عَمَلًا صَٰلِحًا وَءَاخَرَ سَيِّئًا عَسَى ٱللَّهُ أَن يَتُوبَ عَلَيْهِمْ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy102. ሌሎችም ኃጢአቶቻቸውን የተናዘዙ መልካም ሥራንና ሌላን መጥፎ ሥራ የቀላቀሉ አሉ:: አላህ ጸጸታቸውን ሊቀበል ይከጀላል:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خُذْ مِنْ أَمْوَٰلِهِمْ صَدَقَةً تُطَهِّرُهُمْ وَتُزَكِّيهِم بِهَا وَصَلِّ عَلَيْهِمْ إِنَّ صَلَوٰتَكَ سَكَنٌ لَّهُمْ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy103. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከገንዘቦቻቸው የምታጠራቸውና የምታፋፋቸውን ምጽዋት ያዝ:: ለነሱም ዱኣ አድርግላቸው፡፡ ዱኣእህ ለእነሱ እርጋታ ነውና አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ يَعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ هُوَ يَقْبَلُ ٱلتَّوْبَةَ عَنْ عِبَادِهِۦ وَيَأْخُذُ ٱلصَّدَقَٰتِ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy104. አላህም እርሱ ከባሮቹ ንሰሃን የሚቀበልና ምጽዋቶችንም የሚወስድ፤ አላህ ብቸኛ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ መሆኑን አያውቁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقُلِ ٱعْمَلُوا۟ فَسَيَرَى ٱللَّهُ عَمَلَكُمْ وَرَسُولُهُۥ وَٱلْمُؤْمِنُونَ وَسَتُرَدُّونَ إِلَىٰ عَٰلِمِ ٱلْغَيْبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy105. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሥሩ:: አላህ መልዕክተኛውና አማኞችም ሥራችሁን በእርግጥ ያያሉና:: ሩቁንና ቅርቡን ሁሉ አዋቂ ወደ ሆነው አላህ በእርግጥ ትመለሳላችሁ:: ትሰሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَءَاخَرُونَ مُرْجَوْنَ لِأَمْرِ ٱللَّهِ إِمَّا يُعَذِّبُهُمْ وَإِمَّا يَتُوبُ عَلَيْهِمْ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy106. ሌሎችም የአላህን ውሳኔ ትዕዛዝ እንዲጠብቁ የተቆዩ ህዝቦች አሉ:: ይቀጣቸዋል ወይም ጸጸታቸውን ይቀበላቸዋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነዉና፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ مَسْجِدًا ضِرَارًا وَكُفْرًا وَتَفْرِيقًۢا بَيْنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ وَإِرْصَادًا لِّمَنْ حَارَبَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ مِن قَبْلُ وَلَيَحْلِفُنَّ إِنْ أَرَدْنَآ إِلَّا ٱلْحُسْنَىٰ وَٱللَّهُ يَشْهَدُ إِنَّهُمْ لَكَٰذِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy107. እነዚያም አማኞችን ለመጉዳት ክህደትንም ለማበረታታት በአማኞችም መካከል ለመለያየት ከአሁን በፊት አላህንና መልዕክተኛውን የተዋጋውን ሰው ለመጠባበቅ መስጊዱን የሠሩት ሰዎች ከእነርሱ ናቸው:: «መልካምን እንጂ ሌላ አልሻንም።» ሲሉ በእርግጥ ይምላሉ:: አላህ ደግሞ ውሸታሞች መሆናቸውን በእርግጥ ይመሰክራል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا تَقُمْ فِيهِ أَبَدًا لَّمَسْجِدٌ أُسِّسَ عَلَى ٱلتَّقْوَىٰ مِنْ أَوَّلِ يَوْمٍ أَحَقُّ أَن تَقُومَ فِيهِ فِيهِ رِجَالٌ يُحِبُّونَ أَن يَتَطَهَّرُوا۟ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلْمُطَّهِّرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእርሱ ውስጥ በፍጹም አትስገድ:: ይልቁንም ከመጀመሪያ ቀን ይዞ በአላህ ፍራቻ ላይ የተመሠረተው (የቁባ ) መስጊድ በውስጡ ልትሰግዱበት የተገባው ነው:: በውስጡ መጥራራትን የሚወዱ ወንዶች አሉ:: አላህ ተጥራሪዎችን ይወዳል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَمَنْ أَسَّسَ بُنْيَٰنَهُۥ عَلَىٰ تَقْوَىٰ مِنَ ٱللَّهِ وَرِضْوَٰنٍ خَيْرٌ أَم مَّنْ أَسَّسَ بُنْيَٰنَهُۥ عَلَىٰ شَفَا جُرُفٍ هَارٍ فَٱنْهَارَ بِهِۦ فِى نَارِ جَهَنَّمَ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy109. አላህን በመፍራትና ውዴታውን በመፈለግ ላይ ግንቡን የመሠረተ ሰው ወይስ ጎርፍ በሸረሸረው ለመናድ በተቃረበ ገደል አፋፍ ላይ ግንቡን የመሠረተውና እርሱንም ይዞት ወደ ገሀነም እሳት ውስጥ የወደቀው ይበልጣልን? አላህ በደለኛ ሕዝቦችን አይመራም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يَزَالُ بُنْيَٰنُهُمُ ٱلَّذِى بَنَوْا۟ رِيبَةً فِى قُلُوبِهِمْ إِلَّآ أَن تَقَطَّعَ قُلُوبُهُمْ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy110. ያ የካቡት ግንባቸው ልቦቻቸው በሞት ካልተቆራረጡ በስተቀር በልቦቻቸው ውስጥ የመጠራጠር ምክንያት ከመሆን አይወገድም:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ ٱشْتَرَىٰ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ أَنفُسَهُمْ وَأَمْوَٰلَهُم بِأَنَّ لَهُمُ ٱلْجَنَّةَ يُقَٰتِلُونَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ فَيَقْتُلُونَ وَيُقْتَلُونَ وَعْدًا عَلَيْهِ حَقًّا فِى ٱلتَّوْرَىٰةِ وَٱلْإِنجِيلِ وَٱلْقُرْءَانِ وَمَنْ أَوْفَىٰ بِعَهْدِهِۦ مِنَ ٱللَّهِ فَٱسْتَبْشِرُوا۟ بِبَيْعِكُمُ ٱلَّذِى بَايَعْتُم بِهِۦ وَذَٰلِكَ هُوَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy111. አላህ ከትክክለኛ አማኞች ነፍሶቻቸውንና ገንዘቦቻቸውን ገነትን ለእነርሱ በማድረግ ገዛቸው:: በአላህ መንገድ ላይ ይጋደላሉ:: ይገድላሉም:: ይገደላሉም:: በተውራት፤ በኢንጂልና በቁርኣንም የተነገረውን ተስፋ በእርሱ ላይ አረጋገጠ:: ከአላህ የበለጠ በቃል ኪዳኑ የሚሞላ ማን ነው? (ትክክለኛ አማኞች ሆይ!) በዚያም በእርሱ በተሻሻጣችሁበት ሽያጫችሁ ተደሰቱ:: ይህ ታላቅ ዕድል ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلتَّٰٓئِبُونَ ٱلْعَٰبِدُونَ ٱلْحَٰمِدُونَ ٱلسَّٰٓئِحُونَ ٱلرَّٰكِعُونَ ٱلسَّٰجِدُونَ ٱلْـَٔامِرُونَ بِٱلْمَعْرُوفِ وَٱلنَّاهُونَ عَنِ ٱلْمُنكَرِ وَٱلْحَٰفِظُونَ لِحُدُودِ ٱللَّهِ وَبَشِّرِ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy112. እነርሱ ተጸፃቾች፤ ተገዢዎች፤ አመስጋኞች፤ ፆመኞች፤ (በሶላት) አጎንባሾች፤ በግንባር ተደፊዎች፤ በበጎ ሥራ አዛዦች፤ ከክፉ ከልካዮች እና የአላህንም ሕግጋት ጠባቂዎች ናቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትክክለኛ አማኞችንም አብስር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا كَانَ لِلنَّبِىِّ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَن يَسْتَغْفِرُوا۟ لِلْمُشْرِكِينَ وَلَوْ كَانُوٓا۟ أُو۟لِى قُرْبَىٰ مِنۢ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُمْ أَصْحَٰبُ ٱلْجَحِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy113. መልዕክተኛዉም ሆነ እነዚያ በእሱ ያመኑት ሰዎች ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢሆኑም እንኳ ከሓዲያን እነርሱ የእሳት ጓዶች መሆናቸው ከተገለጸላቸው በኋላ የአላህን ምሕረት ሊለምኑላቸው የሚገባ አልነበረም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا كَانَ ٱسْتِغْفَارُ إِبْرَٰهِيمَ لِأَبِيهِ إِلَّا عَن مَّوْعِدَةٍ وَعَدَهَآ إِيَّاهُ فَلَمَّا تَبَيَّنَ لَهُۥٓ أَنَّهُۥ عَدُوٌّ لِّلَّهِ تَبَرَّأَ مِنْهُ إِنَّ إِبْرَٰهِيمَ لَأَوَّٰهٌ حَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy114. ኢብራሂምም ለአባቱ ምህረትን መለመኑ ቀድሞ ገብቶለት የነበረውን ቃል ለመሙላት እንጂ ለሌላ አልነበረም:: እናም የአላህ ጠላት መሆኑ በተገለጸለት ጊዜ ከእርሱ ራቀ:: (ተወው):: ኢብራሂም በእርግጥ አልቃሻ እና ታጋሽ ነበርና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُضِلَّ قَوْمًۢا بَعْدَ إِذْ هَدَىٰهُمْ حَتَّىٰ يُبَيِّنَ لَهُم مَّا يَتَّقُونَ إِنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy115. አላህ ህዝቦችን ካቀናቸው በኋላ የሚጠነቀቁትን ነገር እሥከሚገልጽላቸው ድረስ ሳያውቁ በሰሩት ጥፋት ጥፋተኛ የሚያደርግ ጌታ አይደለም:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ لَهُۥ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ يُحْىِۦ وَيُمِيتُ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِىٍّ وَلَا نَصِيرٍ

Amharic Translation - Africa Academy116. አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ ነው:: ህያው ያደርጋል:: ይገድላልም:: ለእናንተም ከእርሱ በስተቀር ጠባቂም ሆነ ወዳጅ የላችሁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّقَد تَّابَ ٱللَّهُ عَلَى ٱلنَّبِىِّ وَٱلْمُهَٰجِرِينَ وَٱلْأَنصَارِ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُ فِى سَاعَةِ ٱلْعُسْرَةِ مِنۢ بَعْدِ مَا كَادَ يَزِيغُ قُلُوبُ فَرِيقٍ مِّنْهُمْ ثُمَّ تَابَ عَلَيْهِمْ إِنَّهُۥ بِهِمْ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy117. በመልዕክተኛው በስደተኞችና በረዳቶች በእነዚህም በችግሩ ጊዜ (በተቡክ ዘመቻ) ከእነርሱ የከፊሎቹ ልቦች ለመቅረት ሊዘነበሉ ከተቃረቡ በኋላ በተከተሉት ላይ አላህ በእርግጥ ጸጸታቸውን ተቀበለ:: ከዚያ ከእነርሱ ንሰሃ መግባታቸውን ተቀበለ:: እርሱ(አላህ ) ለእነርሱ ሩህሩህና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعَلَى ٱلثَّلَٰثَةِ ٱلَّذِينَ خُلِّفُوا۟ حَتَّىٰٓ إِذَا ضَاقَتْ عَلَيْهِمُ ٱلْأَرْضُ بِمَا رَحُبَتْ وَضَاقَتْ عَلَيْهِمْ أَنفُسُهُمْ وَظَنُّوٓا۟ أَن لَّا مَلْجَأَ مِنَ ٱللَّهِ إِلَّآ إِلَيْهِ ثُمَّ تَابَ عَلَيْهِمْ لِيَتُوبُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy118. በእነዚያም ወደ ኋላ በቀሩት በሶስቱ ሰዎች ላይ ምድር ከስፋቷ ጋር በእነርሱ ላይ እስከምትጠብባቸው፤ ነፍሶቻቸዉም በእነርሱ ላይ እስከምትጠብባቸው፤ ከአላህም ወደ እርሱ ብቻ እንጂ ሌላ መጠጊያ አለመኖሩን እስከሚያረጋግጡ ድረስ በተቆዩት ላይ አላህ ጸጸትን ተቀበለ:: ከዚያም ይጸጸቱ ዘንድ ወደ ጸጸት መራቸው:: አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَكُونُوا۟ مَعَ ٱلصَّٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy119. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን በትክክል ፍሩ:: ከእውነተኞቹም ጋር ሁኑ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا كَانَ لِأَهْلِ ٱلْمَدِينَةِ وَمَنْ حَوْلَهُم مِّنَ ٱلْأَعْرَابِ أَن يَتَخَلَّفُوا۟ عَن رَّسُولِ ٱللَّهِ وَلَا يَرْغَبُوا۟ بِأَنفُسِهِمْ عَن نَّفْسِهِۦ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ لَا يُصِيبُهُمْ ظَمَأٌ وَلَا نَصَبٌ وَلَا مَخْمَصَةٌ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَا يَطَـُٔونَ مَوْطِئًا يَغِيظُ ٱلْكُفَّارَ وَلَا يَنَالُونَ مِنْ عَدُوٍّ نَّيْلًا إِلَّا كُتِبَ لَهُم بِهِۦ عَمَلٌ صَٰلِحٌ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجْرَ ٱلْمُحْسِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy120. የመዲና ሰዎችና በዙሪያቸው ያሉት የዘላን ዓረብ ህዝቦች ከአላህ መልዕክተኛ ጥሪ ወደ ኋላ ሊቀሩና ነፍሶቻቸውንም ከነፍሱ አብልጠው ሊወዱ አይገባቸዉም ነበር:: ይህም የሆነው ለእነርሱ መልካም ሥራ የሚጻፍላቸው ቢሆን እንጂ በአላህ መንገድ ላይ ጥምም ድካምም ርሀብም የማይነካቸው ከሓዲያንንም የሚያስቆጭን ስፍራ የማይረግጡ ከጠላትም የሚጎዳን ነገር (መግደል) የማያገኙ በመሆናቸው ነው:: አላህ የመልካም ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا يُنفِقُونَ نَفَقَةً صَغِيرَةً وَلَا كَبِيرَةً وَلَا يَقْطَعُونَ وَادِيًا إِلَّا كُتِبَ لَهُمْ لِيَجْزِيَهُمُ ٱللَّهُ أَحْسَنَ مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy121. ትንሽንም ትልቅንም ልግስና አይለግሱም ወንዝንም አያቋርጡም አላህ ይሠሩት ከነበረው የበለጠን ምንዳ ይመነዳቸው ዘንድ ለእነርሱ የሚጽፍላቸው ቢሆን እንጂ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا كَانَ ٱلْمُؤْمِنُونَ لِيَنفِرُوا۟ كَآفَّةً فَلَوْلَا نَفَرَ مِن كُلِّ فِرْقَةٍ مِّنْهُمْ طَآئِفَةٌ لِّيَتَفَقَّهُوا۟ فِى ٱلدِّينِ وَلِيُنذِرُوا۟ قَوْمَهُمْ إِذَا رَجَعُوٓا۟ إِلَيْهِمْ لَعَلَّهُمْ يَحْذَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy122. ምእምናንም (ከነቢዩ ጋር ካልኾነ) በሙሉ ሊወጡ አይገባም፡፡ ከእነሱ ውስጥ ከየክፍሉ አንዲት ጭፍራ ለምን አትወጣም፡፡ (ሌሎቹ) ሃይማኖትን እንዲማሩና ወገኖቻቸው ወደነርሱ በተመለሱ ጊዜ እንዲጠነቀቁ ይገስጹዋቸው ዘንድ (ለምን አይቀሩም)፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ قَٰتِلُوا۟ ٱلَّذِينَ يَلُونَكُم مِّنَ ٱلْكُفَّارِ وَلْيَجِدُوا۟ فِيكُمْ غِلْظَةً وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy123. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአቅራቢያችሁ ያሉትን ከሓዲያን ተዋጉ:: በናንተ ውስጥ ብርታትን ያግኙ:: አላህም ከሚጠነቀቁት ጋር መሆኑን እወቁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا مَآ أُنزِلَتْ سُورَةٌ فَمِنْهُم مَّن يَقُولُ أَيُّكُمْ زَادَتْهُ هَٰذِهِۦٓ إِيمَٰنًا فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ فَزَادَتْهُمْ إِيمَٰنًا وَهُمْ يَسْتَبْشِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy124. ምዕራፍ በተወረደ ጊዜ ከአስመሳዮች ውስጥ «ማንኛችሁ ነው ይህ ምዕራፍ እምነትን የጨመረለት?» የሚል ሰው አለ:: እነዚያ ያመኑት ሰዎች የሚደሰቱ ሲሆኑ እምነትን ጨመረላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمَّا ٱلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌ فَزَادَتْهُمْ رِجْسًا إِلَىٰ رِجْسِهِمْ وَمَاتُوا۟ وَهُمْ كَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy125. እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ክፍሎች ግን በርክሰታቸው ላይ እርክሰትን ጨመረላቸው:: እነርሱም ከሓዲያን ሆነው ሞቱ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَا يَرَوْنَ أَنَّهُمْ يُفْتَنُونَ فِى كُلِّ عَامٍ مَّرَّةً أَوْ مَرَّتَيْنِ ثُمَّ لَا يَتُوبُونَ وَلَا هُمْ يَذَّكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy126. በየዓመቱ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እነርሱ የሚሞከሩ መሆናቸውን አያዩምን? ከዚያ አይጸጸቱምን?እነርሱም አይገሰጹምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا مَآ أُنزِلَتْ سُورَةٌ نَّظَرَ بَعْضُهُمْ إِلَىٰ بَعْضٍ هَلْ يَرَىٰكُم مِّنْ أَحَدٍ ثُمَّ ٱنصَرَفُوا۟ صَرَفَ ٱللَّهُ قُلُوبَهُم بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَفْقَهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy127. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን የሚያወሳ ምዕራፍም በተወረደ ጊዜ «የሚያያችሁ (ሰው) አለን?» እያሉ ከፊሎቻቸው ወደ ከፊሉ ይመለከታሉ:: ከዚያ ተደብቀው ይሄዳሉ:: እነርሱ የማያውቁ ህዝቦች በመሆናቸው አላህ ልቦቻቸውን አዞረ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَقَدْ جَآءَكُمْ رَسُولٌ مِّنْ أَنفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُم بِٱلْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy128. (ሰዎች ሆይ!) ከጎሳችሁ ውስጥ የሆነ መቸገራችሁ በእርሱ ላይ ከባድ ጉዳይ የሆነበት፤ እናንተ እምነት እንዲኖራችሁ በጣም የሚጓጓና ለትክክለኛ አማኞችም ሩህሩህና አዛኝ የሆነ መልዕክተኛ (ሙሐመድ) መጣላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَقُلْ حَسْبِىَ ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَهُوَ رَبُّ ٱلْعَرْشِ ٱلْعَظِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy129. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ቢያፈገፍጉ አላህ በቂዬ ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: እርሱም የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70