أَلَا تُقَٰتِلُونَ قَوْمًا نَّكَثُوٓا۟ أَيْمَٰنَهُمْ وَهَمُّوا۟ بِإِخْرَاجِ ٱلرَّسُولِ وَهُم بَدَءُوكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍ أَتَخْشَوْنَهُمْ فَٱللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخْشَوْهُ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy13. እነዚያ መሀላዎቻቸውን ያፈረሱትን፤ መልዕክተኛውንም ከሀገር ለማውጣት ያሰቡትን ህዝቦች እነርሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ጦርነት የጀመሯችሁን ህዝቦች ሲሆኑ ለምን አትወጓቸዉም? ትፈሯቸዋላችሁን? ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ አላህን ይበልጥ ልትፈሩት የተገባው ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqመሓላዎቻቸውን ያፈረሱትን መልክተኛውንም ለማውጣት ያሰቡትን ሕዝቦች እነሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመሩዋችሁ ሲኾኑ ለምን አትዋጉዋቸውም ትፈሩዋቸዋላችሁን ምእምናን እንደ ኾናችሁም አላህ ይበልጥ ልትፈሩት የተገባው ነው፡፡