إِنَّ عِدَّةَ ٱلشُّهُورِ عِندَ ٱللَّهِ ٱثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِى كِتَٰبِ ٱللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ مِنْهَآ أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلْقَيِّمُ فَلَا تَظْلِمُوا۟ فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ وَقَٰتِلُوا۟ ٱلْمُشْرِكِينَ كَآفَّةً كَمَا يُقَٰتِلُونَكُمْ كَآفَّةً وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلْمُتَّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy36. የወራት ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አስራ ሁለት ወር ብቻ ነው:: ከእነርሱም መካከል አራቱ የተከበሩ ወሮች ናቸው:: ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው:: በእነርሱ ውስጥም (ክብሮቻቸውን በመጣስ) ነፍሶቻችሁን አትበድሉ:: አጋሪዎችንም በአንድ ላይ ሆነው እንደሚጋደሏችሁ በአንድ ላይ ሆናችሁ ተጋደሏቸው:: አላህ በእርዳታው እርሱኑ ከሚፈሩት ጋር መሆኑን እወቁ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡ አጋሪዎችንም በአንድ ላይ ኾነው እንደሚዋጉዋችሁ በአንድ ላይ ኾናችሁ ተጋደሉዋቸው፡፡ አላህም ከሚፈሩት ጋር መኾኑን ዕወቁ፡፡