caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ At-Tawba፣ አንቀጽ 107

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 113 · 9:107

وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ مَسْجِدًا ضِرَارًا وَكُفْرًا وَتَفْرِيقًۢا بَيْنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ وَإِرْصَادًا لِّمَنْ حَارَبَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ مِن قَبْلُ وَلَيَحْلِفُنَّ إِنْ أَرَدْنَآ إِلَّا ٱلْحُسْنَىٰ وَٱللَّهُ يَشْهَدُ إِنَّهُمْ لَكَٰذِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy107. እነዚያም አማኞችን ለመጉዳት ክህደትንም ለማበረታታት በአማኞችም መካከል ለመለያየት ከአሁን በፊት አላህንና መልዕክተኛውን የተዋጋውን ሰው ለመጠባበቅ መስጊዱን የሠሩት ሰዎች ከእነርሱ ናቸው:: «መልካምን እንጂ ሌላ አልሻንም።» ሲሉ በእርግጥ ይምላሉ:: አላህ ደግሞ ውሸታሞች መሆናቸውን በእርግጥ ይመሰክራል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያም (ምእምናንን) ለመጉዳት፣ ክህደትንም (ለማበርታት)፣ በምእምናንም መካከል ለመለያየት፣ ከአሁን በፊት አላህንና መልክተኛውን የተዋጋውንም ሰው ለመጠባበቅ መስጊድን የሠሩት (ከነሱ ናቸው)፡፡ መልካምን ሥራ እንጂ ሌላ አልሻንም ሲሉም በእርግጥ ይምላሉ፡፡ አላህም እነሱ በእርግጥ ውሸታሞች መኾናቸውን ይመሰክራል፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70