مَا كَانَ لِلْمُشْرِكِينَ أَن يَعْمُرُوا۟ مَسَٰجِدَ ٱللَّهِ شَٰهِدِينَ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِم بِٱلْكُفْرِ أُو۟لَٰٓئِكَ حَبِطَتْ أَعْمَٰلُهُمْ وَفِى ٱلنَّارِ هُمْ خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy17. አጋሪዎች በራሳቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ ሲሆኑ የአላህን መስጊዶች ሊንከባከቡ አይገባቸዉም:: እነዚያ ሥራዎቻቸው የተበላሹና በአኼራም በእሳት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለከሓዲዎች በነፍሶቻቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ ሲኾኑ የአላህን መስጊዶች ሊሠሩ አይገባቸውም፡፡ እነዚያ ሥራዎቻቸው ተበላሹ፡፡ እነሱም በእሳት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡