caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ At-Tawba፣ አንቀጽ 69

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 113 · 9:69

كَٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ كَانُوٓا۟ أَشَدَّ مِنكُمْ قُوَّةً وَأَكْثَرَ أَمْوَٰلًا وَأَوْلَٰدًا فَٱسْتَمْتَعُوا۟ بِخَلَٰقِهِمْ فَٱسْتَمْتَعْتُم بِخَلَٰقِكُمْ كَمَا ٱسْتَمْتَعَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُم بِخَلَٰقِهِمْ وَخُضْتُمْ كَٱلَّذِى خَاضُوٓا۟ أُو۟لَٰٓئِكَ حَبِطَتْ أَعْمَٰلُهُمْ فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْخَٰسِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy69. (አስመሳዮች ሆይ!) ተግባራችሁ ልክ እንደእነዚያ ከናንተ በፊት እንደነበሩት ህዝቦች ነው:: ከናንተ ይበልጥ በሃይል የበረቱ በገንዘብና በልጆችም ከናንተ ይበልጥ የበዙ ነበሩ:: በእድላቸው ተጠቀሙ:: እነዚያም ከእናንተ በፊት የነበሩት በዕድላቸው እንደተጠቀሙ በዕድላችሁ ተጠቀማችሁ፡፡ እንደዘባረቁትም ዘባረቃችሁ:: እነዚያ ስራዎቻቸው በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ተበላሸ:: ከሳሪዎቹም ማለት እነርሱው ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእንደነዚያ ከናንተ በፊት እንደ ነበሩት ናችሁ፡፡ ከእናንተ ይበልጥ በኃይል የበረቱ በገንዘቦችም በልጆችም ይበልጥ የበዙ ነበሩ፡፡ በዕድላቸውም ተጠቀሙ፡፡ እነዚያም ከእናንተ በፊት የነበሩት በዕድላቸው እንደተጠቀሙ በዕድላችሁ ተጠቀማችሁ፡፡ እንደነዚያም እንደዘባረቁት ዘባረቃችሁ፡፡ እነዚያ ሥራዎቻቸው በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም ተበላሹ፡፡ እነዚያም ከሳሪዎቹ እነሱ ናቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70