مَا كَانَ لِأَهْلِ ٱلْمَدِينَةِ وَمَنْ حَوْلَهُم مِّنَ ٱلْأَعْرَابِ أَن يَتَخَلَّفُوا۟ عَن رَّسُولِ ٱللَّهِ وَلَا يَرْغَبُوا۟ بِأَنفُسِهِمْ عَن نَّفْسِهِۦ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ لَا يُصِيبُهُمْ ظَمَأٌ وَلَا نَصَبٌ وَلَا مَخْمَصَةٌ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَا يَطَـُٔونَ مَوْطِئًا يَغِيظُ ٱلْكُفَّارَ وَلَا يَنَالُونَ مِنْ عَدُوٍّ نَّيْلًا إِلَّا كُتِبَ لَهُم بِهِۦ عَمَلٌ صَٰلِحٌ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجْرَ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy120. የመዲና ሰዎችና በዙሪያቸው ያሉት የዘላን ዓረብ ህዝቦች ከአላህ መልዕክተኛ ጥሪ ወደ ኋላ ሊቀሩና ነፍሶቻቸውንም ከነፍሱ አብልጠው ሊወዱ አይገባቸዉም ነበር:: ይህም የሆነው ለእነርሱ መልካም ሥራ የሚጻፍላቸው ቢሆን እንጂ በአላህ መንገድ ላይ ጥምም ድካምም ርሀብም የማይነካቸው ከሓዲያንንም የሚያስቆጭን ስፍራ የማይረግጡ ከጠላትም የሚጎዳን ነገር (መግደል) የማያገኙ በመሆናቸው ነው:: አላህ የመልካም ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለመዲና ሰዎችና ከአዕራብም በዙሪያቸው ላሉት ሰዎች ከአላህ መልክተኛ ወደኋላ ሊቀሩ ነፍሶቻቸውንም ከነፍሱ አብልጠው ሊወዱ አይገባቸውም ነበር፡፡ ይህ (ከመቅረት መከልከል) ለእነርሱ መልካም ሥራ የሚጻፍላቸው ቢኾን እንጅ በአላህ መንገድ ላይ ጥምም፣ ድካምም፣ ረኃብም፣ የማይነካቸው ከሐዲዎችንም የሚያስቆጭን ስፍራ የማይረግጡ፣ ከጠላትም የሚጎዳን ነገር (መግደልን መማረክን መዝረፍን) የማያገኙ በመኾናቸው ነው፡፡ አላህ የመልካም ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና፡፡