يَحْلِفُونَ بِٱللَّهِ مَا قَالُوا۟ وَلَقَدْ قَالُوا۟ كَلِمَةَ ٱلْكُفْرِ وَكَفَرُوا۟ بَعْدَ إِسْلَٰمِهِمْ وَهَمُّوا۟ بِمَا لَمْ يَنَالُوا۟ وَمَا نَقَمُوٓا۟ إِلَّآ أَنْ أَغْنَىٰهُمُ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ مِن فَضْلِهِۦ فَإِن يَتُوبُوا۟ يَكُ خَيْرًا لَّهُمْ وَإِن يَتَوَلَّوْا۟ يُعَذِّبْهُمُ ٱللَّهُ عَذَابًا أَلِيمًا فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَمَا لَهُمْ فِى ٱلْأَرْضِ مِن وَلِىٍّ وَلَا نَصِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy74. ምንም ያላሉ ለመሆናቸው በአላህ ይምላሉ:: ግን የክህደትን ቃል በእርግጥ አሉ:: ከእስልምናቸዉም በኋላ ካዱ:: ያላገኙትንም ነገር አሰቡ:: አላህና መልዕክተኛው ከችሮታው ያከበራቸው መሆኑን እንጂ ሌላን አልጠሉም:: ቢጸጸቱም ለእነርሱ የተሻለ ይሆናል:: ቢሸሹም አላህ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም አሳማሚን ቅጣት ይቀጣቸዋል:: ለእነርሱም በምድር ውስጥ ምንም ወዳጅና ረዳት የላቸዉም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqምንም ያላሉ ለመኾናቸው በአላህ ይምላሉ፡፡ የክህደትንም ቃል በእርግጥ አሉ፡፡ ከእስልምናቸውም በኋላ ካዱ፡፡ ያላገኙትንም ነገር አሰቡ፡፡ አላህም ከችሮታው መልክተኛውም (እንደዚሁ) ያከበራቸው መኾኑን እንጂ ሌላን አልጠሉም፡፡ ቢጸጸቱም ለእነሱ የተሻለ ይኾናል፡፡ ቢሸሹም አላህ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም አሳማሚን ቅጣት ይቀጣቸዋል፡፡ ለእነሱም በምድር ውስጥ ምንም ወዳጅና ረዳት የላቸውም፡፡