caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ At-Tawba፣ አንቀጽ 60

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 113 · 9:60

إِنَّمَا ٱلصَّدَقَٰتُ لِلْفُقَرَآءِ وَٱلْمَسَٰكِينِ وَٱلْعَٰمِلِينَ عَلَيْهَا وَٱلْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِى ٱلرِّقَابِ وَٱلْغَٰرِمِينَ وَفِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱبْنِ ٱلسَّبِيلِ فَرِيضَةً مِّنَ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy60. ግዴታ ዘካን የሚከፈሉት ለድሆች፤ ለችግረኞች፤ በእርሷም ላይ ለሚሰሩ ሠራተኞች፤ ልቦቻቸው በኢስላም ለሚለማመዱት ወገኖች፤ ጫንቃዎችን (ባሪያዎች) ነጻ ለማውጣት፤ ባለ እዳ ለሆኑት፤ በአላህ መንገድም ለሚሰሩና (ስንቅ ላለቀበት) መንገደኛ ብቻ ነው:: ይህ ስርአት ከአላህ የተደነገገ ግዴታ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱት፣ ጫንቃዎችንም (በባርነት ተገዢዎችን) (ነጻ በማውጣት)፣ በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሠሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70