وَمِنَ ٱلْأَعْرَابِ مَن يُؤْمِنُ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَيَتَّخِذُ مَا يُنفِقُ قُرُبَٰتٍ عِندَ ٱللَّهِ وَصَلَوَٰتِ ٱلرَّسُولِ أَلَآ إِنَّهَا قُرْبَةٌ لَّهُمْ سَيُدْخِلُهُمُ ٱللَّهُ فِى رَحْمَتِهِۦٓ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy99. ከአረብ ዘላኖች መካከል በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሚሰጣቸውንም ምጽዋቶች አላህ ዘንድ መቃረቢያዎችና ወደ መልዕክተኛው ጸሎቶች መዳረሻ አድርጎ የሚይዝ ክፍል አለ:: አስተዉሉ! እርሷ ለእነርሱ በእርግጥ አቃራቢ ናት:: አላህ በችሮታው ውስጥ በገነቱ በእርግጥ ያስገባቸዋል:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከአዕራቦችም በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሚሰጣቸውንም (ምጽዋቶች) አላህ ዘንድ መቃረቢያዎችና ወደ መልክተኛው ጸሎቶች መዳረሻ አድርጎ የሚይዝ ሰው አልለ፡፡ ንቁ! እርሷ ለእነሱ በእርግጥ አቃራቢ ናት፡፡ አላህ በችሮታው ውስጥ (በገነቱ) በእርግጥ ያስገባቸዋል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡