caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ At-Tawba፣ አንቀጽ 24

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 113 · 9:24

قُلْ إِن كَانَ ءَابَآؤُكُمْ وَأَبْنَآؤُكُمْ وَإِخْوَٰنُكُمْ وَأَزْوَٰجُكُمْ وَعَشِيرَتُكُمْ وَأَمْوَٰلٌ ٱقْتَرَفْتُمُوهَا وَتِجَٰرَةٌ تَخْشَوْنَ كَسَادَهَا وَمَسَٰكِنُ تَرْضَوْنَهَآ أَحَبَّ إِلَيْكُم مِّنَ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَجِهَادٍ فِى سَبِيلِهِۦ فَتَرَبَّصُوا۟ حَتَّىٰ يَأْتِىَ ٱللَّهُ بِأَمْرِهِۦ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْفَٰسِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አባቶቻችሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁ፤ ወንድሞቻችሁ፤ ሚስቶቻችሁ ዘመዶቻችሁ፤ የሰበሰባችኋቸው ሀብቶች፤ መክሰሯን የምትፈሯት ንግድና የምትወዷቸው መኖሪያዎች በእናንተ ዘንድ ከአላህ፤ ከመልዕክተኛውና በእርሱ መንገድ ከመታገል ይበልጥ የተወደዱ ከሆኑ አላህ ጉዳዩን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ በላቸው:: አላህ አመጸኞች ህዝቦችን ሁሉ አይመራም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«አባቶቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁም፣ ሚስቶቻችሁም፣ ዘመዶቻችሁም፣ የሰበሰባችኋቸው ሀብቶችም፣ መክሰሩዋን የምትፈሩዋት ንግድም፣ የምትወዷቸው መኖሪያዎችም እናንተ ዘንድ ከአላህና ከመልክተኛው በርሱ መንገድም ከመታገል ይበልጥ የተወደዱ እንደኾኑ አላህ ትእዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ» በላቸው፡፡ አላህም አመጸኞች ሕዝቦችን አይመራም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70