كَيْفَ وَإِن يَظْهَرُوا۟ عَلَيْكُمْ لَا يَرْقُبُوا۟ فِيكُمْ إِلًّا وَلَا ذِمَّةً يُرْضُونَكُم بِأَفْوَٰهِهِمْ وَتَأْبَىٰ قُلُوبُهُمْ وَأَكْثَرُهُمْ فَٰسِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy8. በእናንተ ላይ ቢያይሉ ዝምድናንና ቃልኪዳንን የማይጠብቁ ሰዎች ሲሆኑ እንዴት ከአላህና ከመልዕክተኛው ዘንድ ቃልኪዳን ይኖራቸዋል? በአፎቻቸው ይሸነግሏችኋል:: ልቦቻቸው ግን እምቢ ይላሉ:: አብዛኞቻቸዉም አመጸኞች ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበእናንተ ላይ ቢያይሉም በእናንተ ውስጥ ዝምድናንና ቃል ኪዳንን የማይጠብቁ ሲኾኑ እንዴት (ቃል ኪዳን ይኖራቸዋል)፡፡ በአፎቻቸው ያስወድዷችኋል፡፡ ልቦቻቸውም እንቢ ይላሉ፡፡ አብዛኞቻቸውም አመጸኞች ናቸው፡፡