caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ At-Tawba፣ አንቀጽ 90

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 113 · 9:90

وَجَآءَ ٱلْمُعَذِّرُونَ مِنَ ٱلْأَعْرَابِ لِيُؤْذَنَ لَهُمْ وَقَعَدَ ٱلَّذِينَ كَذَبُوا۟ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ سَيُصِيبُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy90. ከአረብ ዘላኖች መካከል ይቅርታ ፈላጊዎቹ እንዲፈቀድላቸው መጡ:: እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን ያስተባበሉት ግን ተቀመጡ:: እነዚያን በአላህ የካዱት ሰዎች አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል (ያገኛቸዋል)::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከአዕራቦችም ይቅርታ ፈላጊዎቹ ለእነሱ እንዲፈቀድላቸው መጡ፡፡ እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የዋሹትም ተቀመጡ፡፡ ከነሱ እነዚያን የካዱትን አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70