ሱረቱ Yunus يونس
109 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 51
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓر تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ ٱلْحَكِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy1. አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ እነዚህ ጥበብ ከተሞላው መፅሀፍ አንቀፆች ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَكَانَ لِلنَّاسِ عَجَبًا أَنْ أَوْحَيْنَآ إِلَىٰ رَجُلٍ مِّنْهُمْ أَنْ أَنذِرِ ٱلنَّاسَ وَبَشِّرِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَنَّ لَهُمْ قَدَمَ صِدْقٍ عِندَ رَبِّهِمْ قَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎችን (ከሓዲያንን) አስፈራራ፤ እነዚያን ያመኑትን ደግሞ ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መሆኑን አብስር» በማለት ከእነርሱ መካከል ወደ ሆነ አንድ ሰው ራዕይን ማውረዳችን ለሰዎች ድንቅ ሆነባቸውን? ከሓዲያን «ይህ (ሰው) ግልጽ ድግምተኛ ነው።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ يُدَبِّرُ ٱلْأَمْرَ مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِنۢ بَعْدِ إِذْنِهِۦ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy3. ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ ብቻ የፈጠራቸው አላህ ነው:: ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲሆን (ለሱ ክብር በምስማማ መልኩ) በዐርሹ ላይ ተደላደለ፡፡ ከእርሱ በጎ ፈቃድ በኋላ ቢሆን እንጂ አንድም አማላጅ የለም:: እነሆ ይህ አላህ ጌታችሁ ነው:: እናም በትክክል ተገዙት:: አትገሰጹምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَيْهِ مَرْجِعُكُمْ جَمِيعًا وَعْدَ ٱللَّهِ حَقًّا إِنَّهُۥ يَبْدَؤُا۟ ٱلْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ لِيَجْزِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ بِٱلْقِسْطِ وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَهُمْ شَرَابٌ مِّنْ حَمِيمٍ وَعَذَابٌ أَلِيمٌۢ بِمَا كَانُوا۟ يَكْفُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy4. (ሰዎች ሆይ!) የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ እርሱ ብቻ ነው:: ይህም የተረጋገጠ የአላህ ቃል ኪዳን ነው:: እርሱ መፍጠርን ይጀምራል:: ከዚያም እነዚያ ያመኑትንና መልካም የሠሩትን ሰዎች በትክክል ይመነዳ ዘንድ ፍጡራንን ከሞት በኋላ ህያው ያደርጋል:: እነዚያ የካዱት ክፍሎች ግን በክህደታቸው ምክንያት የፈላ ውሃ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ ٱلشَّمْسَ ضِيَآءً وَٱلْقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُۥ مَنَازِلَ لِتَعْلَمُوا۟ عَدَدَ ٱلسِّنِينَ وَٱلْحِسَابَ مَا خَلَقَ ٱللَّهُ ذَٰلِكَ إِلَّا بِٱلْحَقِّ يُفَصِّلُ ٱلْـَٔايَٰتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy5. እርሱ ያ ጸሐይን አንጸባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ፤ የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለጨረቃ የተለያዩ መስፈሪያ እርከኖችን የወሰነ ነው:: አላህ ይህንን በእውነት እንጂ በከንቱ አልፈጠረዉም:: ለሚያውቁ ሕዝቦችም አናቅጽን ያብራራል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ فِى ٱخْتِلَٰفِ ٱلَّيْلِ وَٱلنَّهَارِ وَمَا خَلَقَ ٱللَّهُ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy6. ሌሊትና ቀን በመተካካታቸው አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ በፈጠረው ሁሉ ለሚጠነቀቁ ሕዝቦች ታላላቅ ተአምራት አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يَرْجُونَ لِقَآءَنَا وَرَضُوا۟ بِٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَٱطْمَأَنُّوا۟ بِهَا وَٱلَّذِينَ هُمْ عَنْ ءَايَٰتِنَا غَٰفِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy7. እነዚያ ከኛ ጋር መገናኘታቸውን ተስፋ የማያደርጉ ቅርቢቱን ሕይወት የወደዱና በእርሷም የረኩ እነርሱ ከአናቅጻችን ዘንጊዎች የሆኑት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ مَأْوَىٰهُمُ ٱلنَّارُ بِمَا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy8. እነዚያ ይሠሩት በነበሩት ኃጢአት ምክንያት መኖሪያቸው በእሳት ውስጥ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ يَهْدِيهِمْ رَبُّهُم بِإِيمَٰنِهِمْ تَجْرِى مِن تَحْتِهِمُ ٱلْأَنْهَٰرُ فِى جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy9. እነዚያ በአላህ ያመኑትና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ሰዎች ሁሉ ጌታቸው በእምነታቸው ምክንያት የገነትን መንገድ ይመራቸዋል:: ከሥሮቻቸው ወንዞች ይፈስሳሉ:: በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥም ዝንታለም ይኖራሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
دَعْوَىٰهُمْ فِيهَا سُبْحَٰنَكَ ٱللَّهُمَّ وَتَحِيَّتُهُمْ فِيهَا سَلَٰمٌ وَءَاخِرُ دَعْوَىٰهُمْ أَنِ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy10. በእርሷም ውስጥ ጸሎታቸው የሚሆነው «ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ።» ማለት ብቻ ነው:: በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸው ሰላም መባባል ነው:: የመጨረሻ ጸሎታቸዉም «ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው።» ማለት ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ يُعَجِّلُ ٱللَّهُ لِلنَّاسِ ٱلشَّرَّ ٱسْتِعْجَالَهُم بِٱلْخَيْرِ لَقُضِىَ إِلَيْهِمْ أَجَلُهُمْ فَنَذَرُ ٱلَّذِينَ لَا يَرْجُونَ لِقَآءَنَا فِى طُغْيَٰنِهِمْ يَعْمَهُونَ
Amharic Translation - Africa Academy11. አላህ ለሰዎች ደግን ነገር ለማግኘት እንደ መቻኮላቸው የሚጠይቁትንም ክፉን ነገር ቢያቻኩልባቸው ኖሮ በዚያችው ጊዜያቸው እድሜያቸው በተፈጸመ ነበር:: እነዚያን መገናኘታችንን ተስፋ የማያደርጉትን ሰዎች በጥመታቸው ውስጥ እየዋለሉ እንተዋቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا مَسَّ ٱلْإِنسَٰنَ ٱلضُّرُّ دَعَانَا لِجَنۢبِهِۦٓ أَوْ قَاعِدًا أَوْ قَآئِمًا فَلَمَّا كَشَفْنَا عَنْهُ ضُرَّهُۥ مَرَّ كَأَن لَّمْ يَدْعُنَآ إِلَىٰ ضُرٍّ مَّسَّهُۥ كَذَٰلِكَ زُيِّنَ لِلْمُسْرِفِينَ مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy12. የሰውን ልጅ ጉዳት ባገኘው ጊዜ በጎኑ ላይ ተጋድሞ ወይም ተቀምጦ ወይም ቆሞ ይለምንና ጉዳቱን ከእሱ ላይ በገለጥንለት ጊዜ ላገኘው ጉዳት እንዳልተማጸንን ሆኖ ያልፋል:: ልክ እንደዚሁ ለድንበር አላፊዎች ሁሉ ይሠሩት የነበሩት መጥፎ ሥራ ተሸለመላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أَهْلَكْنَا ٱلْقُرُونَ مِن قَبْلِكُمْ لَمَّا ظَلَمُوا۟ وَجَآءَتْهُمْ رُسُلُهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَمَا كَانُوا۟ لِيُؤْمِنُوا۟ كَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْقَوْمَ ٱلْمُجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy13. ከናንተ በፊት የነበሩትን የብዙ ክፍለ ዘመናት ሰዎች መልዕክተኞቻቸው በማስረጃዎች የመጡላቸው ሲሆኑ በበደሉና የማያምኑም በሆኑ ጊዜ አጠፋናቸው:: ልክ እንደዚሁ ተንኮለኞችን ህዝቦች እንቀጣለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ جَعَلْنَٰكُمْ خَلَٰٓئِفَ فِى ٱلْأَرْضِ مِنۢ بَعْدِهِمْ لِنَنظُرَ كَيْفَ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy14. ከዚያ እንዴት እንደምትሠሩ ልንመለከት ከእነርሱ በኋላ በምድር ላይ ምትኮች አደረግናችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ءَايَاتُنَا بَيِّنَٰتٍ قَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَرْجُونَ لِقَآءَنَا ٱئْتِ بِقُرْءَانٍ غَيْرِ هَٰذَآ أَوْ بَدِّلْهُ قُلْ مَا يَكُونُ لِىٓ أَنْ أُبَدِّلَهُۥ مِن تِلْقَآئِ نَفْسِىٓ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ إِنِّىٓ أَخَافُ إِنْ عَصَيْتُ رَبِّى عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አናቅጻችን ግልጽ ሆነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩት (የማይሹት) ሰዎች «ከዚህ ሌላ የሆነን ቁርኣን አምጣልን ወይም ለውጠው።» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ከራሴ በኩል ልለውጠው አይገባኝም:: ወደ እኔ የሚወረደውን እንጂ አልከተልም:: እኔ በጌታዬ ትዕዛዝ ላይ ባምጽ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُل لَّوْ شَآءَ ٱللَّهُ مَا تَلَوْتُهُۥ عَلَيْكُمْ وَلَآ أَدْرَىٰكُم بِهِۦ فَقَدْ لَبِثْتُ فِيكُمْ عُمُرًا مِّن قَبْلِهِۦٓ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy16. (መልዕከተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ባላነበብኩትና አላህ እርሱን ባላሳወቃችሁ ነበር:: በእናንተም ውስጥ ከእርሱ በፊት ምንም ሳልል ብዙን እድሜ በእርግጥ ኖሬያለሁ። አታውቁምን?» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓ إِنَّهُۥ لَا يُفْلِحُ ٱلْمُجْرِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy17. በአላህ ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይ ከአናቅ ጹ መካከል (በአንዷ እንኳን) ካስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እነሆ አመጸኞች አይድኑም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَٰٓؤُلَآءِ شُفَعَٰٓؤُنَا عِندَ ٱللَّهِ قُلْ أَتُنَبِّـُٔونَ ٱللَّهَ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِى ٱلْأَرْضِ سُبْحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy18. አጋሪዎች ከአላህ ሌላ የማይጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውን ይገዛሉ:: «እነዚህ አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው።» ይላሉም። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ እናንተ ትነግሩታላችሁን?» በላቸው:: አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ:: ላቀም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا كَانَ ٱلنَّاسُ إِلَّآ أُمَّةً وَٰحِدَةً فَٱخْتَلَفُوا۟ وَلَوْلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتْ مِن رَّبِّكَ لَقُضِىَ بَيْنَهُمْ فِيمَا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy19. ሰዎች አንድ ህዝብ እንጂ ሌላ አልነበሩም:: ከዚያ ተለያዩ:: ከጌታህ ያለፈ ቃልም ባልነበረ ኖሮ በዚያ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው በቶሎ በተፈረደ ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَقُولُونَ لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْهِ ءَايَةٌ مِّن رَّبِّهِۦ فَقُلْ إِنَّمَا ٱلْغَيْبُ لِلَّهِ فَٱنتَظِرُوٓا۟ إِنِّى مَعَكُم مِّنَ ٱلْمُنتَظِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ተዓምር ለምን አትወረድለትም?» ይላሉ:: «ሩቅ ነገር ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: እናንተም ተጠባበቁ እኔም ከናንተው ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَآ أَذَقْنَا ٱلنَّاسَ رَحْمَةً مِّنۢ بَعْدِ ضَرَّآءَ مَسَّتْهُمْ إِذَا لَهُم مَّكْرٌ فِىٓ ءَايَاتِنَا قُلِ ٱللَّهُ أَسْرَعُ مَكْرًا إِنَّ رُسُلَنَا يَكْتُبُونَ مَا تَمْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎች ካገኛቸው ጉዳት በኋላ እዝነትን ምቾትን ባቀመስናቸው ጊዜ ወዲያውኑ ለእነርሱ በተዓምራቶቻችን በማላገጥ ተንኮል ይኖራቸዋል:: «አላህ ቅጣቱ ፈጣን ነው።» በላቸው። መልዕክተኞቻችን የምታሴሩትን ነገር ሁሉ በእርግጥ ይጽፋሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هُوَ ٱلَّذِى يُسَيِّرُكُمْ فِى ٱلْبَرِّ وَٱلْبَحْرِ حَتَّىٰٓ إِذَا كُنتُمْ فِى ٱلْفُلْكِ وَجَرَيْنَ بِهِم بِرِيحٍ طَيِّبَةٍ وَفَرِحُوا۟ بِهَا جَآءَتْهَا رِيحٌ عَاصِفٌ وَجَآءَهُمُ ٱلْمَوْجُ مِن كُلِّ مَكَانٍ وَظَنُّوٓا۟ أَنَّهُمْ أُحِيطَ بِهِمْ دَعَوُا۟ ٱللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ لَئِنْ أَنجَيْتَنَا مِنْ هَٰذِهِۦ لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّٰكِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy22. (ሰዎች ሆይ!) አላህ ያ በየብስና በባሕር የሚያስኬዳችሁ ነው:: በመርከቦችም ውስጥ በሆናችሁና በእነርሱም በመልካም ነፋስ በእርሷ የተደሰቱ ሆነው መርከቦቹ በተንሻለሉ ጊዜ ሀይለኛ ነፋስ ትመጣባቸዋለች:: ከየስፍራዉም ማዕበል ይመጣባቸዋል:: እነርሱም ለጥፋት የተከበቡ መሆናቸውን ሲያረጋግጡ ያን ጊዜ አላህን «ከዚህች ጭንቀት ብታድነን ከአመስጋኞቹ እንሆናለን።» ሲሉ እምነታቸውን ለእርሱ ብቻ ፍጹም አድርገው ይለምኑታል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّآ أَنجَىٰهُمْ إِذَا هُمْ يَبْغُونَ فِى ٱلْأَرْضِ بِغَيْرِ ٱلْحَقِّ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّمَا بَغْيُكُمْ عَلَىٰٓ أَنفُسِكُم مَّتَٰعَ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا ثُمَّ إِلَيْنَا مَرْجِعُكُمْ فَنُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy23. በአዳናቸዉም ጊዜ እነርሱ ወዲያውኑ ያለ አግባብ በምድር ላይ ወሰን ያልፋሉ። እናንተ ሰዎች ሆይ ወሰን ማለፋችሁ ጥፋቱ በነፍሶቻችሁ ላይ ብቻ ነው:: እርሱ የቅርቢቱ ህይወት መጠቀሚያ ነው:: ከዚያ መመለሻችሁ ወደ እኛ ነው:: ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እንነግራችኋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّمَا مَثَلُ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا كَمَآءٍ أَنزَلْنَٰهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ فَٱخْتَلَطَ بِهِۦ نَبَاتُ ٱلْأَرْضِ مِمَّا يَأْكُلُ ٱلنَّاسُ وَٱلْأَنْعَٰمُ حَتَّىٰٓ إِذَآ أَخَذَتِ ٱلْأَرْضُ زُخْرُفَهَا وَٱزَّيَّنَتْ وَظَنَّ أَهْلُهَآ أَنَّهُمْ قَٰدِرُونَ عَلَيْهَآ أَتَىٰهَآ أَمْرُنَا لَيْلًا أَوْ نَهَارًا فَجَعَلْنَٰهَا حَصِيدًا كَأَن لَّمْ تَغْنَ بِٱلْأَمْسِ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلْـَٔايَٰتِ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy24. . የቅርቢቱ ህይወት ምሳሌ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ በእርሱም ሰውና እንስሳዎች ከሚበሉት የምድር በቃይ ተቀላቅሎበት እንደፋፋ ምድርም ውበትዋን በያዘችና ባጌጠች ጊዜ ባለቤቶችዋን በእርሷ ላይ እነርሱ ቻዮች መሆናቸውን ባሰቡ ጊዜ ትዕዛዛችን ሌሊት ወይም ቀን መጥቶባት ትላንት እንዳልነበረች የታጨደች እንዳደረግናት ብጤ ነው:: ልክ እንደዚሁ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ሁሉ አናቅጽን እናብራራለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱللَّهُ يَدْعُوٓا۟ إِلَىٰ دَارِ ٱلسَّلَٰمِ وَيَهْدِى مَن يَشَآءُ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy25. አላህ (ሁል ጊዜም) ወደ ሰላም አገር ይጠራል:: የሚፈልገዉን ሰዉም ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِّلَّذِينَ أَحْسَنُوا۟ ٱلْحُسْنَىٰ وَزِيَادَةٌ وَلَا يَرْهَقُ وُجُوهَهُمْ قَتَرٌ وَلَا ذِلَّةٌ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy26. ለእነዚያ መልካም ለሠሩት ሰዎች መልካም ነገርና (ገነት) ሌላ ተጨማሪም አላቸው:: ፊቶቻቸውንም ጥቁረትና ውርደት አይሸፍናቸዉም:: እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ كَسَبُوا۟ ٱلسَّيِّـَٔاتِ جَزَآءُ سَيِّئَةٍۭ بِمِثْلِهَا وَتَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ مَّا لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِنْ عَاصِمٍ كَأَنَّمَآ أُغْشِيَتْ وُجُوهُهُمْ قِطَعًا مِّنَ ٱلَّيْلِ مُظْلِمًا أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy27. እነዚያ ኃጢአቶችን የሠሩት ደግሞ ኃጢአቲቱን የሚመጥን ቅጣት አለባቸው:: ውርደትም ትሸፍናቸዋለች :: እነርሱ ከአላህ ቅጣት ጠባቂ የላቸዉም:: ፊቶቻቸው በድቅድቅ ጨለማ ቁራጮች እንደ ተሸፈኑ ይሆናሉ:: እነዚያ የእሳት ሰዎች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘለዓለም ነዋሪዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَوْمَ نَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا ثُمَّ نَقُولُ لِلَّذِينَ أَشْرَكُوا۟ مَكَانَكُمْ أَنتُمْ وَشُرَكَآؤُكُمْ فَزَيَّلْنَا بَيْنَهُمْ وَقَالَ شُرَكَآؤُهُم مَّا كُنتُمْ إِيَّانَا تَعْبُدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማልክትንና አምላኪዎቻቸውን ሁሉ በአንድ የምንሰበስባቸውንና ከዚያም ለእነዚያ ላጋሩት «እናንተም ተጋሪዎቻችሁም ቦታችሁን ያዙ።» የምንልበትን ተጋሪዎቻቸዉም (እንዲህ) የሚሏቸው ሲሆኑ በመካከላቸው የምንለይበትን ቀን አስታውስ «ትገዙ የነበረው እኛን አልነበረም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَكَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدًۢا بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ إِن كُنَّا عَنْ عِبَادَتِكُمْ لَغَٰفِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy29. (ጣኦታቶቹ) «እኛን ለመገዛታችሁ ዘንጊዎች ለመሆናችን በኛና በእናንተ መካከል የአላህ መስካሪነት በቃ።» ይሏቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هُنَالِكَ تَبْلُوا۟ كُلُّ نَفْسٍ مَّآ أَسْلَفَتْ وَرُدُّوٓا۟ إِلَى ٱللَّهِ مَوْلَىٰهُمُ ٱلْحَقِّ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy30. በዚያ ቀን ነፍስ ሁሉ ያሳለፈችውን ሥራ ታውቃለች:: አጋሪዎች ወደ አላህ እውነተኛ ወደሆነው ጌታቸው ይመለሳሉ:: ያ በአላህ ላይ ይቀጣጥፋት የነበሩት ሁሉ ነገርም ይጠፋባቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ مَن يَرْزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ أَمَّن يَمْلِكُ ٱلسَّمْعَ وَٱلْأَبْصَٰرَ وَمَن يُخْرِجُ ٱلْحَىَّ مِنَ ٱلْمَيِّتِ وَيُخْرِجُ ٱلْمَيِّتَ مِنَ ٱلْحَىِّ وَمَن يُدَبِّرُ ٱلْأَمْرَ فَسَيَقُولُونَ ٱللَّهُ فَقُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረላችሁ ማን ነው? ከሙትም ህያውን የሚያወጣ፤ ከህያዉም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው?» በላቸው:: «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል:: «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ? ታዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمُ ٱلْحَقُّ فَمَاذَا بَعْدَ ٱلْحَقِّ إِلَّا ٱلضَّلَٰلُ فَأَنَّىٰ تُصْرَفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy32. እውነተኛው ጌታችሁ አላህ ብቻ ነው:: ከእውነት በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ? ከእውነት እንዴት ትዞራላችሁ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَذَٰلِكَ حَقَّتْ كَلِمَتُ رَبِّكَ عَلَى ٱلَّذِينَ فَسَقُوٓا۟ أَنَّهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy33. ልክ እንደዚሁ የጌታህ ቃል በእነዚያ ባመጹት ሰዎች ላይ ፈጽሞ የማያምኑ መሆናቸው ተረጋገጠ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ هَلْ مِن شُرَكَآئِكُم مَّن يَبْدَؤُا۟ ٱلْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ قُلِ ٱللَّهُ يَبْدَؤُا۟ ٱلْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከምታጋሯቸው ጣኦታት መካከል መፍጠርን የሚጀምር ከዚያ የሚመልስ አለን?» በላቸው። «አላህ ግን መፍጠርን ይጀምራል:: ከዚያ ይመልሰዋል:: ታዲያ ከእምነት እንዴት ትዘራላችሁ?» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ هَلْ مِن شُرَكَآئِكُم مَّن يَهْدِىٓ إِلَى ٱلْحَقِّ قُلِ ٱللَّهُ يَهْدِى لِلْحَقِّ أَفَمَن يَهْدِىٓ إِلَى ٱلْحَقِّ أَحَقُّ أَن يُتَّبَعَ أَمَّن لَّا يَهِدِّىٓ إِلَّآ أَن يُهْدَىٰ فَمَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከምታጋሯቸው ጣኦታት መካከልስ ወደ እውነት መንገድ የሚመራ አለን?» በላቸው:: «አላህ ግን ወደ እውነቱ ይመራል:: ወደ እውነት የሚመራው ጌታ ነውን ሊከተሉት የተገባው? ወይስ ካልተመራ በስተቀር የማይመራው? ለእናንተ ምን ( አስረጅ) አላችሁ? እንዴት በውሸት ትፈርዳላችሁ?» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا يَتَّبِعُ أَكْثَرُهُمْ إِلَّا ظَنًّا إِنَّ ٱلظَّنَّ لَا يُغْنِى مِنَ ٱلْحَقِّ شَيْـًٔا إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌۢ بِمَا يَفْعَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy36. አብዛኞቻቸው ጥርጣሬን እንጂ አይከተሉም:: ጥርጣሬ ደግሞ ከእውነት በፍጹም አያብቃቃም:: አላህ የሚሠሩትን ሁሉ አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا كَانَ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ ٱلَّذِى بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy37. ይህም (ቁርኣን) ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባዉም:: ይልቁንም ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን መጽሐፍ የሚያረጋግጥና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርግጥ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ يَقُولُونَ ٱفْتَرَىٰهُ قُلْ فَأْتُوا۟ بِسُورَةٍ مِّثْلِهِۦ وَٱدْعُوا۟ مَنِ ٱسْتَطَعْتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy38. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእውነት ሙሐመድ ቀጣጠፈው» ይላሉን? ይህን የሚሉ ከሆነ «መሰሉን አንድ ምዕራፍ እንኳ እስቲ አምጡ:: ለዚህም ጉዳይ ከአላህ ሌላ የቻላችሁትን ሁሉ ረዳት ጥሩ:: እውነተኞች እንደሆናችሁ ለዚህ ተጋግዛችሁ አምጡ።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلْ كَذَّبُوا۟ بِمَا لَمْ يُحِيطُوا۟ بِعِلْمِهِۦ وَلَمَّا يَأْتِهِمْ تَأْوِيلُهُۥ كَذَٰلِكَ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ فَٱنظُرْ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy39. ይልቁንም እውቀቱን ባላዳረሱትና ፍቹም ገና ባልመጣላቸው ነገር አስተባበሉ:: እንደዚሁ እነዚያ ከእነሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል፡፡ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የበዳዮች መጨረሻ እንዴት ይመስል እንደ ነበር በጥሞና ተመልከት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنْهُم مَّن يُؤْمِنُ بِهِۦ وَمِنْهُم مَّن لَّا يُؤْمِنُ بِهِۦ وَرَبُّكَ أَعْلَمُ بِٱلْمُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመካከላቸው ወደፊት በቁርኣን የሚያምኑ አሉ:: ከእነርሱም መካከል በእርሱ የማያምኑ አሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አጥፊዎቹን በጣም አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن كَذَّبُوكَ فَقُل لِّى عَمَلِى وَلَكُمْ عَمَلُكُمْ أَنتُم بَرِيٓـُٔونَ مِمَّآ أَعْمَلُ وَأَنَا۠ بَرِىٓءٌ مِّمَّا تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ቢያስተባብሉህም ለእኔ የራሴ ሥራ አለኝ:: እናንተም የራሳችሁ ሥራ አላችሁ:: እናንተ እኔ ከምሠራው ተግባር ንጹህ ናችሁ (አትጠየቁም):: እኔም እናንተ ከምትሠሩት ነገር ንጹህ ነኝ (አልጠየቅም)።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنْهُم مَّن يَسْتَمِعُونَ إِلَيْكَ أَفَأَنتَ تُسْمِعُ ٱلصُّمَّ وَلَوْ كَانُوا۟ لَا يَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy42. ከእነርሱ መካከል ወደ አንተ ንግግር የሚያዳምጡ የሚሰሙና የማያምኑ አሉ:: አንተ ደንቆሮዎችን የማያውቁ ቢሆኑም ታሰማለህን?::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنْهُم مَّن يَنظُرُ إِلَيْكَ أَفَأَنتَ تَهْدِى ٱلْعُمْىَ وَلَوْ كَانُوا۟ لَا يُبْصِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy43. ከእነርሱም መካከል ወደ አንተ የሚመለከቱ አሉ:: አንተ ልበ እውራንን የማያዩ ቢሆኑም ትመራለህን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَظْلِمُ ٱلنَّاسَ شَيْـًٔا وَلَٰكِنَّ ٱلنَّاسَ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy44. አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም:: ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ كَأَن لَّمْ يَلْبَثُوٓا۟ إِلَّا سَاعَةً مِّنَ ٱلنَّهَارِ يَتَعَارَفُونَ بَيْنَهُمْ قَدْ خَسِرَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِلِقَآءِ ٱللَّهِ وَمَا كَانُوا۟ مُهْتَدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያንን ከቀን አንዲትን ሰዓት እንጂ አንዳልቆዩ መስለው በመካከላቸው የሚተዋወቁ ሲሆኑ በምንሰበስባቸው ቀን የሚከሰተውን አስታውስ:: እነዚያ በአላህ መገናኘት ያስተባበሉት ሁሉ በእርግጥ ከሰሩ:: የተመሩም አልነበሩምና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِمَّا نُرِيَنَّكَ بَعْضَ ٱلَّذِى نَعِدُهُمْ أَوْ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِلَيْنَا مَرْجِعُهُمْ ثُمَّ ٱللَّهُ شَهِيدٌ عَلَىٰ مَا يَفْعَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያንም የምናስፈራራባቸውን ነገር ውጤት ከፊሉን (በሕይወትህ ሳለህ) ብናሳይህ (መልካም ነው):: ወይም ሳናሳይህ ብንገድልህ (ጉዳዩ የእኔ ነው):: መመለሻቸው ወደ እኛ ነውና:: ከዚያ አላህ በሚሠሩት ሥራ ላይ ሁሉ አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِكُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولٌ فَإِذَا جَآءَ رَسُولُهُمْ قُضِىَ بَيْنَهُم بِٱلْقِسْطِ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy47. ለሕዝቦችም ሁሉ መልዕክተኛ አላቸው:: መልዕክተኛቸው በመጣ ጊዜ (ሲያስተባብሉት) በመካከላቸው በትክክል ይፈረዳል:: እነርሱም ፍጹም አይበደሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلْوَعْدُ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እውነተኞች ከሆናችሁ የቅጣቱ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُل لَّآ أَمْلِكُ لِنَفْسِى ضَرًّا وَلَا نَفْعًا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُ لِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌ إِذَا جَآءَ أَجَلُهُمْ فَلَا يَسْتَـْٔخِرُونَ سَاعَةً وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለራሴ ጉዳትን ማድረስም ሆነ ጥቅምን ማስከበር አላህ ከሻው በስተቀር አልችልም:: ለህዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው:: ጊዜያቸው በደረሰ ወቅት አንዲትን ሰዓት እንኳን አይቆዩም:: አይቀደሙምም።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَرَءَيْتُمْ إِنْ أَتَىٰكُمْ عَذَابُهُۥ بَيَٰتًا أَوْ نَهَارًا مَّاذَا يَسْتَعْجِلُ مِنْهُ ٱلْمُجْرِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እስቲ ንገሩኝ ቅጣቱ በሌሊት ወይም በቀን ቢመጣባችሁ አጋሪዎቹ የሚያስቸኩላቸው ነገር ምንድን ነው?» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَثُمَّ إِذَا مَا وَقَعَ ءَامَنتُم بِهِۦٓ ءَآلْـَٰٔنَ وَقَدْ كُنتُم بِهِۦ تَسْتَعْجِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy51. «ከዚያም ቅጣቱ በወደቀ ጊዜ በእርሱ አመናችሁበትን? በእርግጥ በእርሱ የምትቻኮሉ የነበራችሁ ስትሆኑ አሁን ነው የምታምኑትን?» ይባላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ قِيلَ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ ذُوقُوا۟ عَذَابَ ٱلْخُلْدِ هَلْ تُجْزَوْنَ إِلَّا بِمَا كُنتُمْ تَكْسِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy52. ከዚያ ለእነዚያ ለበደሉት ሰዎች «ዘውታሪውን ቅጣት ቅመሱ። ትሠሩ የነበራችሁትን እኩይ ተግባር ዋጋ እንጂ ትመነዳላችሁን? (አትመነዱም)።» ይባላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَسْتَنۢبِـُٔونَكَ أَحَقٌّ هُوَ قُلْ إِى وَرَبِّىٓ إِنَّهُۥ لَحَقٌّ وَمَآ أَنتُم بِمُعْجِزِينَ
Amharic Translation - Africa Academy53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «(ከሞት በኋላ መቀስቀስ) እውነት ነውን?» ሲሉ ይጠይቁሃል:: «አዎን! በጌታዬ እምላለሁ እርሱ እውነት ነው:: እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ أَنَّ لِكُلِّ نَفْسٍ ظَلَمَتْ مَا فِى ٱلْأَرْضِ لَٱفْتَدَتْ بِهِۦ وَأَسَرُّوا۟ ٱلنَّدَامَةَ لَمَّا رَأَوُا۟ ٱلْعَذَابَ وَقُضِىَ بَيْنَهُم بِٱلْقِسْطِ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy54. ለበደለች ነፍስ ሁሉ በምድር ላይ ያለው ሀብት ሁሉ የእርሷ ቢሆንላት በእርግጥ ቤዛ ባደረገችው ነበር:: ቅጣቱንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይደብቃሉ (ይገልጻሉ):: በመካከላቸዉም በትክክል ይፈረዳል:: እነርሱም ቅንጣት ያህል አይበደሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَآ إِنَّ لِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ أَلَآ إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy55. አስተውሉ! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: አስተዉሉ! የአላህ የተስፋ ቃል እርግጥ ነው:: ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هُوَ يُحْىِۦ وَيُمِيتُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy56. እርሱ ሕያው ያደርጋል:: ይገድላልም:: ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدْ جَآءَتْكُم مَّوْعِظَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَآءٌ لِّمَا فِى ٱلصُّدُورِ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy57. ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ዘንድ ግሳጼ በደረቶች ውስጥ ላለው በሽታም ፍቱን መድሀኒት፤ ለአማኞችም ብርሃንና እዝነት የሆነ መልዕክት በእርግጥ መጣላችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ بِفَضْلِ ٱللَّهِ وَبِرَحْمَتِهِۦ فَبِذَٰلِكَ فَلْيَفْرَحُوا۟ هُوَ خَيْرٌ مِّمَّا يَجْمَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በአላህ ችሮታና በእዝነቱ ተደሰቱ:: በዚህም ምክንያት ይደሰቱ:: እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት ሁሉ በላጭ ነው።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَرَءَيْتُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ لَكُم مِّن رِّزْقٍ فَجَعَلْتُم مِّنْهُ حَرَامًا وَحَلَٰلًا قُلْ ءَآللَّهُ أَذِنَ لَكُمْ أَمْ عَلَى ٱللَّهِ تَفْتَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy59. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ከሲሳይ ለእናንተ ያወረደው ከእርሱም ከፊሉን እርም ከፊሉን የተፈቀደ ያደረጋችሁትን አያችሁን?» በላቸው:: «አላህ ይህንን ለእናንተ ፈቀደላችሁን? ወይስ በአላህ ላይ ትቀጣጥፋላችሁ?» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا ظَنُّ ٱلَّذِينَ يَفْتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلْكَذِبَ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy60. እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ሰዎች በትንሳኤ ቀን በአላህ ጥርጣሬያቸው ምንድን ነው? አይቀጡም ይመስላቸዋልን? አላህ በሰዎች ላይ ቅጣትን ባለማቻኮል የልግስና ባለቤት ነው:: ግን አብዛኛዎቹ አያመሰግኑትም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا تَكُونُ فِى شَأْنٍ وَمَا تَتْلُوا۟ مِنْهُ مِن قُرْءَانٍ وَلَا تَعْمَلُونَ مِنْ عَمَلٍ إِلَّا كُنَّا عَلَيْكُمْ شُهُودًا إِذْ تُفِيضُونَ فِيهِ وَمَا يَعْزُبُ عَن رَّبِّكَ مِن مِّثْقَالِ ذَرَّةٍ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَا فِى ٱلسَّمَآءِ وَلَآ أَصْغَرَ مِن ذَٰلِكَ وَلَآ أَكْبَرَ إِلَّا فِى كِتَٰبٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በማንኛዉም ነገር ላይ አትሆንም፤ ከእርሱም ከቁርኣን ትንሽም አታነብም፤ ማንኛውንም ሥራ አንተም ሆንክ ሰዎቹ አትሠሩም፤ በገባችሁበት ጊዜ በናንተ ተግባር ላይ ተጠባባቂዎች ብንሆን እንጂ :: በምድርም ሆነ በሰማይ የብናኝ ክብደት ያክል እንኳን ከጌታህ እውቀት አይርቅም:: ከዚያም ያነሰም ሆነ የተለቀ ነገር በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ቢሆን እንጂ የለም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَآ إِنَّ أَوْلِيَآءَ ٱللَّهِ لَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy62. አስተውሉ! የአላህ ወዳጆች ፍርሀት የለባቸዉም። አይተክዙምም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَكَانُوا۟ يَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy63. እነርሱም እነዚያ ያመኑትና አላህን የሚፈሩት ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَهُمُ ٱلْبُشْرَىٰ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَفِى ٱلْـَٔاخِرَةِ لَا تَبْدِيلَ لِكَلِمَٰتِ ٱللَّهِ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy64. ለእነርሱ በቅርቢቱ ህይወትም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ብስራት አለላቸው:: የአላህ ቃል አይለወጥም:: ይህ እርሱ ታላቅ እድል (ስኬታማነት) ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا يَحْزُنكَ قَوْلُهُمْ إِنَّ ٱلْعِزَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ንግግራቸዉም አያሳዝንህ:: ኃይል በሙሉ የአላህ ብቻ ነውና:: እርሱም ሰሚውና ሁሉን አዋቂው ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَآ إِنَّ لِلَّهِ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا يَتَّبِعُ ٱلَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ شُرَكَآءَ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنْ هُمْ إِلَّا يَخْرُصُونَ
Amharic Translation - Africa Academy66. አስተውሉ! በሰማያት ያሉትና በምድርም ያሉት ሁሉ በእርግጥ የአላህ ናቸው፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ ተጋሪዎችን የሚጠሩ ምንን ይከተላሉ? ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ አይደሉም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِتَسْكُنُوا۟ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبْصِرًا إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَسْمَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy67. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት ጨለማ ቀንንም ልትሠሩበት ብርሃን ያደረገላችሁ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ህዝቦች ሁሉ በእርግጥ ብዙ ተአምራት አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًا سُبْحَٰنَهُۥ هُوَ ٱلْغَنِىُّ لَهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ إِنْ عِندَكُم مِّن سُلْطَٰنٍۭ بِهَٰذَآ أَتَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy68. «አላህ ልጅን ወለደ።» አሉ። ከሚሉት ሁሉ ጥራት ተገባው:: እርሱ በራሱ ተብቃቂ ነው:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: እናንተ ዘንድ በዚህ በምትሉት ምንም አስረጂ የላችሁም:: በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَفْتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلْكَذِبَ لَا يُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy69. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ሰዎች ፈጽሞ አይድኑም።» በላቸው
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَتَٰعٌ فِى ٱلدُّنْيَا ثُمَّ إِلَيْنَا مَرْجِعُهُمْ ثُمَّ نُذِيقُهُمُ ٱلْعَذَابَ ٱلشَّدِيدَ بِمَا كَانُوا۟ يَكْفُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy70. እነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ጥቂት ጊዜ ይጠቀሙና ከዚያም መመለሻቸው ወደ እኛ ነው:: ከዚያም ይክዱ በነበሩበት ምክንያት ብርቱን ቅጣት እናቀምሳቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ نُوحٍ إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِۦ يَٰقَوْمِ إِن كَانَ كَبُرَ عَلَيْكُم مَّقَامِى وَتَذْكِيرِى بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَعَلَى ٱللَّهِ تَوَكَّلْتُ فَأَجْمِعُوٓا۟ أَمْرَكُمْ وَشُرَكَآءَكُمْ ثُمَّ لَا يَكُنْ أَمْرُكُمْ عَلَيْكُمْ غُمَّةً ثُمَّ ٱقْضُوٓا۟ إِلَىَّ وَلَا تُنظِرُونِ
Amharic Translation - Africa Academy71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የኑህንም ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው:: ለህዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውሱ «ህዝቦቼ ሆይ! በእናንተ ውስጥ ብዙን ጊዜ መቆየቴ የአላህንም ተዓምራት ለእናንተ ማስታወሴ በእናንተ ላይ የከበደ ቢሆንባችሁም በአላህ ላይ ተጠግቻለሁ:: ነገራችሁንም ከምታጋሯቸው ጣኦታት ጋር ሆናችሁ እስቲ ቁረጡ:: ከዚያም ነገራችሁ በእናንተ ላይ ድብቅ አይሁን ግለጹት:: ከዚያም የሻችሁትን ወደ እኔ አድርሱ:: ጊዜም አትስጡኝ (ከምንም አልቆጥራችሁም)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِن تَوَلَّيْتُمْ فَمَا سَأَلْتُكُم مِّنْ أَجْرٍ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ ٱلْمُسْلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy72. «ብትሸሹም (አትጎዱኝም::) ከምንዳ ምንንም አለመንኳችሁምና:: ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለምና:: ከሙስሊሞች እንድሆንም ታዝዣለሁ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَكَذَّبُوهُ فَنَجَّيْنَٰهُ وَمَن مَّعَهُۥ فِى ٱلْفُلْكِ وَجَعَلْنَٰهُمْ خَلَٰٓئِفَ وَأَغْرَقْنَا ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا فَٱنظُرْ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلْمُنذَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy73. አስተባበሉት እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች በታንኳይቱ ውስጥ አዳንናቸው:: ለጠፉት ምትኮች አደረግናቸው:: እነዚያንም በአናቅጻችን ያስተባበሉትን አሰመጥን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተስፈራሩት ህዝቦች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበር እስቲ ተመልከት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ بَعَثْنَا مِنۢ بَعْدِهِۦ رُسُلًا إِلَىٰ قَوْمِهِمْ فَجَآءُوهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَمَا كَانُوا۟ لِيُؤْمِنُوا۟ بِمَا كَذَّبُوا۟ بِهِۦ مِن قَبْلُ كَذَٰلِكَ نَطْبَعُ عَلَىٰ قُلُوبِ ٱلْمُعْتَدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy74. ከዚያም ከእርሱ በኋላ መልዕክተኞችን ወደየ ህዝቦቻቸው ላክን:: በግልጽ ማስረጃዎችም መጡላቸው:: ከመላካቸው በፊት ባስተባበሉት ነገር የሚያምኑ አልሆኑም:: ልክ እንደዚሁ በወሰን አላፊዎች ልቦች ላይ እናትማለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ بَعَثْنَا مِنۢ بَعْدِهِم مُّوسَىٰ وَهَٰرُونَ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَإِي۟هِۦ بِـَٔايَٰتِنَا فَٱسْتَكْبَرُوا۟ وَكَانُوا۟ قَوْمًا مُّجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy75. ከዚያም ከእነርሱ በኋላ ሙሳንና ሃሩንን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቱ በተአምራታችን ላክን:: ኮሩም:: ትእቢተኞች ህዝቦችም ነበሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا جَآءَهُمُ ٱلْحَقُّ مِنْ عِندِنَا قَالُوٓا۟ إِنَّ هَٰذَا لَسِحْرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy76. ከእኛም ዘንድ እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምት ነው።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ مُوسَىٰٓ أَتَقُولُونَ لِلْحَقِّ لَمَّا جَآءَكُمْ أَسِحْرٌ هَٰذَا وَلَا يُفْلِحُ ٱلسَّٰحِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy77. ሙሳ አለ፡- «እውነቱን በመጣላችሁ ጊዜ ድግምተኞች የማይድኑ ሲኾኑ (እርሱ ድግምት ነው) ትላላችሁን?ይህ ድግምት ነውን?»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوٓا۟ أَجِئْتَنَا لِتَلْفِتَنَا عَمَّا وَجَدْنَا عَلَيْهِ ءَابَآءَنَا وَتَكُونَ لَكُمَا ٱلْكِبْرِيَآءُ فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا نَحْنُ لَكُمَا بِمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy78. እነርሱም «አባቶቻችንን ካገኘንበት ሃይማኖት ልታዞሩንና በምድር ውስጥ ለእናንተም ኩራት ሹመት ልትኖራችሁ መጣህብን:: እኛ ለእናንተ በፍጹም አማኞች አይደለንም።» አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ فِرْعَوْنُ ٱئْتُونِى بِكُلِّ سَٰحِرٍ عَلِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy79. ፈርዖን፡- «አዋቂ ድግምተኛን ሁሉ አምጡልኝ።» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا جَآءَ ٱلسَّحَرَةُ قَالَ لَهُم مُّوسَىٰٓ أَلْقُوا۟ مَآ أَنتُم مُّلْقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy80. ድግምተኞቹ በመጡ ጊዜም ሙሳ ለእነርሱ፡- «እናንተ የምትጥሉትን ነገር ጣሉ።» አላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّآ أَلْقَوْا۟ قَالَ مُوسَىٰ مَا جِئْتُم بِهِ ٱلسِّحْرُ إِنَّ ٱللَّهَ سَيُبْطِلُهُۥٓ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُصْلِحُ عَمَلَ ٱلْمُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy81. በጣሉም ጊዜ ሙሳ፡- «ያ በእርሱ የመጣችሁበት ነገር ድግምት ነው:: አላህ በእርግጥ ያፈርሰዋል:: አላህ የአጥፊዎችን ሥራ ፈጽሞ አያበጅምና።» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيُحِقُّ ٱللَّهُ ٱلْحَقَّ بِكَلِمَٰتِهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْمُجْرِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy82. አላህም ከሓዲያን ቢጠሉም እውነትን በቃላቱ ያረጋግጣል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَآ ءَامَنَ لِمُوسَىٰٓ إِلَّا ذُرِّيَّةٌ مِّن قَوْمِهِۦ عَلَىٰ خَوْفٍ مِّن فِرْعَوْنَ وَمَلَإِي۟هِمْ أَن يَفْتِنَهُمْ وَإِنَّ فِرْعَوْنَ لَعَالٍ فِى ٱلْأَرْضِ وَإِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلْمُسْرِفِينَ
Amharic Translation - Africa Academy83. ለሙሳም ከፈርዖንና ከሹማምንቶቻቸው ማሰቃየትን በመፍራት ከወገኖቹ ጥቂት ትውልዶች ብቻ እንጂ አላመኑለትም:: ፈርዖንም በምድር ላይ በእርግጥ ይኮራ ነበር። እርሱም በእርግጥ ወሰን ካለፉት ነበር።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ مُوسَىٰ يَٰقَوْمِ إِن كُنتُمْ ءَامَنتُم بِٱللَّهِ فَعَلَيْهِ تَوَكَّلُوٓا۟ إِن كُنتُم مُّسْلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy84. ሙሳም፡- «ህዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በእርሱ ላይ ብቻ ተጠጉ:: ታዛዦች እንደ ሆናችሁም በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ።» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَقَالُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ تَوَكَّلْنَا رَبَّنَا لَا تَجْعَلْنَا فِتْنَةً لِّلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy85. አሉ፡- «በአላህ ላይ ተጠጋን:: ጌታችን ሆይ! ለበደለኞች ህዝቦች መፈተኛ አታድርገን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَجِّنَا بِرَحْمَتِكَ مِنَ ٱلْقَوْمِ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy86. «በእዝነትህም ከከሓዲያን ህዝቦች ግፍ አድነን።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَوْحَيْنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰ وَأَخِيهِ أَن تَبَوَّءَا لِقَوْمِكُمَا بِمِصْرَ بُيُوتًا وَٱجْعَلُوا۟ بُيُوتَكُمْ قِبْلَةً وَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَبَشِّرِ ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy87. ወደ ሙሳና ወደ ወንድሙ፡ «ለህዝቦቻችሁ በግብጽ ውስጥ ቤቶችን ሥሩ:: ቤቶቻችሁንም መስገጃ አድርጉ:: ሶላትንም በደንቡ ስገዱ:: ምዕመናኖቹንም አብስር።» ስንል ላክን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ مُوسَىٰ رَبَّنَآ إِنَّكَ ءَاتَيْتَ فِرْعَوْنَ وَمَلَأَهُۥ زِينَةً وَأَمْوَٰلًا فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا رَبَّنَا لِيُضِلُّوا۟ عَن سَبِيلِكَ رَبَّنَا ٱطْمِسْ عَلَىٰٓ أَمْوَٰلِهِمْ وَٱشْدُدْ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَلَا يُؤْمِنُوا۟ حَتَّىٰ يَرَوُا۟ ٱلْعَذَابَ ٱلْأَلِيمَ
Amharic Translation - Africa Academy88. ሙሳም: «ጌታችን ሆይ! አንተ ለፈርዖንና ለሹሞቹ በቅርቢቱ ህይወት ጌጥን ብዙ ገንዘቦችንም በእርግጥ ሰጠህ:: ጌታችን ሆይ! ከመንገድህ ያሳስቱ ዘንድ ሰጠሃቸው:: ጌታችን ሆይ! ገንዘቦቻቸውን አጥፋ:: በልቦቻቸዉም ላይ አትም:: አሳማሚን ቅጣት አስከሚያዩ አያምኑምና።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ قَدْ أُجِيبَت دَّعْوَتُكُمَا فَٱسْتَقِيمَا وَلَا تَتَّبِعَآنِّ سَبِيلَ ٱلَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy89. (አላህም) ፡- «ጸሎታችሁ ተሰምታለች:: ቀጥም በሉ:: የእነዚያን የማያውቁትን ሰዎች መንገድ አትከተሉ።» አላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَٰوَزْنَا بِبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱلْبَحْرَ فَأَتْبَعَهُمْ فِرْعَوْنُ وَجُنُودُهُۥ بَغْيًا وَعَدْوًا حَتَّىٰٓ إِذَآ أَدْرَكَهُ ٱلْغَرَقُ قَالَ ءَامَنتُ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱلَّذِىٓ ءَامَنَتْ بِهِۦ بَنُوٓا۟ إِسْرَٰٓءِيلَ وَأَنَا۠ مِنَ ٱلْمُسْلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy90. የኢስራኢል ልጆችን ባህሩን አሳለፍናቸው:: ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው:: የመስመጥ አደጋ ባገኘውም ጊዜ «አመንኩ:: እነሆ ከዚያ የእሥራኤል ልጆች ካመኑበት አምላክ በስተቀር ሌላ የእውነት አምላክ የለም:: እኔም ከታዛዦቹ (ሙስሊሞች) አንዱ ነኝ።» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ءَآلْـَٰٔنَ وَقَدْ عَصَيْتَ قَبْلُ وَكُنتَ مِنَ ٱلْمُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy91. «ከአሁን በፊት በእርግጥ ያመጽክና ከአጥፊዎችም የነበርክ ስትሆን አሁን ታምናለህን?» ተባለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱلْيَوْمَ نُنَجِّيكَ بِبَدَنِكَ لِتَكُونَ لِمَنْ خَلْفَكَ ءَايَةً وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ ٱلنَّاسِ عَنْ ءَايَٰتِنَا لَغَٰفِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy92. እናም ዛሬ ከኋላህ ለሚመጡ ትውልዶች ተዓምር ትሆን ዘንድ አካልህን (ከባሕሩ) እናወጣሀለን ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዐምሮቻችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ بَوَّأْنَا بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ مُبَوَّأَ صِدْقٍ وَرَزَقْنَٰهُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ فَمَا ٱخْتَلَفُوا۟ حَتَّىٰ جَآءَهُمُ ٱلْعِلْمُ إِنَّ رَبَّكَ يَقْضِى بَيْنَهُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُوا۟ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy93. የኢስራኢልን ልጆችም ምስጉንን ስፍራ በእርግጥ አሰፈርናቸው:: ከመልካም ሲሳዮችም ሰጠናቸው:: እውቀትም እስከመጣላቸው ድረስ አልተለያዩም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በእርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው ይፈርዳል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِن كُنتَ فِى شَكٍّ مِّمَّآ أَنزَلْنَآ إِلَيْكَ فَسْـَٔلِ ٱلَّذِينَ يَقْرَءُونَ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكَ لَقَدْ جَآءَكَ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُمْتَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)) ወደ አንተ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ከሆንክ እነዚያን ካንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ሰዎች ጠይቅ:: እውነቱ ከጌታህ ዘንድ መጥቶልሃል:: እናም ከተጠራጣሪዎች አትሁን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَتَكُونَ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy95. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነዚያ የአላህን አናቅጽ ካስተባበሉት ሰዎች አትሁን:: ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ حَقَّتْ عَلَيْهِمْ كَلِمَتُ رَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ የጌታህ ቃል የተረጋገጠባቸው ሰዎች አያምኑም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ جَآءَتْهُمْ كُلُّ ءَايَةٍ حَتَّىٰ يَرَوُا۟ ٱلْعَذَابَ ٱلْأَلِيمَ
Amharic Translation - Africa Academy97. ተዓምራት ሁሉ ቢመጣላቸዉም አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ ድረስ(አያምኑም)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَوْلَا كَانَتْ قَرْيَةٌ ءَامَنَتْ فَنَفَعَهَآ إِيمَٰنُهَآ إِلَّا قَوْمَ يُونُسَ لَمَّآ ءَامَنُوا۟ كَشَفْنَا عَنْهُمْ عَذَابَ ٱلْخِزْىِ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَمَتَّعْنَٰهُمْ إِلَىٰ حِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy98. ከነብዩ ዩኑስ በፊት ካለፉት ከተሞች ያመነችና እምነት የጠቀማት ከተማ ለምን አልኖረችም? ግን የነብዩ ዩኑስ ህዝቦች ባመኑ ጊዜ በቅርቢቱ ህይወት የውርደትን ቅጣት ከእነርሱ ላይ አነሳንላቸው:: እስከ ጊዜም ድረስ አጣቀምናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ شَآءَ رَبُّكَ لَـَٔامَنَ مَن فِى ٱلْأَرْضِ كُلُّهُمْ جَمِيعًا أَفَأَنتَ تُكْرِهُ ٱلنَّاسَ حَتَّىٰ يَكُونُوا۟ مُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በሻ ኖሮ በምድር ያሉት ሁሉ በአንድ የተሰበሰቡ ሆነው ባመኑ ነበር:: ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲሆኑ ታስገድዳለህን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا كَانَ لِنَفْسٍ أَن تُؤْمِنَ إِلَّا بِإِذْنِ ٱللَّهِ وَيَجْعَلُ ٱلرِّجْسَ عَلَى ٱلَّذِينَ لَا يَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy100. ማንኛዋም ነፍስ በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ የምታምን አይደለችም:: ከእነዚያ በማያውቁት ላይ ርክሰትን ያደርጋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلِ ٱنظُرُوا۟ مَاذَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا تُغْنِى ٱلْـَٔايَٰتُ وَٱلنُّذُرُ عَن قَوْمٍ لَّا يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy101. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉትን ተዓምራት ተመልከቱ።» በላቸው:: ሆኖም ተዓምራትና አስፈራሪዎች ለማያምኑ ህዝቦች ምንም አይጠቅሙም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَهَلْ يَنتَظِرُونَ إِلَّا مِثْلَ أَيَّامِ ٱلَّذِينَ خَلَوْا۟ مِن قَبْلِهِمْ قُلْ فَٱنتَظِرُوٓا۟ إِنِّى مَعَكُم مِّنَ ٱلْمُنتَظِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy102. የእነዚያን ከእነርሱ በፊት ያለፉትን ህዝቦች ቀኖች ብጤ ያገኟቸውን አይነት ቀናትን እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተም ተጠባበቁ እኔም ከናንተው ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ نُنَجِّى رُسُلَنَا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كَذَٰلِكَ حَقًّا عَلَيْنَا نُنجِ ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy103. መልዕክተኞቻችንንና እነዚያን ያመኑትንም ከጭንቅ ሁሉ እናድናለን:: እንደዚሁም ምእምናንን (ከጭንቅ ሁሉ) እናድናለን፡፡ ይህ በእኛ ላይ ተረጋገጠ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِن كُنتُمْ فِى شَكٍّ مِّن دِينِى فَلَآ أَعْبُدُ ٱلَّذِينَ تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِنْ أَعْبُدُ ٱللَّهَ ٱلَّذِى يَتَوَفَّىٰكُمْ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy104. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! ከእኔ ሃይማኖት በመጠራጠር ውስጥ ከሆናችሁ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አልገዛም:: ይልቁንም ያንን የሚገድላችሁን አላህን ብቻ እገዛለሁ:: ከትክክለኛ አማኞች እንድሆንም ታዝዣለሁ።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنْ أَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ
Amharic Translation - Africa Academy105. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ፊትህን ወደ ቀጥታው መንገድ ያዘነበልክ ስትሆን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ:: ከአጋሪዎቹም አትሁን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَدْعُ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكَ وَلَا يَضُرُّكَ فَإِن فَعَلْتَ فَإِنَّكَ إِذًا مِّنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ በስተቀር የማይጠቅምህንና የማይጎህዳን አትገዛ:: ይህን ብትሠራ ግን ያን ጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ (ተብያለሁ» በላቸው)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن يَمْسَسْكَ ٱللَّهُ بِضُرٍّ فَلَا كَاشِفَ لَهُۥٓ إِلَّا هُوَ وَإِن يُرِدْكَ بِخَيْرٍ فَلَا رَآدَّ لِفَضْلِهِۦ يُصِيبُ بِهِۦ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ وَهُوَ ٱلْغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ጉዳትን ቢያደርስብህ ከእርሱ ሌላ ለእርሱ ገላጭ የለዉም:: በጎ ነገርም ቢሻልህ ለችሮታው መላሽ ማንም የለም:: ከባሮቹ የሚሻውን በእርሱ ይለይበታል:: እርሱም መሓሪውና አዛኙ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدْ جَآءَكُمُ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ فَمَنِ ٱهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِى لِنَفْسِهِۦ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا وَمَآ أَنَا۠ عَلَيْكُم بِوَكِيلٍ
Amharic Translation - Africa Academy108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እውነቱ ከጌታችሁ በእርግጥ መጣላችሁ:: በእርሱ የተመራም የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው:: የተሳሳተም የሚሳሳተው ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው:: እኔ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱتَّبِعْ مَا يُوحَىٰٓ إِلَيْكَ وَٱصْبِرْ حَتَّىٰ يَحْكُمَ ٱللَّهُ وَهُوَ خَيْرُ ٱلْحَٰكِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ አንተ የሚወረደውን ነገር ተከተል:: አላህ በእነርሱና ባንተ መካከል ባለው ጉዳይ ላይ እስከሚፈርድ ድረስ ታገሥ:: እርሱም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ፈራጅ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→