ٱلتَّٰٓئِبُونَ ٱلْعَٰبِدُونَ ٱلْحَٰمِدُونَ ٱلسَّٰٓئِحُونَ ٱلرَّٰكِعُونَ ٱلسَّٰجِدُونَ ٱلْـَٔامِرُونَ بِٱلْمَعْرُوفِ وَٱلنَّاهُونَ عَنِ ٱلْمُنكَرِ وَٱلْحَٰفِظُونَ لِحُدُودِ ٱللَّهِ وَبَشِّرِ ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy112. እነርሱ ተጸፃቾች፤ ተገዢዎች፤ አመስጋኞች፤ ፆመኞች፤ (በሶላት) አጎንባሾች፤ በግንባር ተደፊዎች፤ በበጎ ሥራ አዛዦች፤ ከክፉ ከልካዮች እና የአላህንም ሕግጋት ጠባቂዎች ናቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትክክለኛ አማኞችንም አብስር::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(እነርሱ) ተጸጻቺዎች፣ ተገዢዎች፣ አመስጋኞች፣ ጿሚዎች፣ አጎንባሾች፣ በግንባር ተደፊዎች፣ በበጎ ሥራ አዛዦች ከክፉም ከልካዮች፣ የአላህንም ሕግጋት ጠባቂዎች ናቸው ምእምናንንም አብስር፡፡