caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ At-Tawba፣ አንቀጽ 37

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 113 · 9:37

إِنَّمَا ٱلنَّسِىٓءُ زِيَادَةٌ فِى ٱلْكُفْرِ يُضَلُّ بِهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ يُحِلُّونَهُۥ عَامًا وَيُحَرِّمُونَهُۥ عَامًا لِّيُوَاطِـُٔوا۟ عِدَّةَ مَا حَرَّمَ ٱللَّهُ فَيُحِلُّوا۟ مَا حَرَّمَ ٱللَّهُ زُيِّنَ لَهُمْ سُوٓءُ أَعْمَٰلِهِمْ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy37. የአንዱን ወር ክብር ወደ ሌላው ማዘግየት በክህደት ላይ ክህደትን መጨመር ነው:: በዚህ ተግባር ላይ እነዚያ በአላህ የካዱት (ሰዎች) ይሳሳቱበታል:: በአንደኛው ዓመት የተፈቀደ ያደርጉታል:: በሌላው ዓመት ደግሞ ያወግዙታል:: ይህም አላህ ያከበራቸውን ወሮች ቁጥር ሊሞሉበትና አላህ እርም ያደረገውን ደግሞ የተፈቀደ ሊያደርጉበት ነው:: መጥፎ ሥራዎቻቸው ለእነርሱ ተዋበላቸው:: አላህ ከሓዲያን ህዝቦችን ወደ ቀናው መንገድ አይመራም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየአንዱን ወር ክብር ወደ ሌላው ማዘግየት በክህደት ላይ (ክህደትን) መጨመር ብቻ ነው፡፡ በእርሱ እነዚያ የካዱት ሰዎች ይሳሳቱበታል፡፡ በአንድ ዓመት የተፈቀደ ያደርጉታል፡፡ በሌላው ዓመትም ያወግዙታል፡፡ (ይህ) አላህ ያከበራቸውን ወሮች ቁጥር ሊያስተካክሉ፣ አላህም እርም ያደረገውን የተፈቀደ ሊያደርጉ ነው፡፡ የሥራዎቻቸው መጥፎው ለነርሱ ተዋበላቸው፡፡ አላህም ከሓዲያን ሕዝቦችን አይመራም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70