يَعْتَذِرُونَ إِلَيْكُمْ إِذَا رَجَعْتُمْ إِلَيْهِمْ قُل لَّا تَعْتَذِرُوا۟ لَن نُّؤْمِنَ لَكُمْ قَدْ نَبَّأَنَا ٱللَّهُ مِنْ أَخْبَارِكُمْ وَسَيَرَى ٱللَّهُ عَمَلَكُمْ وَرَسُولُهُۥ ثُمَّ تُرَدُّونَ إِلَىٰ عَٰلِمِ ٱلْغَيْبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነርሱ በተመለሳችሁ ጊዜ ምክንያቶቻቸውን ያቀርቡላችኋል:: «አታመካኙ እናንተን ፈጽሞ አናምንም:: አላህ ከወሬዎቻችሁ አስቀድሞ ነግሮናልና:: አላህና መልዕክተኛው ሥራችሁን ያያሉ:: ከዚያ ሩቅንና ቅርብን ሁሉ አዋቂ ወደ ሆነው አላህ ትመለሳላችሁ:: ወዲያዉም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል።» በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወደእነሱ በተመለሳችሁ ጊዜ ምክንያታቸውን ያቀርቡላችኋል፡፡ አታመካኙ፤ እናንተን ፈጽሞ አናምንም፡፡ አላህ ከወሬዎቻችሁ በእርግጥ ነግሮናልና፡፡ አላህም ሥራችሁን በእርግጥ ያያል፡፡ መልክተኛውም (እንደዚሁ)፤ ከዚያም ሩቅንና ቅርብን ሁሉ ዐዋቂ ወደ ኾነው (አላህ) ትመለሳላችሁ ወዲያውም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል በላቸው፡፡