فَرِحَ ٱلْمُخَلَّفُونَ بِمَقْعَدِهِمْ خِلَٰفَ رَسُولِ ٱللَّهِ وَكَرِهُوٓا۟ أَن يُجَٰهِدُوا۟ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَقَالُوا۟ لَا تَنفِرُوا۟ فِى ٱلْحَرِّ قُلْ نَارُ جَهَنَّمَ أَشَدُّ حَرًّا لَّوْ كَانُوا۟ يَفْقَهُونَ
Amharic Translation - Africa Academy81. እነዚያ ከዘመቻ የቀሩት ሰዎች ከአላህ መልዕክተኛ በኋላ ተገንጥለው በመቀመጣቸው ተደሰቱ:: በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው መታገልን ጠሉ:: ለሌሎችም «በሐሩር አትሂዱ» አሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የገሀነም እሳት ትኩሳት በጣም ከዚህ የበረታ ነው።» በላቸው:: እናም የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ ከዘመቻው አይቀሩም ነበር::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ ከዘመቻ የቀሩት ከአላህ መልክተኛ በኋላ በመቀመጣቸው ተደሰቱ፡፡ በአላህም መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው መታገልን ጠሉ፡፡ «በሐሩር አትኺዱ» አሉም፡፡ «የገሀነም እሳት ተኳሳነቱ በጣም የበረታ ነው» በላቸው፡፡ የሚያውቁ ቢኾኑ ኖሮ (አይቀሩም ነበር)፡፡