ٱسْتَغْفِرْ لَهُمْ أَوْ لَا تَسْتَغْفِرْ لَهُمْ إِن تَسْتَغْفِرْ لَهُمْ سَبْعِينَ مَرَّةً فَلَن يَغْفِرَ ٱللَّهُ لَهُمْ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَفَرُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْفَٰسِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱ ምሕረትን ብትለምንላቸዉም ወይም ባትለምንላቸው ሁሉም እኩል ነው:: ለእነርሱ ሰባ ጊዜ ምህረትን ብትለምንላቸው እንኳን አላህ በፍጹም አይምራቸዉምና:: ምክንያቱም እነርሱ በአላህና በመልዕክተኛው ክደዋልና:: አላህ አመጸኞች ህዝቦችን አያቀናም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለእነርሱ ምሕረትን ለምንላቸው፤ ወይም ለእነሱ ምሕረትን አትለምንላቸው (እኩል ነው)፡፡ ለእነሱ ሰባ ጊዜ ምሕረትን ብትለምንላቸው አላህ ለነሱ በፍጹም አይምርም፡፡ ይህ እነርሱ አላህና መልክተኛውን በመካዳቸው ነው፡፡ አላህም አመጸኞች ሕዝቦችን አያቀናም፡፡