يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّمَا ٱلْمُشْرِكُونَ نَجَسٌ فَلَا يَقْرَبُوا۟ ٱلْمَسْجِدَ ٱلْحَرَامَ بَعْدَ عَامِهِمْ هَٰذَا وَإِنْ خِفْتُمْ عَيْلَةً فَسَوْفَ يُغْنِيكُمُ ٱللَّهُ مِن فَضْلِهِۦٓ إِن شَآءَ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ حَكِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy28. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው:: እናም ከዚህ ዓመታቸው በኋላ ወደ ተከበረው መስጊድ እንዳይቀርቡ። ድህነትንም ብትፈሩ አላህ ቢፈልግ ከችሮታው በእርግጥ ያከብራችኋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህም ዓመታቸው በኋላ የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ፡፡ ድኽነትንም ብትፈሩ አላህ ቢሻ ከችሮታው በእርግጥ ያከብራችኋል፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡