caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ At-Tawba፣ አንቀጽ 40

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 113 · 9:40

إِلَّا تَنصُرُوهُ فَقَدْ نَصَرَهُ ٱللَّهُ إِذْ أَخْرَجَهُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ثَانِىَ ٱثْنَيْنِ إِذْ هُمَا فِى ٱلْغَارِ إِذْ يَقُولُ لِصَٰحِبِهِۦ لَا تَحْزَنْ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَنَا فَأَنزَلَ ٱللَّهُ سَكِينَتَهُۥ عَلَيْهِ وَأَيَّدَهُۥ بِجُنُودٍ لَّمْ تَرَوْهَا وَجَعَلَ كَلِمَةَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ٱلسُّفْلَىٰ وَكَلِمَةُ ٱللَّهِ هِىَ ٱلْعُلْيَا وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy40. (ሙስሊሞች ሆይ!) ነብዩ ሙሐመድን ባትረዱት እነዚያ በአላህ የካዱት ህዝቦች የሁለት ሰዎች ሁለተኛ ሆኖ ከመካ ባስወጡት ጊዜ አላህ ረድቶታል:: ሁለቱም በዋሻው ሳሉ ለጓደኛው «አትዘን አላህ ከእኛ ጋር ነውና» ባለ ጊዜ አላህ እርጋታውን በእርሱ ላይ አወረደ:: ባላያችኋቸዉም ሰራዊት አበረታው:: የእነዚያን በአላህ የካዱትን ሰዎች ቃል የበታች አደረገ:: የአላህ ቃል ግን የበላይ ነው:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(ነቢዩን) ባትረዱት እነዚያ የካዱት ሕዝቦች የሁለት (ሰዎች) ሁለተኛ ኾኖ (ከመካ) ባወጡት ጊዜ አላህ በእርግጥ ረድቶታል፡፡ ሁለቱም በዋሻው ሳሉ ለጓደኛው አትዘን አላህ ከእኛ ጋር ነውና ባለ ጊዜ አላህም መረጋጋትን በእርሱ ላይ አወረደ፡፡ ባላያችኋቸውም ሰራዊት አበረታው፡፡ የእነዚያንም የካዱትን ሰዎች ቃል ዝቅተኛ አደረገ፡፡ የአላህም ቃል እርሷ ከፍተኛ ናት፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70