يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَتَّخِذُوٓا۟ ءَابَآءَكُمْ وَإِخْوَٰنَكُمْ أَوْلِيَآءَ إِنِ ٱسْتَحَبُّوا۟ ٱلْكُفْرَ عَلَى ٱلْإِيمَٰنِ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy23. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አባቶቻችሁንና ወንድሞቻችሁን ክህደትን ከእምነት አብልጠው ከወደዱ ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዟቸው:: ከናንተ መካከል እነርሱን ወዳጅ የሚያደርጓቸው ሁሉ በዳዮች ማለት እነርሱው ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! አባቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ክህደትን ከእምነት አብልጠው ቢወዱ ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ወዳጅ የሚያደርጋቸው እነዚያ እነሱ በዳዮች ናቸው፤