وَمِنْهُمُ ٱلَّذِينَ يُؤْذُونَ ٱلنَّبِىَّ وَيَقُولُونَ هُوَ أُذُنٌ قُلْ أُذُنُ خَيْرٍ لَّكُمْ يُؤْمِنُ بِٱللَّهِ وَيُؤْمِنُ لِلْمُؤْمِنِينَ وَرَحْمَةٌ لِّلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنكُمْ وَٱلَّذِينَ يُؤْذُونَ رَسُولَ ٱللَّهِ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) ከአስመሳዮች መካከል ነብዩ ሙሐመድን የሚያስቸግሩና «እርሱ እኮ ወሬ ሰሚ ነው።» የሚሉ አሉ። «ለእናንተ የበጎ ወሬ ሰሚ ነው:: በአላህ ያምናል:: አማኞችንም ያምናቸዋል:: ከናንተ መካከል ለእነዚያ በአላህ ላመኑት ሰዎችም እዝነት ነው።» በላቸው:: እነዚያ የአላህን መልዕክተኛ የሚያስቸግሩ ሰዎች ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከእነሱም (ከመናፍቃን) እነዚያ ነቢዩን የሚያሰቃዩ «እርሱም ጆሮ ነው» (ወሬ ሰሚ ነው) የሚሉ አልሉ፡፡ በላቸው ለእናንተ የበጎ (ወሬ) ሰሚ ነው፡፡ በአላህ ያምናል፣ ምእምናንንም ያምናቸዋል፣ ከእናንተም ውስጥ ለነዚያ ላመኑት እዝነት ነው፡፡ እነዚያም የአላህን መልክተኛ የሚያሰቃዩ ለነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡