caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Fajr الفجر

30 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 10

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ وَٱلْفَجْرِ

Amharic Translation - Africa Academy1. በጎህ፤ እምላለሁ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَيَالٍ عَشْرٍ

Amharic Translation - Africa Academy2. በአስሩ ሌሊቶችም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلشَّفْعِ وَٱلْوَتْرِ

Amharic Translation - Africa Academy3. በጥንዱም በነጠላዉም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّيْلِ إِذَا يَسْرِ

Amharic Translation - Africa Academy4. በሌሊቱም በሚጓዝበት ጊዜ እምላለሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَلْ فِى ذَٰلِكَ قَسَمٌ لِّذِى حِجْرٍ

Amharic Translation - Africa Academy5. በዚህ መሀላ ለባለ አእምሮ ታላቅ መሀላ የለበትምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِعَادٍ

Amharic Translation - Africa Academy6. ጌታህ በዓድ ህዝቦች ላይ እንዴት እንደሰራ አላወክምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِرَمَ ذَاتِ ٱلْعِمَادِ

Amharic Translation - Africa Academy7. በባለ ረዣዥሚቱ አዕማድ ኢረም ላይም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّتِى لَمْ يُخْلَقْ مِثْلُهَا فِى ٱلْبِلَٰدِ

Amharic Translation - Africa Academy8. በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በሆነችው፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَثَمُودَ ٱلَّذِينَ جَابُوا۟ ٱلصَّخْرَ بِٱلْوَادِ

Amharic Translation - Africa Academy9. በእነዚያ (በሸለቆዎች) ቋጥኝን የቦረቦሩ በሆኑት ሰሙድም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفِرْعَوْنَ ذِى ٱلْأَوْتَادِ

Amharic Translation - Africa Academy10. ባለ ችካሎች በሆነው ፈርዖንም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ طَغَوْا۟ فِى ٱلْبِلَٰدِ

Amharic Translation - Africa Academy11. በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሰሩ (በሆኑትም ላይ)፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَكْثَرُوا۟ فِيهَا ٱلْفَسَادَ

Amharic Translation - Africa Academy12. በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በሆኑት (እንዴት እንደሰራ አታውቅምን?)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَصَبَّ عَلَيْهِمْ رَبُّكَ سَوْطَ عَذَابٍ

Amharic Translation - Africa Academy13. በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ رَبَّكَ لَبِٱلْمِرْصَادِ

Amharic Translation - Africa Academy14. ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَمَّا ٱلْإِنسَٰنُ إِذَا مَا ٱبْتَلَىٰهُ رَبُّهُۥ فَأَكْرَمَهُۥ وَنَعَّمَهُۥ فَيَقُولُ رَبِّىٓ أَكْرَمَنِ

Amharic Translation - Africa Academy15. የሰው ልጅ ጌታው በሞከረው ጊዜ ባከበረውና ባጣቀመው ጊዜ ጌታየ አከበረኝ (አበለጠኝ) ይላል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمَّآ إِذَا مَا ٱبْتَلَىٰهُ فَقَدَرَ عَلَيْهِ رِزْقَهُۥ فَيَقُولُ رَبِّىٓ أَهَٰنَنِ

Amharic Translation - Africa Academy16. በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበበት (ጊዜ) እንዲሁ ጌታየ አሳነሰኝ ይላል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَلَّا بَل لَّا تُكْرِمُونَ ٱلْيَتِيمَ

Amharic Translation - Africa Academy17. በፍፁም! ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَحَٰٓضُّونَ عَلَىٰ طَعَامِ ٱلْمِسْكِينِ

Amharic Translation - Africa Academy18. ድሃንም በማብላት ላይ አትበረታቱም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَأْكُلُونَ ٱلتُّرَاثَ أَكْلًا لَّمًّا

Amharic Translation - Africa Academy19. የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል (ያለአግባብ) ትበላላችሁ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتُحِبُّونَ ٱلْمَالَ حُبًّا جَمًّا

Amharic Translation - Africa Academy20. ገንዘብንም አብዝታችሁ (አለቅጥ) ትወዳላችሁ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَلَّآ إِذَا دُكَّتِ ٱلْأَرْضُ دَكًّا دَكًّا

Amharic Translation - Africa Academy21. (ሰዎች ሆይ! ተዉ):: ታቀቡ:: ምድር ደጋግማ በተንኮታኮተች ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَآءَ رَبُّكَ وَٱلْمَلَكُ صَفًّا صَفًّا

Amharic Translation - Africa Academy22. ጌታህ በመጣና መላዕክትም በሰልፍ በሰልፍ ሆነው በመጡ ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجِا۟ىٓءَ يَوْمَئِذٍۭ بِجَهَنَّمَ يَوْمَئِذٍ يَتَذَكَّرُ ٱلْإِنسَٰنُ وَأَنَّىٰ لَهُ ٱلذِّكْرَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy23. ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው ሁሉ ጥፋቱን በትክክል ይገነዘባል። መገንዘቡ በየት በኩል (ይጥቀመው)?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَقُولُ يَٰلَيْتَنِى قَدَّمْتُ لِحَيَاتِى

Amharic Translation - Africa Academy24. "ወይ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ስራ) ባስቀደምኩ ኖሮ" ይላል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَيَوْمَئِذٍ لَّا يُعَذِّبُ عَذَابَهُۥٓ أَحَدٌ

Amharic Translation - Africa Academy25. በዚያ ቀንም የእርሱን አቀጣጥ የመሰለ አንድም አካል አይቀጣም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا يُوثِقُ وَثَاقَهُۥٓ أَحَدٌ

Amharic Translation - Africa Academy26. የእርሱንም፤አሰተሳሰር አንድም አካል አያስርም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيَّتُهَا ٱلنَّفْسُ ٱلْمُطْمَئِنَّةُ

Amharic Translation - Africa Academy27. (ለአመነች ነፍስም እንዲህ ትባላለች)፡- አንቺ በአላህ የረካሺው ነፍስ ሆይ!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱرْجِعِىٓ إِلَىٰ رَبِّكِ رَاضِيَةً مَّرْضِيَّةً

Amharic Translation - Africa Academy28. (ከእርሱም) የወደድሽ፤ (እርሱ ዘንድም) የተወደደሽ ሆነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱدْخُلِى فِى عِبَٰدِى

Amharic Translation - Africa Academy29. ከዉድ ባሮቼም ጋር ተቀላቀይ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱدْخُلِى جَنَّتِى

Amharic Translation - Africa Academy30. ወደ ገነቴም ግቢ ትባላለች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70