caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Ghaashiya الغاشية

26 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 68

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ هَلْ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ٱلْغَٰشِيَةِ

Amharic Translation - Africa Academy1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሸፋኝቱ ትንሳኤ ወሬ መጣልህን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ خَٰشِعَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy2. በዚያ ቀን የከሓዲያን ፊቶች ተዋራጆች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَامِلَةٌ نَّاصِبَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy3. ሰሪዎች ለፊዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَصْلَىٰ نَارًا حَامِيَةً

Amharic Translation - Africa Academy4. የምታቃጥልን እሳት ይገባሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تُسْقَىٰ مِنْ عَيْنٍ ءَانِيَةٍ

Amharic Translation - Africa Academy5. በጣም ከፈላች ምንጭም ይጋታሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّيْسَ لَهُمْ طَعَامٌ إِلَّا مِن ضَرِيعٍ

Amharic Translation - Africa Academy6. ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃማ) ዛፍ እንጂ ሌላ ምግብ የላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا يُسْمِنُ وَلَا يُغْنِى مِن جُوعٍ

Amharic Translation - Africa Academy7. አካልን አያሰባ፤ ከረኃብም አያብቃቃ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاعِمَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy8. (የአማንያን) ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّسَعْيِهَا رَاضِيَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy9. በስራቸውም ተደሳቾች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِى جَنَّةٍ عَالِيَةٍ

Amharic Translation - Africa Academy10. በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا تَسْمَعُ فِيهَا لَٰغِيَةً

Amharic Translation - Africa Academy11. በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِيهَا عَيْنٌ جَارِيَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy12. በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِيهَا سُرُرٌ مَّرْفُوعَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy13. በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَكْوَابٌ مَّوْضُوعَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy14. በተርታ የተኖሩ ኩባያዎችም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنَمَارِقُ مَصْفُوفَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy15. የተደረደሩ መከዳዎችም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَزَرَابِىُّ مَبْثُوثَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy16. የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አሉ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى ٱلْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ

Amharic Translation - Africa Academy17. (ከሓዲያን) ግመል እንዴት እንደተፈጠረች አይመለከቱምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِلَى ٱلسَّمَآءِ كَيْفَ رُفِعَتْ

Amharic Translation - Africa Academy18. ሰማይም እንዴት ከፍ እንደተደረገች!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِلَى ٱلْجِبَالِ كَيْفَ نُصِبَتْ

Amharic Translation - Africa Academy19. ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِلَى ٱلْأَرْضِ كَيْفَ سُطِحَتْ

Amharic Translation - Africa Academy20. ምድርም እንዴት እንደተዘረጋች አይመለከቱምን?!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَذَكِّرْ إِنَّمَآ أَنتَ مُذَكِّرٌ

Amharic Translation - Africa Academy21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስታውስም:: አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّسْتَ عَلَيْهِم بِمُصَيْطِرٍ

Amharic Translation - Africa Academy22. በእነርሱ ላይ አስገዳጅ (ተሿሚ) አይደለህም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا مَن تَوَلَّىٰ وَكَفَرَ

Amharic Translation - Africa Academy23. ግን ከእውነት የዞረና የካደ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَيُعَذِّبُهُ ٱللَّهُ ٱلْعَذَابَ ٱلْأَكْبَرَ

Amharic Translation - Africa Academy24. አላህም ከባዱን ቅጣት ይቀጣዋል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ إِلَيْنَآ إِيَابَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy25. መመለሻቸው ወደ እኛ ብቻ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ إِنَّ عَلَيْنَا حِسَابَهُم

Amharic Translation - Africa Academy26. ምርመራቸዉም በእኛ ላይ ብቻ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70